Hiber Radio: በሳዑዲ አጎቴን ገድያለሁ ያለው ኢትዮጵያዊ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

August 19, 2013
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ
Hiber Radio: በሳዑዲ አጎቴን ገድያለሁ ያለው ኢትዮጵያዊ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ 1

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ነሐሴ 12 ቀን 2005 ፕሮግራም

<<…የኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው ምንስ መውጫ ቀዳዳ አላት ፓርቲዎች ምን ያስባሉ ? ሲቪክ ተቋማት ምን ያስባሉ በሚል ለምክክር የተጠራ ስብሰባ ነው። …አሁን ያለውን የሁሉንም ሀሳብ ሰብስበን ለሕዝብ የምናቀርብበት ነው። ሕዝብ እያንዳንደን ነገር ይከታተልና ከዚያ በሁዋላ አንድ አቋም ወይ አንድ የትግል ስትራቴጂ የሚነደፍበትን መድረክ እናዘጋጃለን ይሄ አይን ገላጭ ነው። የአቋም መግለጫ ባይጠበቅም…>>

ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ኢሳት የጠራውን በአገር ውስጥና በውጭ ያሉ አብዛኞቹን የዲሞክራሲ ሀይሎች ያሳተፈውን አገራዊ የውይይት መድረክ አስመልክቶ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<<…ቤሄ ሃይማኖታዊና ባህላዊ መልክ አለው።ለመሆኑ የቡሄ ሀይማኖታዊ መሰረት ምንድነው? የሆያሆዬው ጭፈራስ? ለመሆኑ ችቦ ማብራቱስ? …ቡሄን አስመልክቶ ከብጹ አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳ፣የአሪዞናና የዩታ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ም/ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያይተናል። ሙሉውን ያዳምጡ

<<…በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን፣የሲቪክ እና የፖለቲካ ድርጅቶች በግብጽ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ያለብንን ችግር አስመልክተው ድምጻችንን ጄኔቭ ለሚገኘው ለዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ጽ/ቤት ሊያሳውቁልን ይገባል…አሁን መንቀሳቀስም አልቻልንም ከፍተኛ ስጋት አለን ትልቅ መድልዎም በዩ.ኤን በኩል ይደረግብናል…>>

አቶ አስናቀ ሞላ በግብጽ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ

<<…አስቸጋሪ የሚሆነው መንግስት በሙስና ላይ ዘመቻ ይዟል የሚለው አይደለም።በተግባር በሚታይበት ጊዜ ማን የሙስና ወንጀል ይመለከተዋል? ከፍተኛ የፓርቲውና የመንግስት ባለስልጣኖችን ይመለከታል አይመለከትም? ቤተሰቦቻቸውን ይመለከታል አይመለከትም? የጦር ሀይሉን አዛዦች ይመለከታል አይመለከትም? የሚለውን ማየት ይኖርብናል ለፖለቲካ ተብሎ የሚወሰደው እርምጃ ዝቅተኛ ሙሰኞቹን እንጂ ከፍተኞቹን አይነካም…>>

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከህብር ሬዲዮ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ(ክፍል አንድ የተወሰደ.) ሙሉውን ያዳምጡት (ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)

ዜናዎቻችን
– የሙስሊሙ ትግል አስተባባሪዎች የአገዛዙን <<ሼህ ኑሩን ማን ገደላቸው ድራማ አወገዙ

– በሼሁ ሞት የመንግስት እጅ እንዳለበት ጥርጣሬ ማጫሩን ገለጹ

– ቦሌን ከፈንጂ አደጋ አዳንነው ሲሉ የአገዛዙ የጸጥታ ሰዎች ገለጹ

– ሕዝቡ ኢቲቪ ድራማውን ጀመረ እያለ ነው

– በሳዑዲ አጎቴን ገድያለሁ ያለው ኢትዮጵያዊ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

– ድምጻዊ እዮብ መኮንን አረፈ

– የግብጽ የሽግግር መንግስት የሙስሊም ወንድማማቾችን በሕግ ለማገድ ማሰቡን ገለጸ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
Go toTop

Don't Miss