
አዎ ! እርስዎ እንዳሉት የህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞች ከብሔ/ከዘር ፣ ከሐይማኖት እንዲሁም ከፖለቲካ ወገንተኝነት ፈጽሞ መራቅ አለባቸው ።
~ ይህ የሚሆነው በእርስዎ እናት ድርጅት ኢዜማ “በዜጎች የፖለቲካ የማህበራዊ ሥርዓት” እንጂ ” ብሔር ፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ” የፖለቲካ ሥርዓት አይደለም ¡¡
~ እርስዎም ”
#ለህገ_መንግስቱ_ታማኝ በመሆን” የተሰጠኝን ኃላፊነት በቅንነት፣በሕግና ሥርዓት ለማገልገል ቃል እገባለሁ። ብለዋል ¡¡
~ በሕገ-መንግስቱ ደግሞ የሥልጣን እና የሀገሩ ባለቤት ብሔር ፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ፤ እንጂ ግለሰብን ወይም ሰውን በዜግነት የሚቀበል አይደለም ።
~ ምን ይሄ ብቻ ፦ እርስዎ የሚመሩት ተቋም ጨምሮ አብዛኛው የመንግስት የሠራተኞች የቅጥር የምልመላ መስፈርቶች መካከል አንዱ የብሔር ተዋጽኦ ጭምር ነው ¡¡
~ ከዚህም ከፍ ሲል ሠራተኞች “በብሔራቸው” በግዴታ ይሁን ወይም በፍቃድ በፖለቲካ ተቧድነው የገንዘብ መዋጮ ይጠበቅባቸዋል ¡¡
እናም ክቡር ሚኒስትር ፦ ለባለፉት 31 ዓመት በእንዲህ መልኩ የተቃኘው ሥርዓት ፤ አሁን እርስዎ እንደሚሉት እንዲሁ በቀላሉ በስብሰባ ” ብሄርና ዘር ቤታቸው” ትተው ሠራተኞች ይመጣሉ ?!
ሌላው ደግሞ ፦ “…በፖለቲካ ፓርቲ ደጋፊነት ተጠግቼ ይህን ላገኝ እችላለሁ ማለት በፍጹም አይሰራም ” ብለዋል ፤
ክቡር ሚኒስትር ፤ እርስዎ ይህን ኃላፊነት ወይም ሥልጣን ያገኙት በምንድነው ?!