በጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት በአማራ ክልል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በሌብነት የተከሰሱት አቶ በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ ከመጀመሪያ ዙር የ14 ቀን ቀጠሮ በኋላ ዛሬ በባሕር ዳርና አካባቢዋ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ቀርቦ ተጨማሪ የ14 ቀነ ቀጠሮ በመስጠት ለየካቲት 15/2011 እንዲቀርቡ ታዘዘ:: አቶ በረከት በማረሚያ ቤቱ ኢንተርኔት የለም ሲሉ ለፍርድ ቤት ተናግረዋል::
https://www.youtube.com/watch?v=Y35YoqNn01c
የክልሉ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ከሀገር ውስጥና ከውጭ መረጃ ለመሰብሰብ ጊዜ ያስፈልገኛል ብሎ ነው ፍርድ ቤቱን ተጨማሪ ጊዜ የጠየቀው።
ተከሳሾቹ ሲመሩት በነበረው የጥረት ኮርፖሬት የተሟላ መረጃ ባለማግኘቱ የምርመራው ስራ ውስብስብ እንዳደረገበት የገለጸው ኮሚሽኑ ሲዊዘርላንድ በሚገኝ በርክሌይ ባንክ ውስጥ 90 ሚሊዮን ዶላር በግለሰብ ስም እንደተቀመጠ የገለፀው መርማሪው የወንጀል ምርመራውን የበለጠ ውስብስብ ስለሚያደርገው በትኛው ግለሰቡ ስም ገንዘብ እንደተቀመጠ አላስረዳም፡፡ ሆኖም ከጉዳዮ ጋር በተያያዘ የሚያስረዱ ሰዎች በቋሚነትና በህክምና ውጪ ሀገር ያሉ እና ተቋማቸውን የለቀቁ በመኖራቸው አድራሻቸውን የማፈላለግ ስራ ይቀረኛ ብሏል ሲል ለችሎቱ አስረድቷል::
ተከሳሾቹ ደግሞ ተጨማሪ ቀናት አያስፈልጉም የሚል የመቃወሚያ ሃሳብ አቅርበው ነበር።