December 1, 2016
18 mins read

የመደራጀት መብት ግዴትም አለበት (ይገረም አለሙ)

ለማናቸውም ዓላማ ሰዎች ተሰባስበው ድርጅት የመፍጠር መብት አላቸው፤ በአንጻሩ ለድርጅታቸው የሚሰጡት መጠሪያ እናራምደዋለን የሚሉት ዓላማ እና እንደርስበታለን የሚሉት ግብ በተናጠል ግለሰብንም ሆነ በወል ማህበረሰብንና ሀገርን ሊነካ ስለሚችል ከዚህ አንጻር ሊፈጽሙት የሚገባ ግዴት አለባቸው፡፡ በመሆኑም በህገ መንግሥትም ሆነ በፓርቲዎች ማቋቋሚያ አዎጆች ውስጥ እነዚህ ከመደራጀት አንጻር ተግባራዊ የሚሆኑ መብቶችና ግዴታዎች ሰፍረው ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን በፌስ ቡክ ድርጅት ሲመሰረት የመስራቾቹ ቅን ፍላጎትና ራስን ለህግ የማስገዛት ሰውነት ከሌለ በስተቀር ለሕግም ለሞራልም ግዴታዎች እንዲገዙ የሚገደዱበት ሁኔታ አይኖርም፡፡ ይህም በመሆኑ ነው አንዳንዶች በፈለግነው ስም ለፈልግነው ዓላማና ግብ የፈለግነውን የህብረተሰብ ክፍል/ሕዝብ እንወክላለን ብለን መደራጀት መብታችን ነው፣ለምን ብላችሁ አትጠይቁን፣,እንዴት ብላችሁ አትናገሩን የሚሉት፡፡ ስለ ራሳቸው የመደራጀት መብት ሽንጣቸውን ገትረው ሲከራከሩና አትናገሩን ብለው ሲፎክሩ እንወክልሀለን ብለው ስሙን በመጠሪያነት፣ ብሶት በደሉን በመቀስቀሻነት፣ የሚጠቀሙበት ግለሰብም ይሁን ህብረተሰብ የመጠየቅ የመተቸት የመቃወም በጣም ከገፋም በህግ እስከማስቆም መብት እንዳለው የተረዱ አይመስልም፡፡ ይህን ቢያውቁ ኖሮ ዓላማቸውን አስረድተው በሚችሉት አቅም የሚሉትን በተግባር ሆነው በመገኘት ደጋፊ ለማብዛት ይጣጣሩ ነበር እንጂ በጩኸት በዘለፋና በስድብ አፍ ለማስያዝ ተቆጣጣሪ የሌለውን ማህበራዊ መገናኛ ሲያናውጡት ባልታዩ ነበር፡፡ በማህበራዊ መገናኛዎች የምናነባቸውና የምንሰማቸው አንዳንዶቹ የሚጠቀሙዋቸው ቃላቶች አይደለም ፖለቲካ ሊያራምዱና ለወግ ማእረግ በቅተው የሀገር ሀላፊነት ሊሸከሙ ቀርቶ በኢትዮጵያዊ ባህልና ጨዋነት ተኮትኩተው ማደጋቸውን እንኳን እንድንጠራጠር የሚያደርጉ ናቸው፡፡ መቼም ፖለቲከኛ ነን በሚሉ ሰዎች ዘንድ ሕዝብ እና ዴሞክራሲ እንደሚባሉ ቃላቶች መቀለጃም ማላጋጨም የሆነ የለምና ማንነታቸውም ቁጥራቸውም የማይታወቅ ሰዎች ተነስተው አርማ ሰርተው ሰም አውጥተው እከሌ የሚባለውን ህዝብ እንወክላለን ብለው በፌስ ቡክ ብቅ ሲሉ እንወክልሀለን ያሉት የህብረተሰብ ክፍል አባል የሆነ ግለሰብም ይሁን ቡድን ማናችሁ ብሎ ሲጠይቅ፣ የያዛችሁት ዓላማ እኔን አይወክልም፣እንደርስበታልን የምትሉት ግብም የእኔ ራዕይ አይደለም በማለት ሙግት ሲያቀርብ በርግጥ ዓላማ ያላቸው ታግሎ ለማታገል ቆርጠው የተነሱ፣ ወዘተ ከሆኑ ለጥያቄው መልስ ለሙግቱ በመረጃ የተደገፈ መከራከሪያ ማቅረብ ነው የሚጠበቅባቸው፡፡ የምናይ የምንሰማው ግን ይህን የምትጠይቅ አንተ የእኛ ሰው አይደለህም፣ እንዲህ የምትሟገተው ወያኔ ስለሆንክ ነው ወዘተ የሚሉ ምላሾችን ነው፡፡ እንዲህ የሚሉት ሰዎች መሰረትነው የሚሉት ድርጅት ከአየር ላይ ወርዶ መሬት ያረገጠ፣ የመሪዎቹ ማንነት ያልተለየ፣ የአመራር አባሎቹ ስንትነት ያልታወቀ መደራጀት መብታችን ነው ከማለት ያለፈና ከፌስ ቡክ ፉከራ የዘለለ የሚታይ ተግባር የሌላቸው መሆናቸው በጀ እንጂ እንደ ፉከራቸው በተግባር ያሉ ቢሆኑ እንደ ትናንቱ ተውልድ የርስ በርስ ትልልቅ በተፈጠረ ነበር፡፡ እባብ የልቡን አይቶ አግር ነሳው ነው የሚባለው፡፡ ከለማበት የተጋባበት እንዲሉ የትናንቶቹ አንዳላዋጣ አይተው እየተዉት ያለውን ዘረኝነት በአዲስ ወኔ የተያያዙት ወገኖች አንደሚሉት በወያኔ አገዛዝ በህዝብ ላይ የተፈጸመውና አሁንም የሚፈጸመው በደል አማራ ኦሮሞ ኮንሶ ጋምቤላ ብሎ የለየ አይደለም፡፡ ጥቃት ፈጻሚው ወያኔ ተጠቂው ሁሉም ኢትዮያዊ ሆኖ ሳለ እነርሱ አንወክለዋለን የሚሉት ህብረተሰብ/ሕዝብ ጥቃት የደረሰሰበት በማንነቱ ነው የሚለው ዘረኛ ቅስቀሳ የተፈለገው አንድም ህዝብን ለማነሳሳት ቀላሉ መንገድና ስሱ ብልት እሱ በመሆኑ ሁለትም ወያኔ ለሥልጣን የበቃው በዚህ መንገድ ነው ከሚል እሳቤ ነው፡፡ የእኔ ብሔር አባላት በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ነው በወያኔ የሚጠቁት የሚሉን ወገኖች ቢያንስ ሁለት ጥያቄዎችን መመለስ ይጠበቅባቸዋል ግን አይሞክሩትም፡፡ አንደኛ ከእነርሱ ብሄር ውጪ የሆኑት ከ80 በላይ የሚሆኑት የሌሎች ብሄር ብሄረሰብ አባላት ኢትዮጵያውያን በወያኔ ምንም በደል አልደረሰባቸውም ማለት ነው? ሁለተኛ በብሄሩ ምክንያት ብቻ ነው የተጠቃው ከሚሉት ብሄር አባላት አብዛኛው ቁጥር በአንድ ወይንም በሌላ መልኩ ቀጥተኛ ጥቃት ያልደረሰበት ነውና ይህን ምን ይሉታል? ወይንስ በወያኔ የተጠቃው ብቻ ነው የዛ ብሄር አባል ተብሎ ሊገለጽ የሚችለው? በተግባር ከደረሰበኝም ሆነ በቅርብ በሌሎች ሲደርስ ካየሁት የተረዳሁት እኔ ሰው ነኝ ክብር ያለኝ ነጻነት ያለኝ፣ ለአምባገነን አገዛዝ አላጎበድድም፣ ህሊናየን ለሆድ አልለውጥም፣ በሰውነት መብቴ አልደራደርም፣ሕግ አክብሬ ሕግም ተከብሮልኝ መኖር ነው የምሻው ወዘተ ያለ ማናቸውም ኢትዮጵያዊ አማራ ኦሮሞ ትግሬ ጉራጌ ጋምቤላ ሲዳማ አፋር ወዘተ ሳይል የወያኔ የጥቃት ሰለባ ሆኗል እየሆነም ነው፡፡ በአንጻሩ “ጎበዝ ምንድን ነው መላው አየያዙን አይተህ ወደሚያደላው” የሚለውን አባባል የተከተሉ ብሄራቸው ከየትም ይሁን ከየት ተጠቂ ሳይሆኑ በአጥቂነት ተሰልፈው የኢኮኖሚውም የፖለቲካውም ተጠቃሚ ሆነው ኖረዋል እየኖሩ ናቸው፡፡ በሌላም በኩል ለሰርዓቱ ድጋፍ ባይኖራቸውም፣ የሚያዩት የሚሰሙት ሁሉ የህሊና እረፍት ቢነሳቸውም በተለያየ ምክንያት ለመቃወም ባለመቻል ጎመን በጤና ብለው ሆነው ሳይሆን መስለው የሚኖሩት እጅግ በርካታ ቁጥር የሚይዙት ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚ ባይሆኑም ሥርዓቱን ባይፈልጉትም ቀጥተኛ ጥቃት ሳይደርስባቸው በደል ሳይፈጸምባቸው እየኖሩ ስለመሆኑ አሌ የሚል ካለ አይኔን ግንባር ያድርገው የሚል ብቻ መሆን አለበት፡፡ ስለሆነም የወያኔ ጥቃት በዘር ማንነት ላይ ሳይሆን በአመለካከት ላይ የተመሰረተ ነውና መፍትሄውም በዘር ሳይለያዩ የቋንቋ ገድብ ሳይፈጥሩ በሀይማኖት ሳይራራቁ በደል በቃን ነጻነት እንሻለን የሚሉ ወገኖች ሁሉ በአንድ ተሰልፈው መታገል ነው፡፡ ስለሆነም እገሌ የሚባለውን የህብረተሰብ ክፍል ወይንም ሕዝብ እንወክላለን በማለት ድርጅት መስርተው ያለ ውጤት አመታት ያስቆጠሩትም ሆኑ ከእነርሱ ባለመማር በዘር መደራጀትን እንደ አዲስ የተያያዙት ወገኖች ወያኔ ሲያጠቃ የኖረውና አሁንም እያጠቃ ያለው ለሥልጣኔ ያሰጋኛል ያለውን ማናቸውንም ኢትዮጵያዊ ዘር ቋንቋ ሀይማኖት ሳይለይ ነውና የእኔ የሚሉት ወገን ብቻ የተጠቃ አድርገው የሚነዙትንና በወያኔ የጠላውንና ወያኔም (በእምነት ሳይሆን ለማስቀየሻ ስልት) እየተወው የመጣውን የዘረኝነት መርዝ መርጨት አቁመው ሲሆን በኢትዮጵያዊነት ቢደራጁ፣ አረ ምን ሲደረግ ካሉም በመሰላቸው ስምና መንገድ ይደራጁ ዘረኝነቱን ግን ይተውት፤የጎንዮሽ ንትርኩን ያቁሙት፤ እኔ ብቻ ትክክል የሚለውን ግራና ቀኝ ማየት የማያስችል ግርዶሽ ያስወግዱት፡፡ (በነገራችን ላይ ወያኔ ብዙ ነገሮችን ቀስ በቀስ እያለማመድ ወደ እሱ መስመር አስገብቶናል፡፡ የቀበሌውም ነዋሬ የዞኑም የወረዳውም የክልሉም ሕዝብ ይባላል፣ የወለጋ ሕዝብ የኦሮሞ ሕዘብ የጎንደር ሕዝብ የአማራ ሕዘብ የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ አጀኢብ ነው፤ የሚከተል አንጂ የሚያርም የለም) ህብረተሰቡን የሚያሳምኑበት ዓላማና የሚታመን የመታገያ አጀንዳም ሆነ የሚሉትን ሆነው ለመገኘት የሚያበቃ የተግባር እንቅስቃሴ የሌላቸው፣ ለህዝብ የሥልጣን ባለቤትነት መብቃትና ለሀገራዊ ዴሞክራሲ እውን መሆን ሳይሆን ለግል የሥልጣን ፍላጎት የቆሙና በአጭር መንገድ ቤተ መንግሥት ራሳቸውን ለማየት የሚያልሙ ወገኖች የሚታያቸው የጎሰኝነቱ መንገድ ነው፡፡ ለዚህ ምሳሌያቸው ደግሞ ወያኔ ነው፡፡ ነገር ግን ኦነግንም ማየት ቢችሉ አስተሳሰባቸውን ሚዛናዊ ለማድረግ ያስችላቸው ነበር፡፡ በአንድ ወገን እይታ ብቻ ውሳኔ ላይ አይደረስም፡፡ ዘረኝነት አንዴ ከገቡበት በቀላሉ ሊወጡት የማይችሉት አረንቋ ነው፡፡ በጎሳ ተደራጅተን ለሥልጣን ሰንበቃ ኢትዮጵያዊነትን እንላበሳለን ማለት ዘበት ነው፡፡ ለአንዳንዶቹ ኢትዮጵያዊነትን አውልቀው ጥለው ጎሰኝነትን ለመላበስ እንደቀለላቸው ከጎሰኝነት ወደ ኢትዮጵያዊነት መምጣት ቀላል ሊሆን አይችልም፡፡ ሰፊን ነገር ማጥበብ ይቻላል ጠባብን ነገር ለማስፋት ግን አይቻልም ከተቻለም ብዙ አድክሞ ነው፡፡ ገና ለሥልጣን ሳይበቁ በእጃቸውም በደጃቸውም ምንም በሌለበት ዘረኝነት እንዲህ የሚያናግራቸው ለቤተ መንግሥት ቢበቁና ማጥቂያውም(ጦሩ) ማውሪያውም (ሚዲያው) ስኳሩም (ኢኮኖሚው) በእጃቸውና በደጃቸው ቢሆን ወደ ኢትዮጵያዊነት መመለስ አይደለም ምን ሊሆኑና ሊያደርጉ አንደሚችሉ ለመገመት ነብይነት ወይንም ጠንቋይ መቀለብ አይጠይቅም፡፡ ስለሆነም ከአራባ አመታት በላይ ጎሰኝነትን ያቀነቀኑ አንዳልጠቀመ ተረድተው ከዛ ለመውጣት እየታተሩ ባለበት ወቅት ዛሬ በድንገት ተፈጥረው ከእኔ ዘር በስተቀር ለማለት የበቁትና ሀገራዊ ድርጅቶች ላይ የሚንጠላጠሉት የውልደታቸው የትነትና የእድገታቸው እንዴትነት ያልታወቀው ዘረኞች በዘረኝነቱ አረንቋ ውስጥ እሰከ አንገታቸው ከመዘፈቃቸው በፊት ሰከን ብለው፣ አደብ ገዝተው፣ ፊትና ኋላቸውን ቢያዩ ግራና ቀኛቸውን ቢመረምሩ የሚበጃቸው ይመስለኛል፡፡ መሬት ላይ ያለውን እውነት እንዳያመለከቱ፣ በቀናነት የሚነገራቸውንም በጥሞና እንዳያዳምጡ ያገዳቸውን የዘረኝነት ግርዶሽ ከፊታቸው በመግፈፍና መደራጀት መብታችን ነው ከሚለው ደረቅ ሙግት በመውጣት ትናንትን አስታውሰው ዛሬን ተገንዝበው ነገን በመተንበይ የመደራጀት መብታቸውን ከዘረኝነት አስተሳሰብ የጸዳ፣በግል የሥልጣን ጥም ያልተሸበበ፣ ከራስ በላይ ሀገርና ሕዝብ በሚል ቅዱስ አስተሳሰብ የተቃኘ ቢያደርጉት ዛሬም ግዜው አላቸው፡፡ እነርሱ የመደራጀት መብት አለን እንደሚሉት ሁሉ እንወክልሀለን የሚሉት ግን ውክልናውን ያልሰጣቸው ወገንም ከመጠየቅ እስከመቃወም መብት እንዳለው እነርሱም ጥያቄውን የመመለስ ተቃውሞውን የማስተናገድ ግዴታ እንዳለባቸው መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡ የመደራጀት መብት አለን ከሚል ደረቅ ሙግትና በኢትዮጵያዊነት ተደራጅተውና ሀገራዊ ዓላማ ሰንቀው የአቅማቸውን በተግባር እየሰሩ ያሉትን በጠላትንት ከማየት መላቀቅ የሚቻለው መጀመሪያ ከዘረኝነት ልክፍት ሲጸዱና ጭምብሉን አውልቀው መጣል ሲችሉ ነው፡፡ ያኔ ሆኖ መገኘት ቢያቅት እንቅፋት ከመሆን መታቀብ ይመጣል፡፡ ሀገራዊ አስተሳሰብ መያዝ ቢገድ ኢትዮጵያዊነትን ከማጥላላት መቆጠብ ይኖራል፣ መደገፍ ባይቻል ማደናቀፍ ይቀራል፡፡ ምን አልባት ይህ የቅዱስ መጽኃፍ ቃል ምክር ይሰጥ ይሆን፡፡ የሐዋርያው የጳውሎስ መልእክት ወደ ሮሜ ሰዎች መ/Ú፬ ቁÚ፫ እንግዲህ ከዛሬ ጀምሮ ርስ በርሳችን አንፈራረድ፣ይልቁን ግን ለወንድም እንቅፋትን ወይንም ማሰናከያን ማንም እንዳያኖርበት ይህን ቁረጡ፤ – See more at:

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop