በሚኒሶታው መድኃኔዓለም ቤ/ክ ስም መነገድ ይቁም!!! [አቡነ ማርቆስ ቤ/ክርስቲያኑንን አሳማ ያርቡበት ያሉበት አነጋጋሪ ቪዲዮ]

በቀጣይ ያስተናገድንላችሁ መልዕክት ለሰላም እና ለአንድነት ከቆሙ የሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምዕመናን የተላለፈውን ጥሪ ነው።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
5/3/2014

የቤተክርስቲያናችንን አንድነትና ሰላም ለመናድ እየተንቀሳቀሰ ያለው ቡድን በታላቁ ደብራችን በደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ስም የሐሰት ዘመቻ እያደረገ ስለሚገኝ የቤተክርስቲያናችን አባላትና ሌላውም ኃይማኖቱንና አገሩን የሚወድ ሁሉ እየተነዛ ካለው የሐሰት ቅስቀሳና አሉባልታ እራሱን እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

የቤተክርስቲያናችን የሚኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የገለልተኝነት አቋም አሁንም ያልተቀየረና የተጠበቀ ሲሆን በቅርቡ የዚሁ የሰላምና አንድነት አፍራሽ ቡድን ዋነኛ አንቀሳቃሽ ከሆኑት ግለሰቦች መካከል አንዱ ወደ ኢትዮጵያ በመሔድ ሥልጣን ላይ ባለው ኃይል 6ኛ ፓትርያርክ ተብለው ለተቀመጡት አባት ሜኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አዲስ አበባ ባለው ሲኖዶስ ሥር ለመተዳደር ወስኗል በማለት የተሰራጨው የድምጽና የቪድዮ መልእክት ፍጹም ከእውነት የራቀ እንደሆነ ሁሉም እንዲያውቀው እንወዳለን።

ሰላምና አንድነትን አሻፈረኝ በማለት የቤተክርስቲያኑ አባላት ተሰብስበው የመጨረሻ ውሳኔ እንዳያስተላልፉ መሰናክሎችን ሲፈጥር የነበረው የዚህን ቡድን ሕገወጥ አካሔ በፍርድ ቤት አስገዳጅነት የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ለሜይ 11 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲካሔ ከተወሰነ በኋል የሚያደርጋቸውን ሕገወጥ
አካሒዶች መቀጠል ስላልቻለና በጉባኤውም ተሸናፊነቱን አስቀድሞ በማወቁ ራሱን በእለተ ሆሳዕና ከቤተክርስቲያን ለይቷል። በቅርቡ ተወካዩን ወደኢትዮጵያ በመላክም ሕዝቡ ሳይወስንና ስብሰባም ሳያደርግ ሚኖሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በእናንተ አመራር ሥር ለመሆን ወስኗል
በማለት የሐሰት ወሬ ለፓትርያርክ አባ ማቲያስ የተነገረውና እርሳቸውም ያስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ቤተክርስቲያናችንን በማይወክሉ እወደድ ባዮች የተፈጸመ ማወናበድ ስለሆነ ደብራችን ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን አሁንም ሆነ ወደፊት በአባቶች መካከል ያለው መለያየት ተፈትቶ አንድ ሲኖዶስ አንድ ፓትርያርክና አንድ አመራር እስከሚፈጠር ድረስ በገላጋይነት አቋም የሚጸና መሆኑን ለአንድነትና ለሰላም የቆምን ብዙኃን የቤተክርስቲያኑ አባላት ሁሉም እንዲያውቀው በአጽንዖት እናሳስባለን።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወሳኙ የፋኖና የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል። ኅልውናን ከማዳን እስከ ሐገር ግንባታ።

ከዚህም በተጨማሪም በበራሪ ወረቀቶችና በራድዮ እንዲሁም በየዌብ ሳይቱና በፌስ ቡክ ቤተክርስቲያናችን ሰባኪያንን እና ዘማሪያንን በማስመጣት ጉባኤ ያዘጋጀ እንደሆነ ተደርጎ እየተላለፈ ያለው ቅስቀሳም ሐሰት መሆኑን እንገልጻለን። የተባለው ስብሰባ የተዘጋጀውና የሚመራውም በዚሁ ራሱን ለእምነትና ለእውነት ሳይሆን ለፖለቲካ መሳሪያነት ባዘጋጀው ቡድን ስለሆነ ምእመናን ጥሪው የቤተክርስቲያን እንዳልሆነ እንዲያውቁት እንወዳለን።

በቤተክርስቲያናችን ችግር በመፍጠር ሰላማችንን የረበሹትን የቦርድ አባላት ሽሮ በምትካቸው አዳዲስ የቦርድ አባላትን ለመምረጥ እና በዲሴምበር 15/2013 በከፍተኛ ድምጽ ቤተክርስቲያናችን ባለችበት የገለልተኛ/ገላጋይነት አቋም ትቀጥል ተብሎ የተወሰነውን ውሳኔ ለማጽደቅ ሜይ 11/2014 በሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ድምጽ መስጠት የምትችሉ የደብራችን አባላት ሁሉ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ ላለፉት ዓመታት ተከብሮ የቆየውን የእግዚአብሔርን ቤት ይኸው የሰላም እና የአንድነት አፍራሽ ቡድን የጋበዛቸው አቡነ ማርቆስ “ህንጻ” እያሉ ሲያቃልሉትና “አሳማ ያርቡበት” ያሉበትን ቪድዮ በድጋሚ ትመለከቱት ዘንድ፤ ላላዩትም ታሳዩ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። አቡነ ማርቆስ ደብረሰላምን አሳማ ማርቢያ አድርጉት ቢሉም የእግዚአብሄር ቤት የአሳማ ማርቢያ አይሆንም።

ወ ስብሐት ለእግዚአብሔር!

10 Comments

  1. This is the most unbelievable rendition of decadent state of our clergy who have indeed sold Christ again by incarnating Judah the Scarlet. I send this message from Denver as I was live witness almost 20 years ago when this man was the priest of St Mary Church for many Ethiopian faithful’s who were forcefully removed from the church they established. (Today that church is the great Dagmawit Gishen St Mary Church.) Then the victim in reverse was chased out by Woyane Cadres led by non-other than the current so called Patriarch Abune Mathias himself. It was an ironic-poetic justice when the two faced against each other in the Denver court room from the litigation that ensued by Woyane supporters in which they lost. Subsequently, on 07-15-1994 Abune Mathias citing Fetehe Menfesawi Article 5 and 6 excommunicated Aba Markos Tefera from all Church in North America. Today, he is the loyal emissary of the very man who did this to him against those whom he find unacceptable and thereby condemning the church as a “Pig Farm”. Is that right?

    It was not long after 2006 he has traveled back to Denver, this time accompanied by his new fame and title from Addis Ababa to the very same church he was shackled out. Awaiting his return, at that juncture history was made by God by constructing the largest Orthodox Church ever built outside of Ethiopia for those who stood guard for God and Country. At that time, his audiences were the same suspects along with MAHEBERE KIDUSAN who joined the chorus of thunderous applause when he began condemning the very church which be helped established, prosecuted , excommunicated for out of pure failure of the flesh. Verbatim to his present day condemnation he went one step further to call Dagmawit Gishen St Mary Church as “YETEWEGEZE BETECHRISTIAN”. How is that even possible?

    How this man can go from victim to prosecutor on behalf of the most evil collection of people known to history as “nation killer” is truly breath taking. What may be even the most profound telling is such visceral behavior of self-interest and narcissisms engulfing many of our Ethiopians are in fact directly parallel to this man’s journey as “Judha Generation” who sold out its FAITH and the NATION for chump change. Therefore, this entire sad saga is that we all need to look deep into ourselves to truly examine our own commitment to Christ and his church. The church is above any allegiance we have on this earth with anyone or for anything. Many of our fathers who have steadfastly adhered to the faith had never been without trail and tribulation. However, without a doubt they have all relied on the almighty God than fellow men and eagerly paid the needed price to ultimately pass it on to us. We have to be vigilant against the scarlet of the day and pray we shall not inherit the curse uttered “ESAT AMED YEWELDAL”

    I wish I could better write what I felt in Amharic to truly convey my sense of despair for who we have become.
    May God Save our Church!
    May God Save Ethiopia!
    Amen

  2. Eri bakachu mulu negegrachewn enyew ,achin kalat bech mertachu yemtakirbut lemdenew demo zehabesha belo mediya .

  3. በጣም የሚያሳዝነው ነገር ነው። እንዴት አንድ የሃይማኖት አባት ቤተክርስቲያንን እንዲህ ብሎ ይሳደባል? የእነዚህ አይነቱ ጳጳሳት አባትነት ባፍንጫዬ ይውጣ። ማንም ከቤተክርስቲያን በላይ የለም። ጳጳስም ቢሆን ቤተክርስቲያንን የመሳደብ ስልጣን የለውም። የሃይማኖት ችግር በሌለበት ሁኔታ ለምን ስም አትጠሩም ብሎ ይህን ያህል ማለትንስ ምን አመጣው? እነርሱ የደገፉትን ይደግፉ እኛን ግን ለምን ለቀቅ አያደርጉንም? ስም መጥራትም ካለብን የትክክለኛውን ፓትርያርክ የአቡነ መርቆርዎስን እንጂ መንግሥት ያስቀመጠውን መሆን የለበትም። አባ ማርቆስ በትክክልም ከገለልተኛው ወደዚህ አገር ሲቦዶስ ከዚህ አገር ወደ ኢትዮጵያው ሲገለባበጡ የኖሩ አስመሳይ ሆድ አደር ናቸው። የጵጵስና ክብርና ማእረግም የሚገባቸው አይደለም። ከንቱ መለፍለፍ ስለሆነ የሚሰማቸው የለም። በሥልጣንና በገንዘብ ያበዱ ሁላ ሰላማችንን ሊያደፈርሱ አይገባም።

  4. There is no lie in his ababal, truth is truth.
    it is about people not the building
    wake up geleltegna u r still sleeping in deep, and deep in sleep
    how come no body is posting the leba leba woyane , the new kidase by geleltegna and yours leader abune deresee and compare it with the one posted above.
    You forgot you are ethiopian yourself for forgetting how the ethiopians preserved this church for so far undergoing through much more that what you are chanting about in restaurants and bars. they have never chanted lebe leba leba inside and on the mercy stage whom so ever is promoting the stage. You organized damage to ethiopian church in the name of geleltegna. I dont remember other faith followers embarassing orthodox followers and their fathers in their own home of worshiping.
    This is so historic and you can’t erase it from history on how much you insulted the ethiopian orthodox church and its followers.

    And the Habesha and voice of ethiopia radio in mn are the big discriminators and self serving on own people of ethiopia You lost what is ethiopia and who is ethiopia, faith supposed to be individual, as country is common.
    Adios

  5. Abal, please add the Ethiopian Community in Minnesota to your list until they decide to correct the statements they gave regarding Medhanealem church. ECM, we have not forgotten the statements on ZeHabesha (online and on print) and KFAI.

  6. The so called Abune Marcos is the acrobatic Abune who always is behind spliting orthodox believers, see what he has done in Denver, Newyork, Houston & Austin. He preaches hate among people. He doesn’t know where he lives plus more. There will come a day and time where he again seeks a shelter outside Ethiopia

  7. በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

    እባካችሁን አባ ማርቆስና ማህበረ ቅዱሳን ይእቺን ቤተክርስቲያን ለቀቅ አድርጓት ምነው አባ ማርቆስ ቀደም ሲል በኮሎራዶ ዴንቨር ግሸን ማርያም ቤተክርስቲያን አገልጋይ በነበሩበት ጊዜ ምእመኑን በዘር በጎሳ የምትከፋፍሉ አንደበቶት በሀሰት የተሞላ አባት እንደነበሩ በደንብ እናውቃለን በወያኔ ዘንድ ይህ እኩይ ስራዎ ከትልቅ አገልግሎትተቆጥሮ የጵጵስና ማህረግ እንዲሰጦት አድርጎታል እርሶም አላሳፈሩዋቸውም ዴንቨር የሚገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያንን ለመበጥበጥ መተው እዚህ ከተማ ያለው ቤተክርስቲያን ስንት ነው ሁለት በሉ የኪዳነ ምህረትና የመድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ብቻ ነው ግሸን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አይደለም አያሉ ወንጌሉን ወደ ጎን ትተው የቻሉትን ያህል ሕዝቡን ለያየሁ ብለው ሄዱ ይሁን እንጂ ሕዝቡ የወያኔ ጳጳሳትን እንደ ንጉሳቸው እንደ ኢህአዲግ ክርስትና የሌላቸው አረመኔዎች መሆናቸውን ስለሚያውቅ የቁራ ጩኸት እድርጎ ተወው አሁን ደግሞ በሜኒሶታ ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔርን ቤተመቅደስ የአሳማ ማርቢያ እንዲሆን ሱባዬ መያዞትን ሰማሁኝ ይገርማል የማህበረ ቅዱሳን አባላት ሕዝቡ ገንዘቡን እያወጣ ክሬዲት ካርዱን እያስያዘ የሰራውን ቤተክርስቲያን ስላዩት ወይንም ስለወደዱት ብቻ እኛ ካልተረከብን ብለው በመላው ዓለም መከራ ያሳያሉ ገንዘብ አውጥተው ከሚሰሩ ይልቅ የሕዝብ ንብረት መዝረፍ ያስደስታቸዋል ምንያድርጉ እንደ እናንተ አንደበቱን ወንጌል ከመስበክ አንሰቶ ሕዝብን መለያየት ቤተክርስቲያንን የአምልኮ ቦታ ሳይሆን የንግድ ቦታ እንድትሆን የሚሰብክ ለበጎቹ ግድ የሌለው እረኛ በራሱ ሳይሆን በመሃይሞቹ ወያኔዎች ጭንቅላት የሚመራ አይምሮው በገንዘብ በተንኮል ሰውን በማምለክ የተበከለ ለዚሁ መጥፎ ተግባር በመላላክ እንዲረዳ ተብለው በተሾሙ ጳጳሳት በተለይም አባ ማርቆስን የመሰለ እኩይ አባት ይዘው እንዴት አድርገው አይምሮዋቸውን ይዘዙት እግዚአብሔር የንስሐ እድሜ ይስጦት አሜን።

  8. Abal I am very surprised by your comment for the top video. Yes he did disrespect our church also he Is “LEBA” he steal money from poor (people who were too poor to afford to eat at-list ones in a day) farmers in Gojam Reigin. What ales you want to hear about your father. Boy we Geleltena we already wake up thanks for you and your friends which trade my chruch to wiyane and steal our church at day light. Go to the hell wiyane cadres. bye WE LOVE YOU All BUT WE DON”T MISS YOU

  9. ምነው አገር ትተን ብንሰደድ ይሂ ስነምግባር የጎደለው አነጋገር በአውነት ኢትዮፕያዊ ነትን ይገልጸአል በወኑ በውነት ለሃይማኖት ተቆርቁራችው ንው አባቶች የምትሰድብት

  10. አባ መላ አብ ያልተከለው ሁሉ ይነ ቀላል ይህ አይገርምም የትንቢት መፈጸሚይ መሆናችን ይሳዝናል ከብአር ስምህ ስረዳ አባ መላ ማለት መላ የሚያፈልቅ ማለት ነው ባክህ በክርስቲያኑ አገር በጎጃም አትነግድ ያባ ኮስትር ልጆች ናቸው በምንም የማይበገሩ ክርስቲያኖች በጎጃም ትውልድ አትነግዱ ጋጃም ያበቀለው ጀግናነው አባቶችን የሚሰድብ ትውልድ አይደለም ቢበላም ባይበላም ክሩን ማተብን ያባቶቹን ክብር ለማንም አሳልፎ አይተውም ማወቅ ከፈለክ ስለ ሀገሩ ታርክ አብብ ብቻ የክርስትያን አገር ከጎጃም ነው አዳትለን ጎጃም መቸም አንተን የመሰለ አራሙቻ አይበቅልባትም የአባቱን ክብር የሚያስደፍር ዘር የላትም ባንዳ ካልሆነ በቀር
    ለማንናውም ከክርስቲያኑ ሃገር ወረድ ለአባቶቻችን ረጅም ዘመን ለናንተም የንስሃ ግዝየ ያድላችው አባመላ ግዚ የለም ለራስህ መላ ፍልግ በሰው ደም የተለወሰ አጃችሁን በንስሀ አጽዱ ግዝው ሳይደርስ: :

Comments are closed.

Share