246488410 2116478211836849 7252238005556177769 nየኢፌዲሪ አየር ኃይል በመቐለ ከተማ የሚገኙና አሸባሪ ቡድኑ ለሽብር ተግባሩ የሚጠቀምባቸውን ስፍራዎች፣ እና መሳሪያዎች ላይ ካለፈው ሰኞ ጀምሮ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል። መከላከያ ሰራዊቱ በአየር ኃይሉ አማካኝነት በመቐለ ከተማ የሚገኙ የግንኙነት መሳሪያዎችን እና ታወሮችን የሽብር ቡድኑ ሲጠቀምባቸው መቆየቱን በማረጋገጥ እርምጃ የወሰደ ሲሆን ዛሬም የአስቸኳይ ጊዜ ማጣሪያ ባወጣው መረጃ የሽብር ቡድኑ ለመሳሪያ ማከማቻነት እና ለጥፋት ስራው የሚጠቀምባቸው አካባቢዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን አረጋግጧል።