ሸንጎ “የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች መሆናቸው ያብቃ!” አለ

May 7, 2013

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) “የፍትህ አካላት የመጨቆኛና የማፈኛ መሳርያዎች መሆናቸው ያብቃ!” መግለጫ አወጣ። ሸንጎው ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው ላይ እንዳስቀመጠው ” አቶ እሰክንድር ነጋና አቶ አንዱአለም አራጌን ጨምሮ በሽብርተኛነት የፈጠራ ክስ ውንጀላ በረጅም እሰራት የሚማቅቁትን ውድ የኢትዮጵያ ልጆች በቀጣይነት ለማሰቃየት የአዲስ አበባ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወሰደውን እርምጃ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፣በጥብቅ ያወግዛል።”
“በመላው ዓለም የነፃ ፕሬስ መብት በሚከበርበት ቀን ዋዜማ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ በእውቅ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎች ላይ ካሁን በፊት የበታች ፍርድ ቤት ጥሎባቸው የነበረውን ፍርደ ገምድል ብይን እንዲጸናና የስቃይ ዘመናቸው እንዲቀጥል መፍረዱ አገዛዙ ነፃ ፕሬስንና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት ለ21 ዓመታት እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በዚያው አጥፊ ጎዳና እየቀጠለ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። የሀገሪቱ የፍትህ አካላትም ይህንኑ እኩይ ተግባር ለማሳካት ሙሉ በሙሉ የአገዛዙ የፖለቲካ መሳሪያ እንደሆኑ መቀጠላቸውን የሚያመለክት ነው።” ያለው የሸንጎው መግለጫ “የፍትህ አካላቱ የዜጎችን መብት ማሰከበርና መብታቸው የተረገጠባቸው ግለሰቦችም አለኝታ መሆን ሲገባቸው፣ ተራ የፖለቲካ መሣሪያ ሆነው መቀጠላቸው ለሀገሪቱ ህዝብ ብቻ ሳይሆን በሙያው ለተሰማሩትም ሁሉ እጅግ አሳፋሪና አሳዛኝ ነው።” ብሏል።
ሸንጎው መግለጫውን በመቀጠል ” እራሱን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የጫነው አገዛዝ፣ ሁሉንም ተቋማት ለአምባገነን ስርዓቱ እድሜ ማራዘሚያ አድርጎ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ድምጽ የሚያፍን፣ የሀገሪቱን ልዖላዊነት የካደና በተግባርም በመንቀሳቀስ አካሏን ያስቆረሰ፣ ያለባህር በር ያስቀረ፤ ደንበራችንን አሳልፎ ለጎረቤት ሀገር በገጸበረከትነት የሰጠ፤ በህዝብ መካከል የተለያዩ ልዩነቶችን እየፈለገ ግጭቶችን ሆን ብሎ የሚያራግብ፤ በሃይማኖት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት ምዕመናኑን ያሰቃየ፣እምነታቸውን የተፈታተነ፤ በሚናገሩት ቋንቋና በዘውጋቸው እየነጠለ ዜጎችን ለዓመታት ከኖሩበትና ህይወት ከመሰረቱበት ቀያቸው እያፈናቀለ የሚገኝ ፍጹም አምባገነናዊና ጎሰኛ ቡድን ነው። ባጭሩ የሀገራችንና የህዛባችን አበይት ችግሮች ዋናው ምንጭ ይኀው ስርአትና አገዛዙ ናቸው፣ በመሆኑም ከዚህ አስከፊ ስርዓት ፍትሃዊነትን መጠበቅ የሚቻል አይደለም።” ካለ በኋላ “ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ከዓመት ዓመት እየከፋ የመጣውን የመብት ረገጣና ፈላጭ ቆራጭ አምባገነናዊ ስርአት በአንድነት በመቆም አምርሮ እንዲታገል አሁንም ደግመን ጥሪ እናቀርባለን ። በተቃዋሚነት የተሰለፉ የፖለቲካ ሀይሎችም በህዝባችን ላይ የተጫነውን የጨለማ ዘመን ለማሳጠር በአንድነት ቆመን በጋራ ለመታገል እንችል ዘንድ ጊዜ ሳንወስድ ወደ ተግባር እንድናመራ አሁንም ጥሪያችንን እናቀርባለን።” በሚል መግለጫውን ቋጭቷል።

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

አበበ ፈለቀ በዲሲና በአካባቢዋና በሌሎችም የአሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ በተለይም የመኖርያ ፍቃድ የሌላቸውና ህጋዊ ሂደት ውስጥ ያሉት ጭምር በሰፊው እየተወሰደ ባለው የስደተኞች አፈሳና መመለስ (Deportation) ጋ ተያይዞ በቂ መረጃ አለማግኘት፣ ጭንቀትና ስጋት

አሜሪካ ለሚኖሩ፡ የስደተኞች አፈሳና መመለስን በተመለከተ ማወቅ ያለብን ነጥቦች

January 29, 2025
ይነጋል በላቸው “አማራ በድርድር የሚፈታ ችግር አልገጠመውም” በሚል ርዕስ በፈረንጆቹ አቆጣጠር Sept. 16, 2023 የሚከተለውን መጣጥፍ ጽፌ እንቅልፍ ሳይበግራቸው፣ ድካም ወፃማ ሳይፈታቸው ለሀገራቸው ትንሣኤ ሌት ከቀን ለሚታገሉ ድረ ገፆች በመላክ ለንባብ በቅቷል፡፡

የአማራና የኦሮሙማ ድርድር – በሣቅ አትግደሉን!

Go toTop