ከመድረክ የቀረበ ጥሪ፦
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ /መድረክ/ በአሁኑ ወቅት የኢህአዴግ መንግስት ሰላማዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን በኃይል ለማፈን የሚወስዳቸው የኃይል እርምጃዎች እና ተፅዕኖዎች በአስቸኳይ ቆመው የሀገራችን ወቅታዊ እና መሰረታዊ ችግሮች በሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ አግባብ እንዲፈቱ መንግስትን በሰላማዊ ሰልፍ ለመጠየቅ ቅዳሜ ግንቦት 16 ቀን 2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6 ፡00 ሰዓት የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል፡፡
ስለዚህም የአዲስ አበባ እና የአከባቢዋ ነዋሪዎች ልክ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ከአራት ኪሎ በስተምስራቅ ወ.ወ.ክ.ማን አለፍ ብሎ ከሚገኘው የግንፍሌ ወንዝ ድልድይ ተነስቶ በህንድ ኤምባሲ በኩል በመታጠፍ በአድዋ ድልድይ አድርጎ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ኳስ ሜዳ /ታቦት ማደሪያ/ በሚባለው የመሰብሰቢያ ቦታ ድረስ በሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፉ ተካፋይ እንዲሆኑ መድረክ ጥሪውን በአክብሮት ያስተላልፋል፡፡
የኢትዮጵያ እና የህዝቦቿ አንድነት ለዘለዓለም ፀንቶ ይኖራል!!
የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ)