ልትወልድ ሆስፒታል የገባችዋን እናት በህክምና ስህተት ገድለዋል የተባሉት ዶክተር ተከሰሱ

/

(ብስራት ኤፍ ኤም 101.1) የ50 አመቱ ዶ/ር ተስፋዬ ኃ/ስላሴ ሀምሌ 28 2006 ዓ.ም የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ወ/ሮ ሀይማኖት ሲሳይ ማዋለጃ ክፍል ውስጥ በማስገባትና የምጥ ማማጫ መድሀኒት በመስጠት በቀዶ ጥገና ወንድ ልጅ ካዋለዳት በኋላ ማህጸኗን ሲሰፋ ስፌቱ እንዳይለቅ አድርጎ በጥንቃቄ መስፋት ሲገባው ጥንቃቄ ሳያደርግ በቀዶ ጥገና የተደረገው ስፌት በመላቀቁ ብዛት ያለው ደም ፈሷት በዚህ ምክንያት በመጣ የደም ዝውውር እጥረት ተከስቶባት ወደ ሌላ ሆስፒታል ሪፈር ተብላ ውስጥ ገብታ እያለ ህይወቷ ያለፈ በመሆኑ አቃቤ ህግ በቸልተኝነት ሰው መግደል ወንጀል ከስሼዋለሁ ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የምግብ፣ የመድሀኒትና የጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን ስር የተቋቋመው የጤና ሙያ ስነምግባር ኮሚቴ ሀኪሙ ከፍተኛ የሙያ ግድፈት ፈፅሟል በሚል ለ1 አመት በሙያው እንዳይሰራ አግዶት ነበር፡፡

ዶ/ሩ ለኮሚቴው እንደተናገሩት ጽንሱ 41 ሳምንት ከ1 ቀን ስለሆነው ባለቤቷን አስፈቅደው ቀዶ ጥገና እንዳደረጉ፤ 3.8 ኪሎ የሆነ ወንድ ልጅም እንደተወለደ፤ የእንግዴ ልጁ ወደ 3/4ኛ ክፍሉ ከማህጸን ግርግዳ ተላቆ በርካታ የረጋ ደም በመከማቸቱ ምክንያት የማህጸን መኮማተር እንዳጋጠመና ህክምና ሲደረግላት ቆይቶ ወደ ሌላ ICU ወዳለበት ሆስፒታል ስትሄድ ህይወቷ አልፏል፡፡ ስለዚህ የህክምና ስህተት አልፈጸምኩም ይላሉ፡፡ የምኒልክ ሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ በበኩሉ የስፌቱን መልቀቅ ለህይወቷ ማልፍ ምክንያት ነው ይላል፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ በ 20 ሺህ ብር ዋስ የወጡ ሲሆን አቃቤ ህግ ግለሰቡ ከሀገር እንዳይወጡ ለኢሚግሬሽንና ዜግነት መምሪያ ይታወቅልኝ ብሏል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  በየቀኑ ገላን መታጠብ የሚያስገኘው የጤና ጥቅም

1 Comment

  1. ETHIOPIAWUAN wegwnoche kemetemitem memar yikidem.’betam emiyasazinew asfekido gedela ale gin wegenoche.esua yefekedechiw le kedo hikimina engi lememot new endie adelem.’lemin tefeta endenie gin’30’amet erasu yansal.bietesebochin man yasadiglat.lebieteseboch metsinanatin emegnalehu.

Comments are closed.

Share