Health: ስንፈተ-ወሲብ መንስኤዎቹን እንዴት መለየት ይቻላል?

ስንፈተ-ወሲብ ማለት የወንዱ ብልት ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀት (መቆም) አለመቻል ሲሆን ግንኙነት ከተጀመረ በኃላም ቶሎ ጥንካሬውን በማጣት ከግንኙነት በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ማለት ነው፡፡
ስንፈተ-ወሲብ ማለት የወንዱ ብልት ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀት (መቆም) አለመቻል ሲሆን ግንኙነት ከተጀመረ በኃላም ቶሎ ጥንካሬውን በማጣት ከግንኙነት በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ማለት ነው፡፡

(ስንፈተ-ወሲብ) – ስንፈተ-ወሲብ ማለት የወንዱ ብልት ግንኙነት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ መዘጋጀት (መቆም) አለመቻል ሲሆን ግንኙነት ከተጀመረ በኃላም ቶሎ ጥንካሬውን በማጣት ከግንኙነት በፊት ወደነበረው ሁኔታ መመለስ ማለት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ምን ያህል ወንዶች የችግሩ ሰለባ ናቸው የሚለውን ለማወቅ የሚያስችሉ ጥናቶች ባይደረጉም በአሜሪካ ብቻ ከ15-30 ሚሊዮን የሚደርሱ ወንዶች ለስንፈተ ወሲብ ተዳርገዋል። በዚህም ምክንያት ብዙ ወንዶች ለስነልቦና ችግሮች ተጋልጠዋል ብዙ ትዳሮችም የመፍረስ ዕድል አጋጥሟቸዋል፡፡ የወንድ ልጅ ብልት ለግንኙነት ዝግጅ እንዲሆን የተለያዩ ወሲብ ቀስቃሽ ከሆኑ ነገሮች ጋር በተያያዘ ከአንጎላችን ወደ ነርቮቻችን መልዕክት ይተላለፋል በዚህም ምክንያት በብልት ውስጥ የሚገኙ የደም ስሮች ይለጠጡና ደም ወደ ብልት ይገባል ከገባም በኃላ እስፖንጅ መሳይ ክፍሎች ደሙን መጥጠው በመያዝ ለወሲብ ዝግጅ እንዲሆንና በግንኙነት ወቅትም ተገቢው እርካታ ደረጃ ላይ እስኪደርስ ጥንካሬውን እንዲጠብቅ ያስችሉታል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ቴስተስትሮን/ Testosterone የተባለው ሆርሞን በሰውነታችን ውስጥ በተገቢው መጠን መኖሩ ለሂደቱ ጠቃሚ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ነገር ግን እነዚህ ከላይ ያየናቸው ጤናማ ተፈጥሮአዊ ስርዓቶች በተለያዩ ምክንያቶች ሊስተጓጎሉ ይችላሉ በዚህም ምክንያት ስንፈተ ወሲብ ሊከሰት ይችላል፡፡

ስንፈተ ወሲብና መንስኤዎቹ

– የልብና ከልብ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ህመሞችና የስኳር በሽታ ችግሩን ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ ከእነዚህ የጤና ችግሮች ጋር በተያያዘ በተለይም ከስኳር በሽታ ጋር በተያያዘ በሰውነታችን የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ደምን የሚያስተላልፉ የደም ስሮ ለከፍተኛ ጉዳት ይጋለጣሉ በዚህም ጤናማ የሆነ የደም ዝውውር ይስተጓጎልና ችግሩ ይከሰታል፡፡ አንዳንድ የምርምር ውጤቶችን እንደሚያሳዩት ከ35-50 ፐርሰንት የሚሆኑት የስኳር ህመምተኞች ለዚህ ችግር የመጋለጥ ዕድላቸው ሰፊ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የጥርስ ህመምና መዘዙ

Testosterone “ቴስተስትሮን” የተባለው ሆርሞን እጥረት በሰውነታችን ውስጥ ካለ ለወሲብ ያለን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ሊቀንስና አንዳንድ ጊዜ ለስንፈተ ወሲብ ሊያጋልጠን ይችላል፡፡

ለተለያዩ ህመሞች ህክምና ተብለው የሚወሰዱ አንዳንድ መድኃኒቶች ከሚያስከትሉት የተለያዩ የጎንዮሽ ጉዳቶችም ውስጥ ስንፈተ ወሲብ ይገኝበታል በእነዚህ መድኃኒቶች እስከ 25 በመቶ ለሚሆነው ስንፈተ ወሲብ መከሰት ምክንያት ናቸው፡፡

ከ10-20 በመቶ የሚሆኑት መንስኤዎች ደግሞ ስነ ልቦናዊ ችግሮች ናቸው። ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ ጭንቀት፣ ለራሳችን ያለን ዝቅተኛ አመለካከት ምክንያታዊ ያልሆነ የጥፋተኝነት ስሜት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ያለን ጤናማ ያልሆነ ግንኙነት፣ ወሲብን እንደአስፈሪ ነገር አድርጎ መቅረፅ የመሳሰሉት ይገኝለታል፡፡

በአንጎልና በህብለሰረሰር እንዲሁም በተለያዩ የደም አስተላላፊ ቧንቧዎችና የደምስሮች ላይ የሚከሰቱ አደጋዎች ለችግሩ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

የተለያዩ ጎጂ ሱሶች ችግሩን ያስከትላሉ ከእነዚህም ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ሲጋራን ማጨስ የደም ስሮችን እንዲጠቡ በማድረግ ጤናማ የሆነውን የደም ፍሰት በማስተጓጎል ስንፈተ ወሲብን ሊያመጣ እንደሚችል እንዲሁም አልኮልን አብዝቶ መጠጣት በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ቴስተስትሮን/Testosterone/ የተባለውን ሆርሞን ምርት በመቀነስ ለወሲብ ያለን ፍላጎት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖችን ያስከትላል፡፡

የፕሮስቴትና የፊኛ ካንሰር ቀዶ ጥገናዎችና እንዲሁም በፈንጢጣና ብልት አካባቢ የሚደረጉ ቀዶጥገናዎች የተለያዩ ነርቮችን ሊጎዱ ስለሚችሉ አልፎ አልፎ ለችግሩ ሲያጋልጡ ይስተዋላሉ፡፡

የኩላሊት ህመም

ደካማ የሆነ የጤናና የአመጋገብ ሁኔታ

ከልክ ያለፈ የሰውነት ክብደት

ከማንኛውም ጎጂ ሱሶች ራሳችንን መጠበቁ ችግሩ ሳይመጣ ለመከላከል ይረዳናል ሲጋራ፣ አልኮል፣ ጫት የመሳሰሉትን ጎጂ ነገሮች የምንጠቀም ከሆነ እነዚህን ነገሮች ማቆም ያኖርብናል። – አንዳንድ ጥናቶች ስንፈተ ወሲብ ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዞ ሊመጣ እንደሚችል ያሳያሉ፡፡ 5 በመቶ በሚሆኑት ዕድሜያቸው በ40ዎቹ ክልል ውስጥ በሚገኝና ከ15-25 ፐርሰንት በሚሆኑ ዕድሜያቸው ከ65 ዓመት በላይ በሆናቸው ሰዎች ላይ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ በተጨማሪም በ2002 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በየቀኑ ለረዥም ሰዓታት ብስክሌት መንዳት የተለያዩ ነርቮች ላይ ጉዳት በማድረስ የችግሩ መንስኤ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ኃያላንን ለመማረክ ኃያልነትህን ደብቅ - Don't outshine your master

መንስኤዎቹን እንዴት መለየት ይችላል?

– የስንፈተ ወሲብን መንስኤዎች ለማጠራት የሚደረጉ የተለያዩ አይነት ምርመራዎች አሉ ከእዚህም መካከል የሰውየውን ያለፈ የጤናና የወሲብ ታሪኩን ጠይቆ በመረዳት እንዲሁም ይህ ሰው ከዚህ በፊት ምን ዓይነት የጤና ችግር እንደነበረበትና ለእነዚህም ችግሮች ህክምና ምን አይነት መድኃኒቶችን እንደተጠቀመ ወይም እየተጠቀመ እንዳለ ለይቶ በማውጣት ችግሩ በመድኃኒት ወይም በሌላ ምክንያት እንደተከሰተ ለይቶ ማወቅ ይችላል፡፡ – አካላዊ ምርመራ በማድረግ ከእነዚህም ውስጥ የሰውየውን የደም ግፊትና የልብ ምት መጠንን በመለካት ትክክለኛ የሆነ የደም ስርጭትና ዝውውር መኖሩን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ እንዲሁም ሰውየው ብልቱ አካባቢ በሚነካበት ወቅት ምንም አይነት ስሜት የማይሰማው ከሆነ መንስኤው ከነርቭ ጋር የተያያዘ እንደሆነ በቀላሉ ለመረዳት ያስችላል፡፡ – በላቦራቶሪ በሚደረጉ ምርመራዎች “ቴስተስትሮን” የተባለውን ሆርሞን በሰውነት ውስጥ ያለውን መጠን በመለካት ለችግሩ መንስኤ መሆን አለመሆኑን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ – ለችግሩ ሰላባዎች የተለያዩ ስነልቦናዊ ምርመራዎችን ማድረግ

ስንፈተ ወሲብና ህክምናዎቹ

ለስንፈተ ወሲብ የሚሰጡ ህክምናዎች እንደየመንስኤያቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ የህክምና ባለሙያዎች እንደሚገልፁት የችግሩ መንስኤ የሆኑትን ነገሮች መለየትና እነዚህንም መንስኤዎች መቆጣጠር መቻል ከፍተኛ ለውጥ እንደሚያመጣ ይጠቁማሉ፡፡ 1. ከማንኛውም ጎጂ ሱሶች ራሳችንን መጠበቁ ችግሩ ሳይመጣ ለመከላከል ይረዳናል ሲጋራ፣ አልኮል፣ ጫት የመሳሰሉትን ጎጂ ነገሮች የምንጠቀም ከሆነ እነዚህን ነገሮች ማቆም ያኖርብናል። 2. ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ በጤና ባለሙያ በመታገዝ የአመጋገብ ስርዓትን መለወጥ አስፈላጊ ነው ለምሳሌ ከፍተኛ የሆነ ጨውና ጣፋጭ የበዛባቸውን ምግቦች መቀነስ እንዲሁም ፍራፍሬና አትክልቶችን አዘውትሮ በመመገብ ጤናማ የሰውነት ክብደት ክልል ውስጥ መግባት ይቻላል፡፡ የተለያዩ እስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ላይ መሳተፍም ያስፈልጋል፡፡ 3. የችግሩ መንስኤ ሊሆኑ የሚችሉትን የስኳርንና የደም ግፊትን ህመም ከጤና ባለሙያ ጋር በመመካከር በሚገባ መቆጣጠርና የሚታዘዙልንን መድኃኒቶች በአግባቡ መውሰድ ይኖርብናል። 4. በተለያዩ በሽታዎች ህክምና የምንወስዳቸው መድኃኒቶች ካሉ እነዚህን መድኃኒቶች ለጤና ባለሙያ በማሳየት የችግሩ መንስኤ መሆናቸውንና አለመሆናቸውን ማጣራት ይገባናል 5. መንስኤው ስነ ልቦናዊ ችግሮች መሆናቸው ከተረጋገጠ የሥነ-ልቦና ባለሙያዎችን ማማከርና ምክሩንም ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይገባናል፡፡ ከፍቅር አጋራችን ጋር ግልፅ የሆኑ ውይይት ማድረግ፣ ለራሳችን ያለንን ዝቅተኛ አመለካከት ማስተካከል፣ ጭንቀትን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ እነዚህ ከላይ ያየናቸው ህክምናዎች ማንኛውም የችግሩ ሰለባ ተግባራዊ ሊያደርጋቸው የሚችሉና በቀላሉ ከፍተኛ ለውጥ ሊያስገኙ የሚችሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የችግሩ መጠን ከፍ ሲል የተለያዩ መድኃኒቶችን መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ችግሩ የተከሰተው ቴስተስትሮን በተባለው ሆርሞን ማነስ ምክንያት ከሆነ ይህ ሆርሞን መጠኑ እንዲስተካከል በጤና ባለሙያ የሚታዘዙ መድሐኒቶችን መጠቀሙ መፍትሔ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ባሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ በገበያ ውስጥ ተሰራጭተው በጥቅም ላይ እየዋሉ የሚገኙት መድሐኒቶች sildenafil (viagra), Verdanafil & Taldanafil የተባሉት መድኃኒቶች ሲሆኑ እነዚህም በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የጠበቡትን የደም ስሮች እንዲለጠጡ (እንዲሰፋ) በማድረግና የደም ዝውውርን በማስተካከል ለችግሩ ከፍተኛ መፍትሔ ይሰጣሉ፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች ተገቢው የጤና ምርመራ ከተደረገ በኃላ በጤና ባለሙያ የሚታዘዙ ሲሆኑ ባአሁኑ ወቅት ግን የችግሩ ሰለባዎች ያለህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ እነዚህን መድኃኒቶች ገዝተው ሲጠቀሙ ይስተዋላል ይህም ለከፋ የጤና ችግር ሊዳረግ ይችላል። ምክንያቱም እነዚህ መድኃኒቶች እንደማንኛውም መድኃኒት የራሳቸው የሆነ የጎንዬሽ ጉዳት አላቸው። ከእነዚህም ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የራስ ምታት፣ የምግብ ያለመፈጨትና የሆድ ህመም፣ የእይታ ችግር በተለይም ብርሃንን ለመለየት መቸገርና ቀለሞችን ያለመለየት እና የመሳሰሉትን ጊዜያዊ ችግሮች ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም እነዚህ መድኃኒቶች ከተለያዩ መድኃኒቶች ጋር በተለያየ ለልብ ህመምና የደም ግፊትን ለማስከተል ከሚወሰዱ አንዳንድ መድኃኒቶች ጋር ስለሚጋጩ እነዚህን መድኃኒቶች ያለህክምና ባለሙያ ትዕዛዝ ገዝቶ መጠቀም ለጉዳት ሊያጋልጠን ይችላል፡፡ ከላይ ካየናቸው መድኃኒቶች በተጨማሪ በበለፀጉት ሀገራት በወንዱ ብልት ላይ በቀጥታ በመርፌ የሚወጉ እንዲሁም አልፕሮስታዲል (Alprostadil) የተባለ ንጥረ ነገር የያዙ በቅባት መልክ የተዘጋጁ መድኃኒቶች፤ የተለያዩ የሚነፉ እስፕሬዎች በጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ በቀዶ ጥገና አማካኝነት የሚቀበሩና የተስተካከለ የደም ፍሰት በመፍጠር ብልት ለወሲብ እንዲዘጋጅ የሚረዱ መሳሪያዎችንም በስፋት ወደገበያ እየገቡ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  Health: ገንዘብህ ያገልግልህ እንጂ አታገልግለው

 

Source: Farmanet Magazine

Share