ዛሬም ዜሮ ሊያደርጉን የሚፈልጉ አሉና እንንቃ!( የኢትዮጵያ ችግር በዘመናዊ ፉከራ እንደ በጋ ጉም በን ብሎ አይጠፋምና !!)

ዘመናዊ ፉከራ
ዛራፍ!ዘራፍ!ዘራፍ !! …
አካኪ !ዘራፍ!
ሮጬእገባለሁ ዘራፍ!…
ከእናቴ ቀሚስ!
ህዝብ ሲጯጯህ !ጀግና ሲጋደል!…
ሀገር ሲታመስ!
ህምምም! ህምምምም !….
ዘራፍ! ዘራፍ!
በአፍ ይጠፉ!
 በለፈለፉ ! …
በአንዱ ምላስ ነው!
እትት! ትት!ትት!
ሺዎቹ ጅሎች፣የሚቀሰፉ !
የአፍ ዴሞክራሲ፣ዘራፍ!ከቶ አይገባኝም   !
ዘራፍ!ዘራፍ!ዘራፍ!አካኪ ዘራፍ !
በአንደኛው ዳፋ  – ምች  አይመታኝም!
ዘራፍ!ዘራፍ ! ዘራፍ ! የጠቅል አሽከር!…
ዘራፍ! ዘራፍ ! ዘራፍ!የደርግ  አሽከር!!…
ዘራፍ!ዘራፍ ! ! ዘራፍ!ወያኔ አሽከር!!…
እያልክ፣እንደጦስ ዶሮ፣በላ ተሸከርከር !!     …
በላ!በላ!በላ !ተናገር !!!…
እኮ!በላ!በላ!በላ!ፎክር !!!
ዘራፍ!የጮማዬ ጌታ! … የጠጁ ጌታ!
ዘራፍ!ጠቅል ንጉሴ፣ዘራፍ!የአፍሪካ ባለውለታ!
ዘራፍአንተን !ገልብጦ፣ዘራፍ መንጌ መጣብኝ !!
ዘራፍ!”ቀይሽብር” እያለ፣ደርግ ውሻ  አደረገኝ፣
ዘራፍ!ዘራፍ!እያለ !በአደባባይ ረፈረፈኝ፣
“የፍየል ወጠጤ  ትክሻው ያበጠ ልቡም ያበጠበት
ና እነዋጋ ብሎ ለነበር ላከበት፣
የማትረባ ፍየል ዘጠኝ  ትወልዳለች፣
ልጆቿም የልቃሉ አሷም ትሞታለች፡፡”
እያለ በህዘብ ፊት አቅራራብኝ፤
ዘራፍ! ዘራፍ! በቀንፀሐዬንአጨለመብኝ !!…
ዘራፍ!ዘራፍ ! አካኪዘራፍ!ይህንን አይቶ !
ደሙፈላና ፣ወጣት ተደራጀ በርሃ ገብቶ!
እትት! እንቢ!ባርነት!ብሎም ወይኖ…
ነጻ አወጣ ተጨቋኙን ህዘብ፣ በትግሉ ገኖ !
ዘራፍ!”ኢህአዴግ “ነኝ በማለት ሥሙን አወጀ፣
ዘራፍ!አካኪ! ዘራፍ!…
ነፃነት አሁን በማለት ህዝብ አደራጀ፤
በህዝቦች ህብረት ደርግን ጣለና!
ዲሞክራሲ ነፃነት  እነሆ አለ ይኸው በቁና !!
እንሆ፣ዛሬ!በላ! በላ !በላ !…
ዘራፍ!ዘራፍ !አካኪዘራፍ!
ዘራፍ! ዘራፍ!  ይስፍን ዲሞክራሲ!
ዘራፍ!ዘራፍ!ተቀበል አብይ! ሲፅፍ ሃያሲ
እትትትትት!እትትትትት!ዘራፍ !ልበል ዛሬ !!
አካኪ ዘራፍ!ዘራፍ!ዘራፍ፣ዘራፍ!…
ልቀቁኝ አትገድቡኝ ይውጣልኝ ተናግሬ!……
በ2011 ተሻሽሎ የተፃፈ
መኮንን ሻውል ወ/ጊ
በ2004 የተፃፈ ና ያልታተመ ግጥሜ ነው።
     ከምድር በፊት ሰው አልተፈጠረም ።ከምድሪቷም ውሥጥ አልፈላም።ከምድር ቢፈላ ኖሮ ፣እንደ ዕጽዋት ይሆን ነበር። ሰው እንደ እፅዋት  ሳይሆን እንደ ሰው ተፈጥሯል። የፈጠረውም በፍጡሩ ሊመረመር አይችልም? ሮቦት ፈጣሪውን ሊጠይቀው ፣ለምን ብሎ ሊከሰው ይቅርና የፈጠረውን አያውቀውም። (በአንዳንድ ፊልሞች ፈጣሪያቸውን የሚያውቁ ሮቦቶችን፣የሰው ባህሪ ያላቸውን የአኒሜሽን ፈጠራዎች ማየታችንን እርግጥ ነው።ይሁን እንጂ ይህ ልቦለድ ነው።)
    ሰው ሸክላ ነው ።ለእግዜር።እንደወደደ ሰርቶታል። “ለምን እንዲህ አድርገህ ሰራኸኝ? ” ብሎ የሰው ልጅ ቢጠይቅም መልስ አያገኝም።
     ሰው፣ሲፈጠር አንድ ከሆነ ፣ መልኩ ለምን ዠንጉርጉር ሆነ? ነጭ፣ቢጫ፣ ጥቁር ፣ ክልስ ፣ ወዘተ ።” ይህ የምድር አየር ንብረት ያሥከተለው ጣጣ ነው። “ብለን እንደምድም። ።ወይሥ ይህንን የሚተካ ሌላ ታሪክ እንፍጠር?
      ” ፈጣሪ ኑ በአምሳላችን ሰውን እንፍጠር ” ብሎ ሰውን ፈጠረው። ከእርሱ ጋር ሰው መሳይ ሰዎች ነበሩ ። እነዚህ ሰዎችም ወደምድር ተጥለዋል።የቀለም ልዩነትም የተከሰተው ከዛ አንፃር ነው። በፈጣሪ የመፍጠር ሂደት የተፈጠሩ ፣የተለያየ ቀለም ያላቸው ወንድና ሴቶች ነበሩ። ዛሬም ፈጣሪ መፍጠሩ አላባራም።በኢትዮጵያ እንኳ አሥገራሚ የጠፈር ሊቆችን እየፈጠረ ነው።ገና እንቦቃቅላ የሆኑ ግን ደግሞ ፒኤችዲ ካላቸው ጎልማሶች የላቀ አእምሮ  ያላቸውን …(ይህ አፈ ታሪክ ነው ዩኔ ሃሳብም ብቻም አይደለም።)
     እምነታችሁ የየራሳችሁ ነው።በበኩሌ በማንም እምነት ጣልቃ አልገባም ።በተጠለላችሁበት ና ” ከሞት ባሻገር የምንኖርበትን የዘላለም ህይወት የሚያጎናፅፈን ፣ ኃይማኖት ይሄ ነው።”የምትሉም ባላችሁበት ጽኑ። ትክክል ናችሁ። ማንም ሞቶ መቅረትን ከቶም አይፈልግም።
  ይሁን እንጂ     ይህ ጭንቀት  ፣የሁሉም ሰዎች አይደለም። እስከዛሬም በራቁትነት የሚኖሩ አሉና።ከቶም ባዶነታቸውን ያልተረዱ ፣በሥድነት መለመላቸውን የሚጎዙ፣አያሌ ሰዎች በዚች ምድር ያለ ህሊና እንደሚጓዙም አትዘንጉ።
    ህሊና ሥለሌላቸው ፣  የራሳቸው ጥቅም እንጂ የሌላው ሀገር ጥቅም ቅንጣት ያህል የማያሥጨንቃቸው የመንግሥት መሪዎች … የራሳቸውና በዘር ተሰባሥበው የፈጠሩት  ፓርቲ አባላት  ጥቅም እንጂ የሌሎች ዜጎች ጥቅም ጉዳያቸው ያልሆነ የፓርቲ መሪዎች … ከነዚህ ባዶነታቸውን ካልተረዱ ሆኖም እሥከዛሬም በዜሮ ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ይደመራሉ።
   ዓለም በእኩይ ድርጊት በተደጋጋሚ  የምትናጠው ዜሮነታቸውን ባለማወቅ ፣እሥከነ አሥጠሊ ገበናቸው የሚመፃደቁ  ግለሰቦች በየሀገሩ ፣ በማይገባቸው የመሪነት ሥፍራ ፣አጋጣሚው፣ ፈቅዶላቸው፣ ተቀምጠው ፣   በዘፈቀደ የዕለት ትርፋቸውን ብቻ በማየት ፣በህሊና ቢሥነት  ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ሥለሚመሯት ነው።
       ይህችን የኛዋንም  ሀገር ፣ ትላንት ወደኋላ ያሥቀሯት ፣ እነዚህ ነበሩ። ዛሬም ይህንን  እውነት በመገንዘብ  ራቁቱን መፈጠሩን እና ራቁትነቱን ፣ በጥበብ በማደሥ ፣ለትውልዱ ራቁትነትን ሣይሆን ብልፅግናን ለማውረስ የሚተጋን ፣ትንታግ ትውልድ የሚገዳደሩ ፣እነዚሁ ናቸው።
      ኢትዮጵያዊያን እንንቃ !!  ትላንት በዘር ና በጎሣ ከፋፍለውን ፣እኛ ሥንደኸይ እነሱ በልፅገዋል።ዛሬ ደግሞ አንገታችንን  ቀና ሥናደርግ በሥውር እጃቸው ሊኮረኩሙን ዜሮ ሊያዱርጉን ይፈልጋሉና !!…
ተጨማሪ ያንብቡ:  የጥንታዌት ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን  አጭር ታሪክና ሥርዓት
Share