የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ም/ዋና ዳይሬክተር የነበረውና ሲፈለግ የቆየው ዶ/ር ሐሺም ቶፊቅተይዞ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ግለሰቡ ከሌሎች ሶስት ተጠርጣሪዎች ጋር ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሙስና ክስ ቀርቦበታል፡፡ ከዶ/ር ሀሺም ጋር ፍርድ ቤት የቀረቡት ፊልሞን ግርማይ እና ቴዎድሮስ ያዕቆብ የተባሉት ግለሰቦች በወንጀል የሚፈለጉ የተጠርጣሪዎችን ሰነድ በመደበቅና በማሸሽም ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
ግለሰቦቹ በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀል ከሚፈለጉትና የደህንነት ከፍተኛ የስራ ኃላፊ ከነበሩት ከአቶ ተስፋዬ ገብረፃድቅ ቤት ሰነድ አሽሽተዋል በሚል የተጠረጠሩ ሲሆን፣ ዶ/ር ሐሺም ደግሞ በወንጀል የተጠረጠረችውን ባለቤታቸውን ዊዳድ አህመድና ወንድሟን ሰሚር አህመድ በተሽከርካሪ ወደ መቀሌ በማሽሽና ሰነድ በመደበቅ ተከሰዋል፡፡
ዶ/ር ሀሺም የተጠረጠሩበት ወንጀል ከባድ መሆኑን ያስረዳው ፖሊስ በባለቤታቸው ስም ምንጩ ያልታወቀ ሀብት እንዳፈሩና ያንን እያጣራ መሆኑን ጠቁሟል፡፡
ከአቶ ተስፋዬ ገ/ፃድቅ ቤት ሰነድ በማሸሽ የተጠረጠሩት ፊልሞን ግርማይና ቴዎድሮስ ያዕቆብ የጦር መሳያና ሁለት ቦምቦችን ከተፈላጊው ቤት አውጥው ሲሸሹ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውንም ፖሊስ አስረድቷል፡፡
በመኆኑም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የተጠየቀው ጊዜ ቀጠሮ ተፈቅዶ መዝገቡ ለህዳር 17 ተቀጥሯል፡:
https://www.youtube.com/watch?v=W20KYng_SXM