ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአየርላንድ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊዮ ቫራድካርን ዛሬ ጥር 1 ቀን 2011 በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። እንደ ጠሚሩ ጽህፈት ቤት መረጃ ይህ ይፋዊ ጉብኝት በኢትዮጵያና በአየርላንድ መካከል ያለውን ከ20 አመታት በላይ የዘለቀ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ተብሎ ይታመናል።
https://www.youtube.com/watch?v=pKU8igiCV3I&t=500s
በሁለትዬሽ ውይይቱ ወቅት ጠ/ር ዐቢይ እንደተናገሩት የአየርላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉብኝት በኢትዮጵያና አውሮፖ መካከል ያለውን የጠነከረ ግንኙነት ማሳያ ነው:: የአየርላንዱ መሪ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ወራት የተመዘገቡትን ለውጦች አድንቀው አገራቸው ለኢትዮጵያ በተለይም በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንቨስትመንት ድጋፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል:።
በሌላ በኩል የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴይንሜር በዚህ ወር መጨረሻ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ:: ፕሬዚዳንት ፍራንክ በኢትዮጵያ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ይፋዊ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተሰምቷል::