የኢትዮጵያ መንግስት ፌስቡክን ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ሊዘጋ ነው

November 5, 2013

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ መንግስት ፌስቡክን ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ሊዘጋ መሆኑን የዘ-ሐበሻ ታማኝ ምንጮች ገለጹ። ከአዲስ አበባ የመጡ መረጃዎች እንደጠቆሙት ሕዝቡ በተለይ ነፃ ሚዲያ በሌለበት ሃገር መረጃዎችን ከፌስቡክ በቀላሉ ማግኘት በመቻሉና የንቃት ደረጃውም እየጠነከረ በመሄዱ   የሃይለማርያም ደሳለኝ መንግስት “በመንግስት መሥሪያ ቤቶች እና በትምህርት ቤቶች በከፍተኛ ሁኔታ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር እየበዛ በመምጣቱ የመማር ማስተማሩን ሂደትም ሆነ የሥራ ሁኔታዎችን አስተጓጉሏል” በሚል ሰንካላ ምክንያት የፌስቡክን አገልግሎት ለማገድ ተዘጋጅቷል።

በግብጽም ሆነ በቱኒዚያ የተነሱት የአረቡ ዓለም አብዮቶች አድማሳቸው በአንድ ጊዜ የተንሰራፋው እንደፌስቡክ ባሉ ቀላል የማህበራዊ ሚዲያዎች መሆኑን የተረዳው የኢትዮጵያ መንግስት ነፃ ጋዜጦችን ዘግቶ ሁሉን ሚዲያ በተቆጣጠረበት በዚህ ዘመን እንደ ዘሐበሻ እና ሌሎችም ያሉ የኢትዮጵያ ድረገጾች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይታዩ ቢታገዱም በፌስቡክ እና በትዊተር አማካኝነት በሰፊው እየተነበቡ በመሆኑ መንግስት “ተማሪዎች ፌስቡk እየተጠቀሙ በትምህርታቸው ደካማ ሆኑ፤ የመንግስት ሠራተኞችም ሥራቸውን ጥለው ፌስቡክ ላይ እየተጣዱ የመንግስትን ሥራ እየበደሉ ነው” በሚሉ አንካሳ ምክንያቶች ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ለማገድ መዘጋጀቱን ምንጮቻችን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ቁጥር በ እጅጉ እየጨመረ መሄዱና መንግስት እንዲሰሙ የማይፈልጋቸው መረጃዎችም በአጭር ጊዜ ሕዝብ ጋር መድረሳቸው የስርዓቱ ራስ ምታት እየሆነ መምጣቱን በተደጋጋሚ መዘገባችን አይዘነጋም።

13 Comments

 1. bewnetu betam yemidegef hasab new mikniatum asamagn new senkala bilo yemiasb sew kale astesasebu new enji senkala mikniatu aydelem besira botam hone be timhirt bet eyefetere yalewn chigr lemasweged bians hizbu negerochin be program yemasked nikate hilinaw eskidabr dires bizega melkam new be ahunu seat sewoch gizeachewn yalagbab eyabakenu new

 2. ድሮ የመንግስቱ ሚስት መርካቶ ወጥታ እቃ ስትገዛዛ እዛ “ፈስ ተፈሳ”፣ እሱዋም ማን ነው የፈሳው እያለች ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል፣አንዱ በሹክሹክታ “ባሉዋ አፋችንን ዘጋው እሱዋ ደግሞ እንትናችንን ልትዘጋው ነው እንዴ ” አለ ይባላል።
  አሁንም ሜዲያዎቹ ሁሉ ተዘጉ ፌስቡክም ሊዘጋ ነው እንዴ?

 3. Ay woyane gira gebtosh keresh endihu? Emiseraw yelelew serategna fb bitekem min cheger alew yenantenpolitikegnoch kemawara

 4. @አቤል
  ባአለም ላይ በስራ የበለፀጉ ሀገሮች ናቸው ፌስ ቡክን የፈጠሩት፣ እነሱ እንኩዋን አልከለከሉም። ሰራተኞች በስራቸው ላይ ሀላፊነትን የሚወስዱት ራሳቸውና መስሪያቤቱ ነው።ተማሪዎችና ትምህርት ቤትም እነዲሁ፣ ካልተሳሳትኩ በዚህ ምክንያት በሀገሪቱ ውስጥ ፌስ ቡክ የመዝጋት ጉዳይ ከሆነ ግን የኖርዝ ኮሪያና የኤርትራ አይነት ነገር ነው።ምነው ዜጎች በእፅ ኮንሰምሺንና በስራ አጥነት ጊዜያቸውን በከንቱ ሲያጠፉ ለምን እዚያ ላይ ትኩረት አልተሰጠም።ፌስ ቡክ በሀገሪቱ መዝጋትማለት የዜጎችን መብት መርገጥ ነው፣የስራንም ትርጉም አለማወቅ ነው። እንደ ሀይማኖቱ በ ሶሻል ሜዲያ ላይ ጣልቃ እንደ መግባት ነወ።

 5. አቶ አቤል፡- ስለሌላው ኢትዮጵያዊ ጊዜ ማባከን መቆርቆርህን ትተህ ስለራስህ አስብ፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብም ስለራሱ አስቦ የማንበብ፣ በራሱ የመማር ወይንም ከመረጠ ጊዜውን የማጥፋት መብቱን አንተ ወይንም የአንተ አገዛዝ አይወስንለትም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳንተና እንደ ቢጤህ ወያኔ ደደብ እንዳይመስልህ!

 6. I am happy and most parents would be happy too. Because facebook spoiled kids will focus on their education.

  • @brook, ትንሽ አታፍርም? አሁን አንተ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የበለጠ አዋቂ ስለሆንክ ነው ኢንተርኔት የምትጠቀመው? ኢትዮጵያ ከዓለም ሀገራት የተለየ ዓለም ውስጥ ነው እንዴ ያለችው? ወያኔ እኔ ከሌለሁ ህዝብ ይበላሻል፤ በትምህርቱም ሰነፍ ይሆናል የሚለው አባዜ ድድብናው ጣሪያn መንካቱን ከሚያሳይ ውጪ ሌላ ሊባል አይችልም። ሶሻል ሚዲያ የተከለከሉባቸው ሀገራት ሰሜን ኮሪያ፤ ኢራን በትምህርት ከማን በልጠዋል? shame for BROOK’S dull mind.

   • Dr. Larry D. Rosen, a professor of psychology at California State University, has been studying the effects of technology on people for more than 25 years.

    Dr. Rosen’s study found the following worrisome details:

    • Teenagers and young adults who are persistently logged on to Facebook are more often to show psychological disorders, like mania, paranoia, aggressive tendencies , antisocial behavior and increased alcohol use. These teens also more often displayed narcissistic tendencies, which are fed by their ability to constantly broadcast information about themselves through Facebook.

    • Children, pre-teens and teenagers who used technology, like the Internet and video games, on a regular basis have more stomach aches, sleeping problems, anxiety and depression. They also miss school more often.

    • Not surprisingly, middle school and high school students who logged into Facebook at least once during a 15-minute study session received lower grades. Rosen and his team found that most students were only able to maintain focus on their studies for two or three minutes before distracting themselves with technology, like text messages, mobile apps or the Web.

    • Rosen also revealed that the average teenager sends approximately 2,000 text messages per month, a massive amount of information processing that has been founded to be related to problems with sleep and concentration, as well as physical stress.

    I hope you will understand my concern.

 7. Good job mister pm hailemariam Desalegn Thank you so mach now please destroy tplf and its intelegence and the military…. and tigrians……good job

 8. Good job mister pm hailemariam Desalegn Thank you so mach now please destroy tplf and its intelegence and the military…. and tigrians……good job temesasleh gebteh kulachew…..yemeles raey eyalk shewdachew…thank u hailemariam and his grupe….now arest azeb…..

 9. Then why until 9:00 pm? If the problems are school and workplaces then why is necessary to close FB evenings??

 10. facebook laye erasu bezu memariya pejoche alu ename ende techemari insteractionale media mewsede yechalale kematefate lejochune endeZi ayenete pegoche enditeqemu degafe maderege teru new wanawe gene lesrategnaweme hone letemariwe mechu huneta mefetre teru new lelaweme yeziche melekamu qertobate astedadere yenafeqate hager newari new hulune yamakele hege enafeqalene l

Comments are closed.

Previous Story

የፖለቲካው ስር ቁማርተኞች! (ተመስገን ደሳለኝ)

8968
Next Story

ጥጋበኞቹ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሱማሊኛ ሙዚቃ በሸራተን ሲደንሱ የሚያሳይ ቪድዮ

Latest from Blog

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የሚደነግግ አዋጅ ቀረበ

ዮሐንስ አንበርብር በጥፋተኝነት ላይ ያልተመሠረተ ንብረት የመውረስ ድንጋጌም በአዋጁ ተካቷል አዋጁ የሚፀድቅ ከሆነ 10 ዓመት ወደኃላ ተመልሶ ተፈጻሚ ይሆናል ከውጭ በተላከ ገንዘብ ሀብት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ሰው ወይም ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሀብት አፍርቶ ምንጩ ሕጋዊ መሆኑን ማረጋገጥ ያልቻለ ሰው፣ ንብረት በመንግሥት እንዲወረስ የሚፈቅድ ድንጋጌ የያዘ
Go toTop