September 18, 2023
1 min read

የአብይ አህመድ ግፍ: በአውራ ጎዳና መንደር ግድያ፡ ዘረፋ ተስፋፍቷል። ህዝቡ አከባቢውን ለቆ ተሰዷል

185799

https://youtu.be/su2dS0Z3_mk?si=Vw9y9wwUSUTvNEPC

https://youtu.be/RNEFNlOSl5c?si=5O4NNV0qllch_YEV

 

 

1 Comment

  1. ወይ ጉድ መቼ ነው ቆም ብለን በማሰብ ከመተኮሳችን በፊት እንዴትና ለምን ብለን የምንጠይቀው? ነው ወይስ እንደ ወያኔ ዋርድያ ተኩሶ ገድሎ ቁም ማለት ተለመደ? አፍሪቃ አሳዛኝ አህጉር ነበረች አሁንም ብሶባታል እንጂ አልተሻላትም። ለዚህም ያለ ቅጥ የሰው መብዛትና በየምክንያቱ መከፋፈል ሌሎችንም ችግሮች ተዳብለው የሚያፈልቁት የሰቆቃ ውጤት ነው። አሁን በቅርብ በወጣ ዜና ላይ በደቡብ አፍሪቃ የስደተኞች ጥላቻ ጣራ ላይ ስለወጣ ያኔ በነጩ የአፓርታይድ አገዛዝ ሃበሳቸውን ሲያዪ የነበሩ ጥቁሮች ዛሬ ጥቁር ጠል ሆነው ታጣቂ በማሰባሰብ ሰውን በማሳደድና ቤቱን በመለኮስ ላይ ይገኛሉ። በቱኒዚያ የሃገሪቱ መሪ ጥቁሮች የሃገራችን ችግር ናቸው ብለው በመናገራቸው እዚያው ተሰደው በስደትም ይሁን በሥራ የነበሩ ሁሉ ግማሹ ወደመጣበት ሲመለስ ሌላው በባህር ተንሳፎ ባህር ይበላዋል ወይም ላምፓድሳ ደሴት ላይ አርፎ የአውሮፓን በስደተኞች መጥለቅለቅ ፍራቻ ጫፍ ላይ አድርሶታል። የአውሮፓ የስደተኞች አቀባበል ፓሊሲ ተለውጧል/ይለወጣል። ጊዜው ተቀይሯል። ድሮ ሰው የፓለቲካም ሆነ የሌላ ጥገኝነት ይጠይቅ ነበር። አሁን ላይ ግን ኑሮን ለማሸነፍ የሚደረግ ስደት ስለሆነ እየተተኮሰበትም አይቆምም። ሰዓቱ መሽቷል። ሰው በምናቡ በሚያየው እንጂ በጨበጠው ነገር አይረካም።
    ትላንት ኤርትራ ለኤርትራዊያን ሲሉን የነበሩ የፓለቲካ ጀለፎዎች ዛሬ ምድሪቱ ሰው የማይኖርባት ሁሉ በየደረሰበት እግሬ አውጭኝ የሚልባት ምድር ሆናለች። ቀድመው የወጡትም ሆነ አሁን በየምክንያቱ በዓለም የተበተኑት አሁን እንሆ ተከፋፍለው ሲዋቀጡ ማየት አይ የሃበሻ ፓለቲካ ሁሌ ጡጫና ጠበንጃ ያሰኛል። ከቁራሽ የተረፈችው ኢትዮጵያም በወያኔ አጥንቷ ተግጦ ህዝቦቿ በዘርና በቋንቋ ተከፋፍለውና ደንበርና ክልል ተበጅቶላቸው ሲገድሉና ሲገዳደሉ ኖረው አሁን ይባስ ብሎ የኦሮሞው ፓለቲካ ትሻልን ትቼ ትብስን እንድንል አድርጎናል። ጎረቤት ሃገሮች በተለይም ለብዙ ሃበሾች መጠለያና ማሻገሪያ የሆነችው ሱዳን የእብድ ገላጋይ ሆነው ገብተው ለዚህም ለዚያም እሳት እያቀበሉ አሁን የምናየውን የሰዎች እልቂትና ስደት መከራና ረሃብ አስከትለዋል። ሱዳንን ለረጅም ጊዜ መከራ ውስጥ ዘፍቀዋታል። የኢትዪጵያ እድል ፈንታ ከሱዳኑ ቢከፋ እንጂ አይሻልም። መግደል መሸነፍ ነው ያለን ጠ/ሚ አሁን ላይ እናሸንፋለን ሲል መደመጡ ፓለቲካው ከመንገድ የወጣ መሆኑን ያሳያል። ወንድምና እህቱን ገድሎ፤ ሃገር አፍርሶና አፈናቅሎ ያሸነፈ የለም። እኔን የናፈቀኝ በዙሩና በጎሳው የሚያቀነቅን ሲልለት የነጭ አገልጋይ፤ ሳይሆንለት የአረብ አፍቃሪ የሚሆን ፓለቲከኛ ሳይሆን በዓለም ላይ ለተበተኑ የጥቁር ህዝቦች አንድነት የሚታገል ነው። በየትኛውም የዓለም ክፍል የቆዳ ቀለማቸው በመጥቆሩ የተነሳ ተገለው፤ ድሃ ሆነው፤ ወይም በጉልበት ሥራና በሚያስከፋ የፋብሪካ ሥራ ላይ ተጠምደው ያለ እድሜአቸው የሚሞቱ እልፎች ናቸው። በዝባዡ ነጭና አረብ ነው። ለዚያውም ሥራው ከተገኘ ነው። እንግዲህ ክፋትና ተንኮልን በመተው ብዕርና ስብዕናን ተላብሶ ዓለምን በሚያስደምም መልኩ ለጥቁር ህዝቦች እኩልነት መታገል እንጂ ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ እልፍ ዘመን በጥይት መጠዛጠዙ የህዝባችን መከራ ያራዝመዋል እንጂ መፍትሄ አያመጣም። አሁን በምንጃርና በአውራ ጎዳና እንዲሁም በተለያዪ የአማራና የኦሮሞ አልፎ ተርፎም በሱማሊያ ክልሎች የምናየው መገዳደል፤ ሰውን ማገትና ገንዘብ መጠየቅ፤ ካልሆነም መግደል የሃገሪቱን ህግ የለሽነትና የህዝባችን መከራ አጉልቶ ያሳያል። ግን በዚህም በዚያም የወሬ ቋት ሆነው የሆነውንም ያልሆነውንም እየቀጠሉ የሚያወሩን ሁሉ ለሃገሪቱ ጥቅም ሳይሆን ለራሳቸው ሽርፍራፊ ሳንቲም ለቀማ መሆኑን ልንረዳ ይገባል። ማንም ምንም የዜና አውታር ሙሉ እውነትነት የለበትም። እንደ ምዕራባዊያን ሸቀጥ ከእቃው መጠቅለያው ያምራል እንጂ። ግን የሃገራችን ገበሬ እንዳለው
    ሃሜት መወጣጫው
    መሰላል ምላሱ
    አንድ ቀን አይቀርም ወድቆ መሰበሩ ነው።
    ዛሬ በግፈኞች የሚሞተው ይሞታል ገዳይም በሌላ ገዳይ ይገደላል ሌላውን ገዳይም ሌላ ገዳይ ይገድለዋል። የአዙሪት ፓለቲካ ማለት ይህ ነው። በሰው ደምና እንባ የሚሳለቁ ሁሉ የቁም እንስሳዎች ናቸው። የአብይ አህመድና የኦሮሞ ፓለቲከኞች ፈንጠዚያም ያከትማል። የሩቅና የቅርብ ታሪክ የሚያሳየን ይህኑ እውነታ ነው። 2016 ዓ. ም ምን አሳይቶን ያልፍ ወይም እናልፍ ይሆን? ቆይቶ ማየት ነው። ጅምሩ ግን ደግ አይደለም።፡ በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Fz2WSkuaEAAhBI6
Previous Story

ለኢትዮጵያ  ሰላም፤  ዲሞክራሲ፤  አንድነትና  ልማት  ስለሚያስፈልጉ  መሠረታዊ መፍትሔዎች

185810
Next Story

ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ከሀገር ወጡ

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop