July 29, 2013
3 mins read

የቅዱስ ዑራኤል ንግሥ ለ10ኛ ጊዜ በሚኒሶታ ተከበረ

5716

(ዘ-ሐበሻ) ከተመሰረተ አስረኛ ዓመቱን ያከበረው የሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ ዛሬ የቅዱስ ዑራኤልን ዓመታዊ በዓል በደመቀ ሁኔታ አከበረ። በዚህ ለ10ኛ ጊዜ በተከበረው በዓል ላይ ብጹዕ አቡነ ሳሙኤል የዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስ፣ ብጹዕ አቡነ ሳዊሮስ የሚኒሶታ፣ የሳውዝ ዳኮትና የኮሎራዶ ሃገረ ስብከት ሊቀጳጳስና፣ ሐዲስ ሐዋርያ አባ ወ/ትንሣኤ አያልነህን ጨምሮ በርከት ያሉ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም በሚኒሶታና አካባቢው የሚኖሩ ምዕመናን እና የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ተገኝተዋል። በተለይም በዛሬው ዓመታዊ ንግሥ በዓል ላይ በዋልድባ ገዳም እየደረሰ ያለው የአባቶች ስቃይ የተነሳ ሲሆን በዚህም ላይ ከፍተኛ የሆነ የአባቶች ምስክርነት ተሰምቷል። ለምዕመናኑም ግንዛቤ ተሰጥቷል።
በ4ኛው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሪዮስ የሚመራውና በሚኒሶታ የዑራኤልና ኪዳነ ምህረትን ደብሎ የያዘው ይኸው ቤተክርስቲያን ለ10ኛ ጊዜ ዑራኤልን ባነገሰበት በዓል ላይ የተገኙት አባቶች ስለሰላም፣ ስለቤተክርስቲያን አንድነትና በተለይም ኢትዮጵያ ውስጥ በየገዳማቱ በአባቶች ላይ እየደረሰ ያለውንና በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ላይ ስውር እጆች እያደረሱ ያሉት ጥፋቶች ሁሉ ለምዕመናኑ ተገልጿል።
የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ገብረሚካኤል ተሰማ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት ነሐሴ 1 (ኦገስት 7) ቀን የሚገባውን የፍስለታ ጾም በማስመልከት በየቀኑ በቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ ቅዳሴ እንደሚኖር ገልጸው ም ዕመናኑ በቅዳሴው ላይ እንዲገኝ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ለፍልሰታ ጾም ፍቺም የኪዳነ ምህረት ዓመታዊ ክብረ በዓል በዚሁ ቤተክርስቲያን እንደሚደረግ አስተዳዳሪው ጨምረው ገልጸዋል።
የዛሬውን በዓል በከፊል የሚያሳይ ቪድዮ ደርሶናል – ተመልከቱት።

moral choices1
Previous Story

Health: ፖርኖግራፊ – (ወሲባዊ ምስሎችንና ፊልሞችን የማየት ሱስ)

Pen 4
Next Story

ሰላማዊ ሠልፍን እንደ ትግል ስልት – በ ሰለሞን ጎሹ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop