የራያ ሕዝብ በትግራይ ክልል መንግስት የሚደርስበትን በደል በመቃወም የራያ የአማራ ማንነት መከበር እንዳለበት በግልጽ ከሕወሓት ሲለቅ በጻፈው ደብዳቤ ያስቀመጠው የቀድሞው የድርጅቱ ባለስልጣን አቶ ዛዲግ አብርሃን አባት ሕወሓት በትግራይ ቴሌቭዥን ቃለምልልስ እንዲሰጡ እያስፈራራ መሆኑ ተገለጸ::
https://www.youtube.com/watch?v=xfHo-pr6jRQ
ከዚህ ቀደም የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን አባት በማስፈራራት በትግራይ ቴሌቭዝን ላይ በማቅረብ “ወልቃይት የትግራይ ነው” ያስባለው ሕወሓት አሁን ደግሞ ዛዲግ ራያ አማራ ነው በማለቱ አባቱን አቶ አብርሃም ሃኪምን በቴሌቭዥን አቅርቦ በአባቱ ራያ ትግራይ ነው ማስባል እንደሚፈልግ ነው ምንጮች የተናገሩት::
“የአቶ ዛዲግ ከህወሓት መልቀቅን ተከትሎ በሕወሓት ሰፈር ከፍተኛ ተስፋ መቁረጥ እና ትርምስ በመፈጠሩ ሳቢያ በአቶ ዛዲግ ቤተሰብ ላይ ውክቢያ ተጀምሯል::” ያሉት የቅርብ ምንጮች አባቱ በትግራይ ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው የማይናገሩ ከሆነ እርምጃ እንደሚወስዱባቸው ሕወሓቶች እያሰፈራሩ መሆኑ ተነግሯል::
በድሮው የሕወሓት ሥርዓት ሕወሓት ፌዴራል መንግስቱን ተቆጣጥራ በነበረችበት ወቅት “ፍየልን በድብደባ አሳምና ተኩላ ነኝ” ታስብል የነበረ ሲሆን ከፌዴራል መንግስቱ ከተባረረች በኋላ በትግራይ ክልል ግን ይህን ድርጊቷን አላቆመችም::
ትግራይ የሕዝቡ በደል ገንፍሎ እስኪወጣ ድረስ በአፈና ውስጥ እንዳለች የአረና ፓርቲ አመራሮች አቶ አብርሃ ደስታና አምዶም ገብረሥላሰኤ በተደጋጋሚ ለሕዝብ ይፋ ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወሳል: