ESFNA 2013: የኢትዮጵያ ቀን በሜሪላንድ በደመቀ ስነ ሥርዓት ተከበረ

(ዘ-ሐበሻ) ከተጀመረ 6ኛ ቀኑን በያዘው የሰሜን አሜሪካ የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ የኢትዮጵያ ቀንን በደመቀ ሁኔታ በሜሪላንድ አከበረ። በሲልቨርስፑሪንግ በርድ ስታዲየም በ20-30 ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ይህን የኢትዮጵያ ቀን አድምቀውታል። በሌላ በኩል በሼህ መሀምድ አላሙዲ ስፖንሰር አድራጊነት በዲሲ እየተደረገ ያለው ስፖርት ዝግጅት በባዶ ስታዲየም መካሄዱን የቀጠለ ሲሆን በአላሙዲ ሰዎች ወጪያቸው ተችሎ ለክብር እንግድነት የመጡ ሰዎች ሳይቀሩ ወደሜሪላንድ በመምጣት ኢትዮጵያውያኑን ተቀላቅለዋል።
ከነዚህም ውስጥ የብሄራዊ ቡድናችን ተጫዋች አዳነ ግርማ የዲሲውን ዝግጅት ጥሎ ወደ ሜሪላንዱ በመምጣት ከሕዝብ ጋር የኢትዮጵያን ቀን አክብሯል።
“ይህ ሕዝብ ገንዘብ አይገዛውም” በሚል መፈክር ያሰማ ሲሆን በመሃሉም የባህል እና የዘመናዊ ሙዚቃዎች በስታዲየሙ የሚገኘውን ሕዝብ አስናንቶታል።
ተጨማሪ መረጃ ይዘን እስከምንመለስ ፎቶዎችን እና ጥቂት ቪድዮዎችን እናቃምሳችሁ፦

http://www.youtube.com/watch?v=8tEAjPJhc6g

http://www.youtube.com/watch?v=b48TWiumJAE

http://www.youtube.com/watch?v=aDMweIj9LrQ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የራያ ተወላጆችና ወዳጆች ማህበር የተሰጠ መግለጫ

1 Comment

Comments are closed.

Share