
የአፍሪካ ሕብረት የወከላቸው የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዘዳንት ኦባሳንጆ ወደ መቀሌ በማምራት ከሕወሃቱ ዶር ደብረጽዪን ጋር ተነጋግረዋል። የዶር አብይ አህመድ መንግስትም ለድርድር ተዘጋጅቶ የፕሬዘዳንት ኦባሳንጆን ምላሽ እየጠበቀ ነው።
ይህ የመንግስት የመደራደር አካሄድ፣ ምን ያህል የሕወሃት ጦርነት ሰላባ የሆኑት የአፋርና የአማራ ክልል መስተዳደሮች እንደሚያውቅት አላውቅም። እነዚህ ክልሎች ክተት አውጀው ባለበት ሁኔታ፣ የፌዴራል መንግስቱ ግልጽነት በሌላው መልኩ፣ ብቻውን ፣ የአማራውናን የአፋር ማሀብረሰብ ተወካዮች አግሎ፣ በተናጥል የሚያደርጋቸው “ድርድሮች” ምን ያህል አዋጭ እንደሆነ አይገባኝም። ተገቢም ናቸው ብዬ አላምንም።
ረፖርተር