በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ ሲያጠምቁ የከረሙት አነጋጋሪው መ/ር ግርማ ወንድሙ እንዳያጠምቁ ታገዱ

May 9, 2013

“በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ ሲያጠምቁ የከረሙት አነጋጋሪው መ/ር ግርማ ወንድሙ እንዳያጠምቁ ታገዱ” width=”150″ height=”150″ class=”alignleft size-thumbnail wp-image-3064″ /> (ዘ-ሐበሻ) በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤ/ክ የማጥመቅ አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበሩት መምህር ግርማ ወንድሙ ካሁን በኋላ በደብሩ ውስጥ እንዳያጠምቁ በደብሩ አስተዳደር መልአከ ኃይል አባ ሚካኤል ታደሰ (ቆሞስ) ሚያዚያ 28 ቀን 2005 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ታገዱ። የዘ-ሐበሻ የአዲስ አበባ ምንጮች ደብዳቤውን አግኝተው አድርሰውናል። ለ እገዳው ምክንያትነት የቀረቡት አካባቢው የቱሪስት ቦታ ስለሆነ ለጸጥታ እና ለንጽህና የሚሉ ይገኙበታል።

“በደብሩ ውስጥ ከቀኖና ቤተክርስቲያን ውጭ እየፈጸሙ ያለውን የማጥመቅ ሥራ ማገድን ይመለከታል” በሚል ለመምህር ግርማ በተጻፈው ደብዳቤ ላይ ከዚህ በፊትም መምህሩ እንዳያጠምቁ ታግደው የነበረ ቢሆንም ጉዳዩ ሳይፈጸም መቆየቱንና ከሚያዝያ 28 ጀምሮ ግን መስቀል አደባባይ አካባቢ በሚገኘው እስጢፋኖስ ቤ/ክ እንዳያጠምቁ ታግደዋል።

እገዳው ለምን እንዳስፈለገ ደብሩ በጻፈው ደብዳቤ ላይ “የብጹዕ አቡነ ቀውስጦስ በ/አ/አ/ሀ/ስ የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ረዳት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ሰኔ 8 ቀን 2003 ዓ.ም በደብዳቤ ቁጥር 4290/90/03 የሰጡት የእገዳ ትዕዛዝ ያልተነሳና ያልተሻረ በመሆኑ፤ በግቢው ውስጥ ያለው ሁኔታ ለሃገርም ሆነ ለቤተክርስቲያኒቱ ሰላም አስጊ በመሆኑ፣ በተጨማሪም ደብራችን የአዲስ አበባ እንብርት በሆነው በመስቀል አደባባይ አካባቢ፣ በአፍሪካ ህብረት እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤትና በታላቁ ቤተመንግስት አካባቢ በመገኘቱ ምክንያት ሰላማዊ ቦታ መሆን እንዳለበት ከዚህም ሌላ በብዙ የውጭ ሃገር ዜጎች ቱርስቶችም በተደጋጋሚ ቦታው ስለሚጎበኝ በሰላም ገብተው እንዲገለገሉ እና እንዲጎበኙ፤ ንጽህናው የተጠበቀ፣ ሰላም እና ጸጥታ የተሞላ የጸሎት ስፍራ መሆን እንዳለበት ሰበካ ጉባኤው ስላመነ፤ አሁን እየተፈጠረ ካለው ችግር አንጻረና የተጀመረውም የማጣራት ሥራ ተጠናክሮ የማያዳግም ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ከዛሬ ሚያዝያ 28 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ለጊዜው የማጥመቅ አገልግሎትዎን እንዲያቆሙ የደብሩ አስተዳደር ሰባካ ጉባኤ ጽ/ቤት የ እግዳ ውሳኔ አስተላልፏል። ውሳኔውን ባለማክበር በቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ ለሚፈጠረው ማንኛውም ችግር ዋነኛ ተጠያቂ መሆንዎን እናስታውቃለን” ይላል።

የዘ-ሐበሻ ምንጮች ደብዳቤውን አድርሰውናል ይመልከቱት፦

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

Go toTop