May 2, 2014
14 mins read

የአዲስ-ኦሮምያ ጉዳይ በመቐለ-እንደርታ ዓይን – ከአብርሃ ደስታ

ስለ አዲስ አበባ ማስተር ፕላንና የኦሮምያ አርሶአደሮች መፈናቀል ጉዳይ በፃፍኩት ላይ “የኦሮሞ ተማሪዎች ዓመፅ ከብሄር አንፃር አትየው፤ መታየት ካለበት አርሶአደሮቹ ከቀያቸው ካለመፈናቀል መብት አንፃር ነው” የሚል አስተያየት ደርሶኛል። እኔም ይሄን ጉዳይ በቅርበት ከማውቀው የመቐለ እንደርታ አርሶአደሮች ልምድ አንፃር ልየው ይፈቀድልኝ።

በመቐለ የከተማ ዕድገት ፕላን መሰረት አንዳንድ በከተማው ዙርያ የሚገኙ የገጠር መንደሮች ወደ መቐለ ከተማ ይገባሉ። ይህንን ዉሳኔ ባከባቢው አርሶአደሮች ከፍተኛ ተቃውሞ አጋጥሞታል። አርሶአደሮች የተቃውሞ ሰልፍ ለማካሄድ ሞክረዋል። የክልል ፖሊስ፣ የፌደራል ፖሊስ እንዲሁም የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጣልቃ ገብተው የኃይል እርምጃ ወስደው ሰልፈኞቹን ደብድበው፣ አስረው፣ ገድለው ዓመፁ ለግዜው አስቁመውታል። ጥያቄው ግን እስካሁን ድረስ አለ። በዚህ ምክንያት ያከባቢው አርሶአደሮች የመንግስት አገልግሎት ተነፍገዋል። አርሶአደሮቹም ከመንግስት ጋር ላለመተባበር አድመዋል። ለምሳሌ የእግሪሐሪባ አርሶአደሮች ልጆች የመማር መብታቸው ተነፍጓል። የነዚህ አርሶአደሮች ልጆች ለምን እንዳይማሩ ተከለከሉ? ወላጆቻቸው መሬታቸው ወደ ከተማ መግባቱ በመቃወማቸው ምክንያት ነው። የትግራይ ክልል ባለስልጣናት “የወላጆቻቹ መሬት የከተማ እንዲሆን ካልፈቀዱ እናንተ ህፃናት እዚሁ ትምህርትቤት አትማሩም። ምክንያቱም ይሄ ትምህርትቤት የከተማ ሆኗል” አሏቸው። እናም እስካሁን ድረስ እነኚህ ልጆች የመማር መብታቸው እንደተነፈጉ ነው።

“የገጠር መሬት ወደ ከተማ ሲገባ ለምን ይህን ያህል ተቃውሞ ይነሳበታል?” የሚል ጥያቄ መነሳቱ ተገቢ ነው። ከተማ ማደግ አለበት። ከተማ ሲያድግ በዙርያው ወዳለ የገጠር መንደር ይሰፋል። ግን ለምን አርሶአደሮች አምርረው ይቃወሙታል?

(አንደኛ) አርሶአደሮች ከቀያቸው መፈናቀል አይፈልጉም። ለመሬታቸው ልዩ ፍቅር አላቸው። የያለ መፈናቀል መብትም አላቸው (በመርህ ደረጃ)። አንድን አርሶአደር ያለፍቃዱ ከቀዩ መፈናቀል የለበትም። ግን መንግስት በኃይል ያፈናቅላቸዋል። መንግስት በአንድ በኩል “አርሶአደሮች መሬት ከተሰጣቸው ሽጠው ከቀያቸው ይፈናቀላሉ፣ ስለዚህ መሬት ሊሰጣቸው አይገባም” በሚል ስሌት መሬት የመንግስት አድርጎታል። በኢትዮጵያ ታሪክ አርሶአደሮች ከቀያቸው የሚፈናቀሉ በኃይል እንጂ በፍቃዳቸው አይደለም። በዘመነ መሳፍንት ግዜ አርሶአደሮች መሬት አልባ ጭሰኛ የሆኑ በኃይል እንጂ በፍቃዳቸው አልነበረም። አሁንም በመንግስት ትእዛዝ እንጂ በፍላጎቱ ከቀዩ የሚፈናቀል የለም። ስለዚህ ተቃውሞው ከቀያቸው ላለመፈናቀል የሚያደርጉት ትግል ነው።

ግን አርሶአድሮች ከቀያቸው ያለመፈናቀል መብት ካላቸው ለምን ወደ ተቃውሞና ዓመፅ ይሄዳሉ? አርሶአደሮች መፈናቀል አይፈልጉም። መንግስት በኃይል ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ያስገድዳቸዋል። መንግስት እንዲፈናቀሉ ሲያስገድዳቸው ለምን አቤት አይሉም? አቤት ለማለት’ኮ ገለልተኛ የፍትሕ አካላት መኖር አለባቸው። የፍትሕ አካላት ሲኖሩ ደግሞ የያለመፈናቀል መብት በሕግ የተደነገገ መሆን አለበት። ከመሬት የያለመፈናቀል መብት በሕግ የተደነገገ እንዲሆን መሬት የዜጎች መሆን አለበት።

አሁን በኢህአዴግ ሕገመንግስት መሰረት ዜጎች መሬት ተከራይተው የመጠቀም መብት እንጂ የመሬት ባለቤት የመሆን መብት የላቸውም። መሬት የዜጎች ሳይሆን የመንግስት ነው። ስለዚህ ዜጎች መሬት የመከራየት (ሊዝ የመሬት ኪራይ መሆኑ ነው) መብት አላቸው። ባለቤትነቱ ግን የመንግስት ነው። ስለዚህ አንድ ተካራይ ከተከራየሁት ቤት (መሬት) መልቀቅ (መነሳት) የለብኝም ብሎ መከራከር አይችልም። ተግባሩ ግን መቃወም ይችላል።

እናም አርሶአደሮቹ ከመሬታችን አንፈናቀልም ሲሉ መሬትኮ የመንግስት እንጂ የናንተ አይደለም፤ ስለዚህ ትነሳላቹ ይሏቸዋል። አርሶአደሮቹም “መሬትኮ የመንግስት መሆን የለበትም” ሲሉ “መሬት የመንግስት ካልሆነማ መሬታችሁን ሽጣቹ መሬት አልባ ትሆናላቹ። መሬት በጥቂት ሃብታሞች እጅ ይገባል” የሚል መልስ ይሰጣቸዋል። መሬታቹ ሌሎች ሊወስዱት ስለሚችሉ ቀድመን እኛ ወስደነዋል ዓይነት ማለት ነው።

ስለዚህ አርሶአደሮቹ መሬታችን አንሰጥም ብለው በሕግ ፊት እንዳይከራከሩ ሕጉ አይደግፋቸውም። ምክንያቱም ሕጉ መሬት ለዜጎች ሳይሆን ለመንግስት ነው የሰጠው። ስለዚህ የሕግ ድጋፍ የላቸውም። የህግ ድጋፍ ባይኖራቸው እንኳ ተግባሩ ትክክል አለመሆኑ ያውቃሉ። እናም ይቃወሙታል። መቃወም ሳይፈቀድላቸው ሲቀር ያምፃሉ። ሲያምፁ በኃይል ይደፈጠጣሉ። እናም አማራጭ ስለሌላቸው አኩርፈው ይቀመጣሉ። በኦሮምያ ግን ዓመፁን አቀጣጠሉት።

ስለዚህ የችግሩ መንስኤ የመንግስት የተሳሳተ የመሬት ፖሊሲ ነው። መሬት የህዝብ (የዜጎች) ቢሆን ኑሮ አርሶአድሮች ከመሬታቸው ያለመፈናቀል መብታቸው በሕግ ይከበርላቸው ነበር (ገለልተኛ የዳኝነት ስርዓት ሲኖር ማለት ነው)። ምክንያቱም መሬት የአርሶአደሮች ከሆነ ማንም ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ አያስገድዳቸውም ነበር። መሬት ለራሹ ከተሰጠ አርሶአደሮች ያለ ፍቃዳቸው ከመሬታቸው (ከቀያቸው) አይፈናቀሉም። ካልተፈናቀሉ ደግሞ መሬታችን ወደ ከተማ ይገባል ብለው ዓመፅ አይቀሰቅሱም ነበር። ስለዚህ የችግሩ ምክንያት የመሬት ፖሊሲው ነው።

(ሁለት) አስፈላጊ ሁኖ ሲገኝ አርሶአደሮች የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል። ይሄ የሚሆነው ግን አርሶአደሮችን በማሳመን (በፍቃዳቸው) ሁኖ ለመሬታቸው ተገቢ ካሳ (ራሳቸው በጠየቁት መሰረት) ሊከፈላቸው ይገባል። በመቐለ ዙርያ ያሉ አርሶአደሮች ግን ከመሬታቸው ተፈናቅለው ሲያበቁ በቂ ካሳም አይሰጣቸውም። የካሳ መጠን የሚወስነው መንግስት ነው (ካሳ የማያገኙም አሉ)። መሬታቸው አጥተው በቂ ካሳ ካላገኙ ከዚህ የባሰ መነቀል አለንዴ? ይህ ሲሆን እንዴት አይቃወሙም? የኦሮምያ ጉዳይም ተመሳሳይ ስጋት ሊጭር ይችላል።

(ሦስት) “መሬታቹ የከተማ አካል ሁኗል” በሚል ምክንያት አርሶአድሮች ከቀያቸው ያለፍቃዳቸውና ያለ በቂ ካሳ ከተፈናቀሉ በኋላ መሬቱ በሙስና ለሙሰኞች ይቸበቸባል። መሬት የመንግስት በመሆኑ እንዲሁም መንግስትና ገዥው ፓርቲ በመቀላቀላቸው ምክንያት የገዥው ፓርቲ ጥቂት ካድሬዎች መንግስት ሁነዋልና ከአርሶአደሮች የተረከቡትን መሬት እንደፈለጉ ለፈለጉትን ባለሃብት ይሸጡታል። መሬት ከአርሶአደሮች ነጥቀው ለራሳቸው ያደርጉታል። ወይ ይሸጡታል ወይም ደግሞ ህንፃ ያቆሙለታል። መሬት አይሸጥም አይለወጥም እየተባለ የመንግስት አካላት ግን እንደፈለጉ ይሸጡታል፣ ይለውጡታል። መሬት እንዳይሸጥ እንዳይለውጥ የተከለከለ አርሶአደሮቹ እንጂ መንግስትማ የፈለገ ያደርጋል። እናም ከአርሶአደሮች የተነጠቀ መሬት ለግል ሃብታሞች እየተሸጠ እየተመለከቱ እንዴት አይቃወሙም? እንዴት ለመሬታቸው አያምፁም? በኦሮምያም በእንደርታ የተተገበረውን እንደማይደረግ ምን ማረጋገጫ አለን?
ስለዚህ የመቐለ እንደርታ አጀንዳ በመውሰድ የአዲስ አበባ ኦሮምያ ጉዳይ መገመት ይቻላል። ጉዳዩ ከመንግስት የመሬት ፖሊሲ ጋር ይገናኛል።

“የኦሮምያ ተቃውሞ ፖለቲካዊ አጀንዳ አለው” ካላችሁኝም ያው ፖለቲካዊ ተልእኮ ሊኖረው ይችላል። ፖለቲካዊ ተልእኮ ያለው ዓመፅ ሲቀሰቀስምኮ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ መሰረት አድርጎ ነው። ፖለቲካዊ ዓመፅ የሚቀሰቀሰው ጭቆና ሲኖር ነው። የፍትሕ እጦት ሲኖር ነው። የዴሞክራሲ እጦት ሲኖር ነው። ነፃነት ሲታፈን ነው። ስለዚህ ዓመፁ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለው ከሆነም ያው መንስኤው ደግሞ የኢህአዴግ ጨቋኝ አገዛዝ መሆኑ ነው። ምክንያቱም በሀገሪቱ ፍትሕ ቢሰፍን ኑሮ ዜጎች ፖለቲካዊ አጀንዳ ይዘው አያምፁም ነበርና ነው።
የፖለቲካዊ ዓመፅ መንስኤ ጭቆና ቢሆንም ዓመፅ ግን የጭቆና ነፀብራቅ እንጂ ጭቆና የሚወገድበት ትክክለኛ ስትራተጂ አይደለም። በዓመፅ ጨቋኞችን ከስልጣን ማባረር ይቻል ይሆናል። በዓመፅ ጭቆናን ማስወገድ ግን አይቻልም። ጭቆና የሚወገደው ዴሞክራሲ በማስፈን ነው። በዓመፅ የሚገነባ ዴሞክራሲ ደግሞ የለም። የዴሞክራሲ መንገድ ዴሞክራሲ ነው። ዓመፅ የሰው ህይወትና ንብረት ይበላል። በዓመፁ ምክንያት ህይወታቸው ላጡ ተማሪዎች ጥልቅ ሐዘን ይሰማኛል።

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop