June 5, 2013
4 mins read

“ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም” ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም

ከሰሞኑ መነጋገሪያ እየሆነ የመጣው የግብጽና የኢትዮጵያ በአባይ ጉዳይ እየተሰጣጡ ባለው እሰጥ አገባ ዙሪያ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም በፌስቡክ ገጻቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦
“ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩ ሞልተው ነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነት ያለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለ ወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግናን እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡

ለፍቅር መተዋወቅ እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለጠብም መተዋወቅ ያስፈልጋል፤ የተሟላ መረጃ ቢኖረን የጥንት ታሪክ እየጠቀስን ሰዎችን ለጦርነት እንቀሰቅስም ነበር ብዬ አምናለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ አስፈላጊ መረጃዎችን ላቅርብ፤ —

1. የግብጽ የጦር ኃይል በዓለም አሥረኛ ነው፣ በአፍሪካና በመሀከለኛው ምሥራቅ የሚወዳደረው የለም፤ አንድ ሚልዮን ተኩል ያህል የጦር ኃይል አለው፤ በዓየር ኃይልም ከዓለም አሥራ አራተኛ ነው፤ በታንክ ብዛት አራተኛ ነው፤ በባሕር ኃይል ሰባተኛ ነው፤ በጦር በጀት አርባ ሦስተኛ ነው፤
2. በኢትዮጵያ ዙሪያ ጂቡቲ፣ ሶማልያ፣ ሱዳን የአረብ ማኅበር አባሎች በመሆናቸው ለግብጽ ማኅበረተኞች ናቸው፤ በወያኔ ፈቃድ የተገፋችው ኤርትራም የዚሁ ማኅበር ታዛቢ አባል ነች፤ ከቀይ ባሕር ማዶ ያሉት አገሮች ሁሉ ሀብታሙንና ኃይለኛውን ሳኡዲ አረብያንም ጨምሮ የግብጽ ማኅበርተኞች ናቸው፤ በዚህ ሁሉ መሀከል የተከታተፈች ኢትዮጵያ ብቻዋን ነች፤
3. የቤንዚን ሀብትና ከሀብቱም ጋር የሚገኘውን ወዳጅና ጡንቻ አንርሳ፤

ይህ ማስታወሻ ለማስፈራራት አይደለም፤ ማስፈራራትን አላውቅበትም፤ እንዲያውም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ‹‹አትፍሩ›› ብሏቸዋል ተብዬ ተከስሼ ታስሬአለሁ፤ ስለዚህ አላስፈራራም፤ ጦርነት ከመጣብን ልናስቀረው እንሞክር፤ ሌላው ቢቀር እንድንዘጋጅ ጊዜ እናገኛለን፤ ገፍቶ ከመጣ ግን እንቋቋመዋለን፤ ለጦርነት አንቸኩል፤ ለኤርትራም ጊዜ ተናግሬ ነበር፤ የሰማኝ የለም፤ ጥጋብ ላይ ያሉ የሚርባቸው ዝና ነው፤ የሚያገኙት ግን ውርደትን ነው፡፡”

Latest from Blog

መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ዛሬ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥር 1ቀን 2025 ዓ/ም ነው ። አውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትን “ሀ” ብለው ጀምረዋል ። አዲሱን ዓመት ሲጀምሩም ከልክ ባለፈ ፈንጠዚያ ነው ። ርቺቱ ፣ ምጉቡና መጠጡ

ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። )

Go toTop