June 23, 2022
6 mins read

ይህ ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሙከ ጡሪ ውጫሌ ወረዳ ሰሜን ሸዋ ዞን ነው። ሸኔ አማራን ለማፅዳት በአብይ አህመድ የተመሰረተ ጦር

289270244 2666812546785901 46589885988475758 nይህ ከአዲስ አበባ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው #ሙከ_ጡሪ ውጫሌ ወረዳ ሰሜን ሸዋ ዞን ነው። ሸኔ አማራን ለማፅዳት በአብይ አህመድ የተመሰረተ ጦር ነው የምንለው ያለ ምክንያት አይደለም።

ፈለገ ግዮን

287991934 2666812496785906 987661575801547264 n

 

“የአማራ ህዝብ በክንዱ፣ በትግሉ ሰብዓዊ ክብሩን እንደሚያስመልስ ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም” – መስከረም አበራ

አካሌ ከእስር ሲፈታ አእምሮዬ የሚያስበውን የምፅፍባቸው “Devices” (ስልኬ፣ Lap topዬ ) ከእስር አልተፈቱም። አካውንቶቼ ሁሉ ይበጃል ብዬ ባደረግኩት “Two step verification adjustment” ምክንያት ስልኬ እጄ ላይ ሳይኖር አካውንቶቼን መክፈት አልቻልኩም። ስለሆነም ታስሬ በነበረበት ወቅት እኔንም፣ የጨቅላ አራስ ልጄንም፣የቤተሰቤንም ጩኸት ለጮሃችሁልኝ ውዶቼ ምስጋና ማቅረብ እንኳን አልቻልኩም። ዛሬ ግን የባሰው ስለመጣ በባለቤቴ አካውንት መጣሁ
ከቅርብ አመታት ወዲህ እየተባባሰ የመጣው የአማራ ህዝብ የሰቆቃ ኑሮና የውርደት ሞት አእምሮዬን ሰቅዞ ስለያዘኝ የገባሁበት የትግል መስመር በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እጅግ አደገኛው መስመር እንደሆነ ጠንቅቄ እረዳለሁና እስሩ ብዙ አላስገረመኝም፤ የዚህ ህዝብ አሰቃቂ ሞት እስኪያበቃ ድረስ ልሄድበት ለራሴ ከማልኩት ጉዞም የሚያስተጓጉለኝ አይሆንም – እንደውም ይበልጥ ያበረታኝ ይሆናል እንጅ!
ገና ከእስር ከመፈታቴ የጠበቀኝ በአሰቃቂነቱ ዓለምን ሁሉ ያነጋገረ የመከረኛው የአማራ ህዝብ ሞት ነው። ይህ የአማራ ህዝብ እልቂት ዛሬ የተጀመረ ይመስል ዓለምን ሁሉ ገና ዛሬ ማነጋገሩ ልክ ባይሆንም አውቆ የተኛ በተነሳ ሰዓትም ቢሆን የህዝባችንን መከራ ተረድቼ አዘንኩ ማለቱ የዓማራን ህዝብ የህልውና ትግል ያግዛል እንጅ ክፋት የለውም።ሆኖምየአማራ ህዝብ ለድፍን አራት አመት በር ተዘግቶበት ሲጨፈጨፍ አውቆ የተኛው ዓለም ዛሬ ለደረሰው ጭፍጨፋ አስተዋፅኦ እንዳለው መረሳት የለበትም።
የአማራ ህዝብ በትግሉ ሰብዓዊ ክብሩን ሲያስከብር ዓለም በሞቱ ላይ ጆሮውን ደፍኖ የኖረውን ዓለም ሁሉ በሩዋንዳው የዘር ፍጅት እንዳደረጉት ይቅርታ የሚጠይቁበት ዘመን ይመጣል።
እነዚህ ዘግይተው የነቁ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች፣ ኢምበሲዎች፣ ታዋቂ ዲፕሎማቶች እንኳን ጭፍጨፋው በአማራ ህዝብ ላይ በማንነቱ ምክንያት የተደረገ ጭፍጨፋ እንደሆነ አስረግጠው ሲናገሩ በማከብረው ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ኢሰመጉ “የንፁሃን ዜጎች ሞት” ሲሉ ወንጀሉን ያድበሰበሱበት ምን ለማግኘት እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም! እንዲህ ያለው የ”Genocide”ን ወንጀል የማድበስበስ አደገኛ አካሄድ ዘር ማጥፋቱን የሚያግዝ ብሎም የሚያባብስ እንደሆነ ጠንቅቄ ስለማውቅ በእነዚህ ሁለት ተቋማት አካሄድ እጅግ ማዘኔን መግለፅ እወዳለሁ!!!! ኢዜማ፣ኦፌኮ ፣ኦህዴድ፣ኦነግ ስላወጡት መግለጫ ምንም ማለት አያስፈልገኝም!!!!!
ከገዳይ በላይ፣ ከጭፍጨፋው ሰቆቃ በበለጠ ለሞቱ የሚሰጠው ስም እና ትርጉም እንደሚያሳዝነኝ ግን ሳልገልፅ አላልፍም። ሃዘኔን የሚያበረታው እንዲህ ያሉ አስመሳይ አካሄዶች ወደፊትም ይህን መሰል ጭፍጨፋ እንዳይከሰት የሚያግዙ ስላልሆኑ ነው! ሰው በስንቱ ያዝናል?
በእውነት ለመናገር አሁን ላይ የሚሰማኝን ስሜት ለመግለፅ ይቸግረኛል። ውስጤ ያለቅሳል፣ ጥቅመ ቢስነት አጥንቴን ዘልቆ ይሰማኛል፣ በሃገሬ ፖለቲካ ሁለመና ቂም ለመቋጠር ከሚዳዳው ልቤ ጋር ሙግት እገጥማለሁ፣ ነፍሴ “ምን ይሻላልን?” በማሰላሰል ትቃትታለች……የአማራ ህዝብ በክንዱ፣በትግሉ ሰብዓዊ ክብሩን እንደሚያስመልስ ግን ቅንጣት ያህል አልጠራጠርም! ለዚህ ህዝብ የሚወጣ ቀን አለ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop