የፍትህ ምኒስትሩ ዶክተር ጌድዮን ጢሞቲዎስ የመንግስት ባለስልጣን ከመሆኑ ጥቂት ቀደም ብሎ በትዊተር ገጹ ላይ የሚከተለውን አስፍሮ ነበር። “በፖለቲካ ውሳኔ፣ ለፖለቲካ አላማ ክስ ይመሰረታል። በፖለቲካ ውሳኔ፣ለፖለቲካ አላማ ክስ ይቋረጣል። ስልጣንን ለመጠበቅ ሰዎች ይታሰራሉ፣ ስልጣንን ለማቆየት ደግሞ ይፈታሉ። ሕግ ሙሉ በሙሉ በፖለቲካ ሞግዚትነት ስር በሚያድርበት ሀገር፣ ሕግ ለሃቅና ለፍትህ ባዳ ሆኖ በፍርድ አደባባይ ሸፍጥ ይገናል። ለማንኛውም፣ ፓርላማ ልናያቸው ሲገባ ዘብጥያ የከረሙት ሊፈቱ