
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመታቸው የአፋር ክልል ሕዝብን ይበልጥ ለሌላ ድል እንዲነሳሳ አድርጓል ሲሉ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ። የአፋር ክልል ሕዝብና አመራሮች የአሸባሪ ኃይሉን ግብአተ መሬት ለማፋጠን በጽናት እየተፋለሙ እንደሚገኙም አመልክተዋል።
የአፋር ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አሕመድ ኑርሳሊ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ወደ ግንባር መዝመት የአፋር ሕዝብ ወራሪውን ኃይል ለመፋለምና ድል ለመቀዳጀት የበለጠ አነሳስቶታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ለአፋር ክልል አመራሮችና ታዋቂ ግለሰቦችም ከፍተኛ መነሳሳትን ፈጥሯል ብለዋል።
የአፋር ክልል ሕዝብ ወራሪውን የሕወሓት ቡድን በመፋለም እየተገኘ ያለው ድል እንደተጠበቀ ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ግንባር መዝመታቸው የበለጠ ሕዝቡን በማነቃቃትና የአሸናፊነት ሥነ ልቦና በመላበስ በጠላት ኃይል ላይ ከፍተኛ ድልን ለመቀዳጀት እንደሚያስችል አብራርተዋል።
በተጨማሪም አሸባሪው ኃይል የሚነዛውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ሙሉ ለሙሉ የሚያመክንና መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ የጥፋት ኃይሉን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር የሚያነሳሳ ውሳኔ መሆኑን አቶ አሕመድ ኑርሳሊ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደ ግንባር ለሚዘምቱት..
የዚህን ዜና ሙሉ መረጃ ለማንበብ ከስር ያለውን ሊንክ ተጭነው ወደ ድረገጹ ይግቡ
(ኢ ፕ ድ )