አቅራቢ:- ሐይለገብርኤል አያሌው
ዓለማችን በኢኮኖሚ ነውጥ በጦርነት እሳት በዋጋ ንረትና በችግር ወላፈን በየአቅጣጫው እየተናወጠች ትገኛለች:: የአፍሪካ ቀንድም ቀን ባነሳቸው ዲታ የአረብ ሃገራት እስፖንሰርነት የቀጠናው ሃገራት ወደ ፍርሰት ለሚያደርሳቸው የእርስ በእርስ ጦርነት እየዳረጉ ነው:: ሱዳን በቀላሉ ልታገግም የማትችልበት የጦርነት ማዐበል ውስጥ ወድቃለች:: በሃገራችንም የቀጠለው አፈና ጦርነት እና ማህበራዊና ኢኮነሚያዊው
ቀውስ ሊያስከትል የሚችለው አደጋ እጅግ አስፈሪ ነው::
የአብይ አህመድ ሕዝብ ጨረሽ የድሮንና የከባድ መሳሪያ ጭፍጨፉና ማፈናቀል እና በሕዝብ ላይ የሚያደርሰውን ጭቆና ትኩረት ሊሰጥ የሚችል ዓለም አለም አቀፉዊ የዲፕሎማሲ ጫና አሁን ላይ አይታይም:: ምዕራብያኑም በየራሳቸው ጉዳይ በመውጠራቸው እንደ ኢትዮጵያን ላለ ሃገር ትኩረት የሚሰጡበት ሁኔታ የለም:: ስለዚህም የሕልውና አደጋ ላይ የወደቀው የአማራ ሕዝብ እራሱን ከበበው አደጋ ለማላቀቅ በሚችለውና ባለው አቅም ሁሉ ከመታገል ውጪ ሌላ አማራጭ የለውም::
አማራ እንደ ሕዝብ የደረሰበትን በደል ለመታገል ትግል ከጀመረ ሶስት አስዕርተ አመታት ሆኖታል:: በዚህ የአንድ ትውልድ ዘመን የትግል ሂደት ብዙ ውጣውረዶችና መስዋዕትነት ተከፍሎበታል:: እንደ ትግሉ እርዝማኔና እንደ ሕዝብ አማራ የገጠመውንአደጋ በቅጡ ተረድቶ በግዜ ለመደራጀትና ለመታገል ባለመቻሉ ብዙ ዋጋ እንዲከፍል እናም ዛሬ ላይ ለደረሰበት መከራ በቅቷል:;
የአማራ ሕዝብ የተጋረጠበትን አደጋ ለመመከት ብረት አንስቶ የፉኖ እንቅስቃሴ ከጀመረ ሁለት አመት ሊሞላው ተቃርቧል:: በዚህ ግዜ ውስጥ በርካታ አመርቂ የአደረጃጀት የሕዝብ ድጋፍና ወታደራዊ ቁመናን
መፍጠር ችሏል:: የፉኖ ፈጣንና ተስፉ ሰጪ አጀማመር በተለያዩ እዚህ ግባ በማይባሉ ምክንያቶች የታዩት የእርስ በእርስ መለያየቶች በትግሉ በደጀኑ ሕዝብና በደጋፊው ዲያስፖራ ላይ ቀላል የማይባል የሞራል መቀዛቀዝ አስከትሏል::
ጋብ ያለ ትግል ለቅልበሳ ! የተከፉፈለ ሃይል ለውድቀት የተናጥል ዘመቻ ለድምሰሳ! የመዳረግ እድሉ ከፍተኛ ነው:: የተባበረ ትግል ለውጤት የተቀናጀ ጦርነት ለድል እንዴት እንደሚያበቃ በቅርቡ የሶሪያ ሃይሎችን ሁኔታ መቃኘት በቂ ነው:: የጸረ አላሳድ ተቃዋሚ ሃይሎች በተራዘመው ትግል ተዳክመው
ወደተለያዩ ቀጠናዎች በማፈግፈግ ለእረጅም ግዜ ባልተሳካ ሙከራ ብቻ ተወስነው ቆይተዋል:: በመጨረሻም ልዩነታቸውን አጥብበውና አቻችለው በጥምር ያደረጉት ዘመቻ ለአመትት ያልቻሉትን በቀናት ውስጥ አሳክተው ለድል መብቃታቸውን አይተናል:: የሶሪያ ሃይሎች ያለባቸውን ጽንፍ የረገጠ የሃይማኖት የጎሳና የርዕዮተ ዓለም ልዩነት አርግበው በጋራ መቆም ከቻሉ በአጠቃላይ አስተሳሰብ መቶ በመቶ የሚመሳል አላማ ያነገበው የአማራ ፉኖ በአንድነት እንዳይሰለፍ ያደረገው ምንድን ነው?
የፉኖ አንድነት ማጣት ለገባበት የእርስ በእርስ ቅራኔ ትልቁን ድርሻ የሚወስደው በዲያስፖራ ያለው ደጋፊ ወቅቱንና ትግሉን የሚመጥን ቁመና ማጣቱ ነው:: የተሻለ የትምህርት የገንዘብና የሃሳብ ግብዐት ያለው በውጭ ያለው የአማራ ዲያስፖራና እንደ ጽዋ ማህበር የበዙት ድርጅቶች የመፍትሄ ሳይሆን የቀውስና : የቅራኔ ምንጮች የመለያየትና የመጠፉፉቱ : አቅጣጫ መንግድ ጠራጊዎች ; ሆነው መገኘታቸው የሃገር ውስጡን ትግል ጎድቶታል::
ለምን በስደት ያሉ ልሂቃንና ማህበራት በዚህ ያህል ደረጃ ለትግሉ እንቅፉት ሆነው ተገኙ የሚለውን ከተሞክሮ ያየሁትን እዚህ ላይ ማንሳቱ ምን አልባት ችግሩን ለመቅረፍ አስተዋጽዖ ይኖረዋል ብዬ እገምታለ :: በአብዛኛው በፖለቲካው ጎራ የተሰለፈው ወገን ወደ ትግሉ መድረክ ሲመጣ ለበጎ አላማ ቢሆንም
የትግሉ ባህሪ የማህበረሰቡ ሁኔታ ወቅቱን ያማከለ ግንዛቤ መረጃና : ትንተና ላይ ተመስርቶ ሳይሆን በስሜትና
በቁጭት ላይ ተመርኩዞ ነው:: ይህን አይነት በስሜት ላይ የተመሰረተ ግብታዊነት ያለበት የትግል ሁኔታን
ለማረቅ የሚችል የተማከለ አመራር አለመኖር ደግሞ ቀውሱን አብሶታል:: በዚህ ሁኔታ ውስጥ የበለጠ
በውስጥም በውጭም ያለው የአማራ አደረጃጀት እንዲከፉፈል ያደረጉት ሌሎች ነጥቦች:-
1.የፖለቲካ ንቃት እና አላዋቂነት
2.የጎጠኝነት መንሰራራት
3.ትምክህት
4.ባዶ ኢጎ
5.ቅንነት ማጣት
6.የማህበራዊ ሚድያ ያሳበጣቸው አላዋቂዎች መንገስ
7.የጋራ ርዕይና ትርክት አለመኖር
8.የሞራልና የመንፈሳዊነት መንጠፍ ( አባቶቻችን ካኖሩት በጎ ልማድ እና ባህል መራቅ
9.ፖለቲካዊ ውይይት ትችት ሂስና ግለሂስ በአሉባልታ እና ስድብ መተካቱ
10.በሚድያ ስም የተሰማሩ ከፉፉዬች መበራከት እና ሌሎችም የትግላችን እንቅፉቶችን መዘርዘር ይቻላል:: እነዚህን ነጥቦች በዝርዝር ማቅረቡ ግዜን የሚሻማ በመሆኑ የተወሰኑትን በወፍ በረር ብቻ ለመዳሰስ
እሞክራለሁ::
አማራው ዛሬ ላይ ለትግል ተነስቷል:: በሃገር ውስጥ ነፍጥ አንስቶ ለመታገል የቆረጠው ፉኖ በቁጥር ከአገዛዙ ሠራዊት እንደማይተናነስ ይነገራል:: ለወታደራዊ ትግል ትልቁ መሠረት በዲሲፕሊን የታነጸ የዕዝ ሰንሰለቱን የጠበቀ የበቃ ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራር ይጠይቃል:: በዚህ በኩል ፉኖ ውስጥ ከፍተኛ የብቃት ክፍተት መኖሩ ዛሬ ላይ የአደባባይ ሚስጥር ነው:: ፉኖን እየመሩ ያሉት መሪዎች ሰራዊቱን የሚመጥን ቁመና መፍጠር አልቻሉም:: የእርስ በእርስ መካሰሱ እና ለውጊያ መፈላለጉ ከቡድኖች ፍላጎት እና ከመሪዎች ኢጎ ውጭ ይህ ነው የሚባል ተጨባጭ ምክንያት የለውም::
በውጭ ያለው ዲያስፖራ በልምድ በእውቀትና በገንዘብ ለፉኖ ያደረገውና ሊያደርግ የሚችለው ድጋፍ ቀላል አይደለም:: እውቀት በልምድ በቅንነትና በሕዝባዊ ወገንተኝነት ካልታገዘ ካላዋቂው አጥፊ በላይ አደገኛ ይሆናል:: አሁን ላይ እየሆነ የሚታየውም ይህው ነው:: ቅዱስ መጽሃፍ “አውቂዎች ነን ሲሉ ደንቆሮዎች ሆኑ እንዲል” ለአንድ የፖለቲካ ትግል ተገቢውን እውቀትና ዝግጁነት ይጠይቃል::በዲያስፖራ ያለው ልሂቅ ይህን ማድረግ ተስኖታል :: ኢጎና ትምክህቱን ያስቀደመ ምሁር የአማራን ትግል እጅጉን ጎድቶታል:: ፖለቲካ
ሳይንስ ነው:: ነባራዊውን ሁኔታ የሕዝቡን ስነልቦናና የትግል መነሻና መድረሻ በቅጡ ገምግሞ : አንብቦና አጥንቶ በትግል ውስጥ ከመሳተፍ ይልቅ የምሁራዊ ማዕረጉን ብቻ በማስቀደም ፖለቲካውን በማወሳሰብ የአማራው ምሁር ያደረሰውን ጥፉት ዛሬ ላይ የአደባባይ ሚስጥር ሆኗል::
ከአማራ ቤተሰብ የተወለዱት የትላንት አብዮታውያኑ እነ ዋለልኝ በኩታና ጋቢ ሚዛን የባህል አድሎንና የብሄረሰቦች ጭቆናን የተነተኑበት መንገድ አማራን ብዙ ዋጋ እንዲከፍል አድርጎታል:: የትላንቶቹ አብዮታውያን በንባብ የሚታሙ ባይሆንም ያገላበጡት መጽሃፍ በአውድም ሆነ በሁኔታ ፈጽሞ የማይመሳሰለውን የሃገራችንን ፖለቲካ በቅልውጥ ርዕዮትና በተዛባ ትንተና ያኖሩት የሃሳብ መርገምት ለሚሊዮኖች የመጥፊያ መሳሪያ ሆኗል::
በተቃራኒው አሁን ላይ ያለው በአማራ ፖለቲካ ውስጥ ተዋናኝ ነኝ የሚለው ምሁር ትግሉን በተመለከተ ያለው ግንዛቤ እጅግ ደካማ ነው:: ችግሩን ከምንጭ የመፈለግ ከአድሏዊነትና ከፍርሃት የተላቀቀ የጠራና የነጠረ አቋም መያዝ የማይችል ሆኖ ይታያል:: ለዚህ ነው ጠቢባን “ደካማ ሕብረተሰብ የደካማ ልሂቅ ውጤት ነው” የሚሉት :: የምሁራኑ ድብታ ማህበረሰቡን ለሽብር ዳርጎታል:: ለመልቲዎች ስብከት ለጮሌዎች ግርግር አመቻችቶታል :: ለከፉፉዮች ሴራ አጋልጦታል:: የአማራ ፖለቲካ ብቁና ተደማጭ አሰባሳቢ ተቋም ባለመገንባቱ ቀውስና ቅራኔ እንዲነግስ በር ከፍቷል::
ይህ የልሂቃን ቅራኔን ማኔጅ የማድረግ አቅም ማጣት ትግሉን የሚመጥን ገዢ ሃሳብ ማቅረብ አለመቻል መፍትሄውን አርቆታል:: በዚህ ሁኔታ ውስጥ ጎጠኝነት ጥርስ አብቅሎ ብቅ ብሏል:: ጎጠኝነት ከትራኮማ ይልቅ አይን የሚያሳውር : ከኤድስ ይልቅ የሚያመነምን ከተስቦ ይልቅ የሚገል የሕዝባዊ ትግል ካንሰር ነው:: ጎጠኝንት የማይድን በሽታ እና ሗላቀርነት ብቻ ሳይሆን ሕዝባዊ ትግል የሚበላ ጭራቅ ነው:: ጎጠኝነት ምክንያታዊነት የሌለው ደመነብሳዊ የመንጋ አካሄድ ነው :: ጎጠኝነት ካገነገነ ሕዝባዊ ትግል በትንንሽ መንደሮች የሚበትን ለቅልበሳና ለዘመናት አበሳ የሚያሸጋግር አደገኛ መርገምት ነው::
ጎጠኝነት ተቋማዊ ቅርጽ እንዲዝ እየሆነ ነው:: ይህ ከአብይ አህመድ ድሮን መድፍና ሚሳዔል በላይ የአማራን ሕዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ አክርካሪውን ሰብሮ ለውደቀት የሚዳርገው የጥፉት መንገድ ነው:: ይህን ትግሉን ሊያመክን ያገጠጠ የጎጠኝነት ጥርስ በግዜ ማርገፍ ከሁሉም አማራ የሚጠበቅ ድርሻ ነው::
በአማራ የሕልውና ትግል ውስጥ: ዲያስፖራውም በሃገር ውስጥ ያለውም : ትግሉም ታጋዩም : ድርጅቱም ክፍለጦሩም ሻለቃ ይሁን ብርጌድ የአማራን አንድነት እስካላረጋገጠ ድረስ የትም አይደርስም:: አንዱን ጥሎ አንዱን አንጠልጥሎ ወንዝ መሻገርም አይቻልም:;አንዱን አጀግኖ ሌላውን ተሳድቦ ፈጽሞ ውርደትን እንጂ እንደ ሕዝብ ወደ ክብር አያሸጋግረንም:: በዘመናት የትግል ታሪካቸው የከበሩትን ጀግኖች
ቀርቶ ትግሉን ዛሬ የሚቀላቀለው ጭምር ሊከበር ሊወደስ ይገባል:: እያየን ያለነው እየሆነ ያለው ከዚህ ፍጹም ተቃሪ ጠላቶቻችንን የሚጠቅም የሕዝባችንን የትግል ተነሳሽነት የሚጎትት የትውልዱን ወኔ የሚሰልብ አካሄድ ነው::
አሁን ላይ የአማራው ፖለቲካ ከዘለፉ የመንጋ ፖለቲካ ከጭፍን ቀኖናዊ አቋም ከጎጠኝነት ከግለሰቦች አንጋሽነት ከምክንያት አልባ ውዝግብ እስካልተላቀቀ ድረስ የትም አይድርስም:: ከዚህ ለመውጣት መፍትሄው የመዳኛችን መድሃኒት አንድነታችን ብቻና ብቻ ነው:: አማራ ዛሬ ላይ ያለው አንድ አይን ብቻ ነው:: እሱም ፉኖ ነው:: ፉኖ በጋራ ካልቆመ ድልም ሰላምም ለውጥም አይታሰብም:: ስለዚህም መፍትሄው:- ◦
1.ሁሉንም ሃይሎች በቅጡ በሃቅና በመርህ የገመገመ በመረጃ የተደገፈ አቋም ላይ መድረስ
2.እጥፍቷል የሚባለውን መውቀስ በጎ የሰራውን መደገፍ
3.እርቅና መስማማትን ለማምጣት በሃቅና በመረጃ ላይ የተደገፈ የመፍትሄ አቅጣጫ ማንጸባረቅ:
4.አለ የሚባል ልዩነት ካለ በማስረጃ አስደግፎ ለሕዝብ ይፉ ማድረግ
5.በፉኖ አደረጃጀት ውስጥ ያሉት መሪዎች በተሻሉ ታጋዮች እንዲተኩ ሰራዊቱ አመራሩን እየገመገመ ብቁ ታጎዬችን ወደፊት ለማምጣት እንዲችል ማድረግ:
6.በዲያስፖራ እንደ አሸን የፈሉ አደረጃጀቶች በትኖ በአንድ ወጥ አደረጃጀት እንዲተኩ መስራት
7.ክፍለሃገራዊ አደረጃጀቶችን ማፍረስ የዚህ አይነት ዝንባሌ ያላቸውን ተቋማት ማግለል
8.በአማራ ተቆርቋሪነት ስም የተንሰራፉትን ሚድያዎች ላይ ጥራት ብቃት እና ሕዝባዊነታቸውን ገምግሞ ጥሩዎቹን መደገፍ አፍራሽ አላማ ያላቸውን ማጋለጥ;; ድል ለአማራ ፉኖ ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር
June 14 2025