August 17, 2013
4 mins read

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በኦስሎ ኖርዌይ ተካሄደ

6404

Friday, August 16, 2013

በዛሬው እለት Aug 16.2013   በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ በኖርዌይ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ፊት ለፊት  የኢትዮጵያ ስደተኛ ማህበር በጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ሲቪክ ማህበረሰብ የተገኙ ሲሆን በዝግጅቱም ላይ  ከየድርጅቶቻቸው ተወክለው የተገኞት ተወካዮቻቸውም ንግግር አድርገዋል ።

የሰላማዊው ሰልፎ ዋና አላማ  ሃገራችንን ኢትዮጵያ ለሐሃያ ሁለት አመታት በዘረኛውና ከፋፋዮ ወያኔ ገዢ መንግስት ያደረሰባትን የዘር ማጥፋት፣ ከትውልድ ቄያቸው በግዳጅ ማፈናቀል ፣የሐይማኖት ነጻነት አለመኖር ህዝቦቿም ወደ ማይወጡት ችግር ውስጥ በማስገባት ለስደትና ለመከራ በመዳረግ ከዛም አልፎ ተርፎ በቅርቡ በሙስሊም ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻች ላይ እያደረሰ ያለውን ጭፍጨፋና ግድያ እንዴሁም በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ላይ የሚያደርሰውን እስር፤ ድብደባ ፤ እንግልት በመቃወምና  የኖርዌ መንግስት ከአምባ ገነኑ የወያኔ መንግስት ጋር የምታደርገውን  ግኑኝነትና የምትሰጠውን እርዳታ እንድትመረምር  የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር።

በፕሮግራሞ ላይም ከኖርዌይ ፖለቲከኞች የተለያዩ ፓርቲዎች ተጋበዥ ሲሆን ሓገራቸው በአሁን ሰአት የምርጫ ጊዜ ስለሆነ ጥቂቶቹ ሊገኙ ስላልቻሉ በቴሎፎን ድጋፋቸውን ገልጸዋል  ከመሐከላቸውም  ከቬንስትረ ፓርቲ ወኪላቸውን በመላክ በኢትዮጵያ መንግስት ያላቸውን ተቃውሞና ለሰላማዊ ሰልፈኛው ድጋፋቸውን  በላኩት መልእክተኛ አስነብበዋል በመጨረሻም ከዲቬሎፕመት ፈንድ ተወካይ የመጣው ባለስልጣን አጠር ያለ ንግግር ካደረጉ በኋላ መልእክታችንን ተቀብለዋል።

በመዝጊያውም  የተለያዩ መፈክሮች ከተሰሙ በኋላ ሰላማዊ ሰልፉ እንደ ሐገራችን  መንግስት ሰላማዊ ሰልፈኛውን በድብደባና የገባበት ገብቶ ለመያዝ በማሳዳድ  ሳይሆን በዲሞክራሲ መብታችን የፈለግነውን ተናግረንና ተቃውመን በሰላም ተጠናቋል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይም ከተሰሙት መፈክሮች በጥቂቱ,TPLF is evil, There is apartheid in Ethiopia, Don’t remove indigenous people from their livelihood, We need freedom of religion., Regime change is needed in Ethiopia now, We need freedom of speech, ድምጻችን ይሰማ እኛ ሙስሊም ክሪስቲያን ኢትዮጵያኑች አንድ ነን አንለያይም , ሞት ለወያኔ  በሚሉ መፈክሮች ያሸበረቀና ሌሎችንም መፈክሮች ያካተተ ነበር። ሰላማዊ ሰልፉም በኖርዌ ሰአት አቆጣጠር ከቀኑ kl 13; 00 ተጀምሮ በ 14፡30 ተጠናቋል ቸር ያሰማን

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ተከብራ ትኑር

 

እስክንድር አሰፋ

 

ከኖርዌይ
16.08.2013

2 Comments

  1. Down! Down! With TPLF!
    ወያኔ ይውደም!!
    ኢትዮጵያ አገሬን የደፈረ ይውደም።
    ኢትዮጵያ አገሬን ያስደፈረ ይውደም።
    አሜን!!

  2. Ere selam ennifter sewoch, ahun eko tiru new yallenew. Limatum eyetefatene new kedar eskedar, alfo alfo tikakin chiggiroch besteker. Ebakachun telat aysakibin biyans yetejemerew yelimat guzo yitenakek!?!?!

Comments are closed.

Germany Demon
Previous Story

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ ተካሄደ

meseret defar 2
Next Story

Sport: ኢትዮጵያ ዛሬ በሜዳሊያዎች ተንበሸበሸች

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop