
የትግራይ ሕዝብ እባክህ ንቃ! ወያኔ በስምህ እየነገደ ልጆችህን የሚያስፈጀው እስከ መቼ ነው? ወያኔ ያልነበረ ታሪክ እየፈጠረ በአንተ ስም አገርህን ኢትዮጵያን እንደ ጣቃ ጨርቅ ቦጫጭቆ ጣለ!
ወያኔ ልጆችህን በእሳት ማግዶ አስጨርሶ በውጪ ሐይሎች ትከሻ ስንልጣን ሲይዝ ተሞት የተረፉትን ልጆችህን ወደ መጡበት መልሶ የራሱን ልጆችና ዘመዶች በሐብት ሲያጎልበት፣ በውጪ አገር በተዘረፈ ገነዘብ ሲያስተመርና ሲያንደላቅቅ ኖረ፡፡ ወያኔ ኢትዮጵያ እንዳትቦጫጨቅ የተቃወሙትን የትግራይ አዛውንት በአንተ ስም እየነገደ ጨፈጨፈ!
ወያኔ በስምህ እየነገደ የአማራንና የኦሮሞን ሕዝብ በመደዳ ሲገድልና በእስር ቤት ሲያጉር፣ ጉራጌውን ተስራ ሲያገል፤ ሲዘርፍ ኖሮ ሕዝቡ በምሬት ሲነሳበት አሁንም ራሱን ሊያድን ልጆችህን ለጦርነት ማገደ! ወያኔ በስህ እየነገደ ጋንቤላን ወሮ አኝዋኮችን ጨርግዶ መሬቱን እያረሰ በሐብት ሲደልብ ኖረ፡፡ ወያኔ በስምህ እየነገደ የኢትዮጵያን ሱማሌዎች በጀታቸውን ሲበላና እየረሸነና መሬት እየጎተተ ሲያሰቃያቸው ኖረ፡፡
ወያኔ የኢትዮጵያን ሐብት እየዘረፈ በአውሮጳና አሜሪካ ሲያከማች ኖረ፡፡ ወያኔ የኢትዮጵያን እናቶች፣ አባቶችና ልጆች እየገደለ መሬቱን ደም ስለቀባው ዛሬ እዳው ለአንተም ተረፈ፡፡ ወያኔዎች የራሳቸውን ልጆች በውጪ እያንደላቀቁ ዛሬም አንተን አታለውና ሕፃናት ልጆችህን አስገድደው በጦርነት እየማገዱ ነው! የትግራይ ሕዝብ ልብ በል! የኢትዮጵያ ሕዝብ ድሮ ተነብሩት፣ ዛሬም ታሉት ሆነ ነገ ከሚመጡት የትግራይ ልጆች ወንድምና እህት ነው፡፡ ችግሩ ተጭራዉ ተወያኔ ጋር ነው፡፡ የትግራይ ሕዝብ እባክህ ንቃ! ተወያኔ ተፋታና ከኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ ታሪክህ ተጋባ!