ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ

ከጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ጋር የተለያየው ዩጋንዳዊው አማካኝ ያሳር ሙጊርዋ በሰአታት ልዩነት ውስጥ የትግራዩን ሽሬ ከነማ እንደተቀላቀለ ተሰማ፡፡

https://www.youtube.com/watch?v=ZdkEBlHGPDA&t=1s

የኡጋንዳው ካዎዎ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ተጨዋቹ ከአዲሱ ክለቡ ሽሬ ጋር ለአንድ አመት የሚቆይ ውል ተፈራርሟል፡፡ የውሉ መጠን በምስጢር እንዲያዝ የተወሰነ ቢሆንም ጋዜጣው ምንጮቹን ጠቅሶ ለፊርማ ከ25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ እንደተከፈለው ዘግቧል፡፡ ተጨዋቹ ከደቡብ አፍሪካው ኦርላንዶ ፓይሬትስ ክለብ በመጀመሪያ ወደኢትዮጵያ የመጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ በመፈረም ነበር፡፡ በመቀጠል ከፋሲል ከነማ ጋር የሁለት አመት ውል ፈፅሞ ወደጎንደር ሊያመራ ችሏል፡፡

 

ተጨዋቹ ከፋሲል ከነማ ክለብ ጋር ያለው ውል ያልተጠናቀቀና አምስት ወር የሚቀረው ቢሆንም ለክለቡ ቤተሰባዊ ምክንያት አቅርቦ በስምምነት ስምምነቱ መቀደዱ ይታወቃል፡፡  ያሳር ሙጊርዋ ዛሬ ለንባብ ለበቃው ጋዜጣው ሲናገር ‹‹የሽሬ እግር ኳስ ክለብ አባል በመሆኔ ደስተኛ ነኝ፡፡ ህይወት የአዳዲስ ፈተናዎች ጉዞ ናትና በአዲሱ ቤቴ ጥሩ ለመስራት ዝግጁ ነኝ›› ብሏል፡፡ ሽሬ እግር ኳስ ክለብ ዘንድሮ የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ የተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል፡:

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የ5000 ሜትር ሪከርድ አሻሽላለች
Share