የኮሬ ነጌኛ: በኦሮሚያ ክልል ለሚፈፀም ከሕግ ውጭ ግድያ

February 24, 2024
በኦሮሚያ ክልል ለሚፈፀም ከሕግ ውጭ ግድያ እና እስራት አንድ ከፍተና የባለስልጣናት ሚስጥራዊ ኮሚቴ ትዕዛዝ ሲሰጥ መቆየቱን ሮይተርስ የዜና ወኪል ገለፀ

በኢትዮጵያ የከፍተኛ ባለሥልጣ


ናት የሚስጥራዊ ኮሚቴ፣ብዙ ህዝብ በሚኖርበት የኦሮሚያ ክልል፤ አማጽያንን ለመደምሰስ በሚል ከሕግ አግባብ ውጭ ግድያ እና ሕገወጥ እስራት እንዲፈፀም ትዕዛዝ ማስተላለፉን የሮይተርስ የምርመራ ግኝት አመልክቷል።

425335462 800269238804945 8907195604200840529 nሮይተርስ በዚህ ምርመራው ከ30 በላይ የፌደራል እና የአካባቢ ባለስልጣናትን ፣ዳኞችን፣ጠበቆችን፣በባለሥልጣናት እና በደል የሚደርስባቸውን ሰለባዎች ማነጋገሩን ጠቁሟል።
የዜና ምንጩ በሀገር ውስጥ ፖለቲካ እና የፍትህ ባለስልጣናት የተነደፉ ሰነዶችንም መገምገሙንም አስታውቋል።ከእነዚህ ቃለ መጠይቆች እና ሰነዶችም በኦሮምኛ ቋንቋ «ኮሬ ነጌኛ»ወይም የደህንነት ኮሚቴ የሚባለውን አካል አሠራርን ይፋ የሚያደርግ መረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ መገኘቱን የዜና ምንጩ ገልጿል።
እንደ ሮይተርስ የፀጥታ ኮሚቴው በኦሮምኛ ቋንቋ ፤«ኮሬ ነጌኛ» ሥራ የጀመረው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ከወራት በኋላ ሲሆን፤ከጎርጎሪያኑ 2018. ዓ/ም በፊት ግን ኮሚቴው አለመኖሩን ዘግቧል።
አምስት የአሁን እና የቀድሞ የመንግስት ባለስልጣናት ነገሩኝ ብሎ ሮይተርስ እንዳሰፈረው፤ ይህ ኮሚቴ ዓላማው የራስን እድል በራስ ለመወሰን ለዓመታት የዘለቀውን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ጦር የሽምቅ ውጊያ እንዲያበቃ ማድረግ ነው።
ከሮይተርስ ከአምስቱ ምንጮች አንዱ የቀድሞ የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ሚልኬሳ ገመቹ ሲሆኑ፤ እሳቸውን ጨምሮ አምስቱ ባለስልጣናት እንዳሉት ፤ በጎርጎሪያኑ 2019 ዓ/ም አዲስ የኦሮሞ ህዝብ አመፅ ሲቀሰቀስ ጠንከር ያለ እርምጃ በመውሰድ ይህ ኮሚቴ የመሪነት ሚና ነበረው።
የኮሬ ነጌኛ እንቅስቃሴዎችን የሚያውቁ ሰዎች በኮሚቴው ትዕዛዝ በርካታ ግድያዎች ተፈጽመዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እስር ተካሂዷል ሲል ሮይተርስ ባወጣው ዝርዝር የምርመራ ዘገባ አመልክቷል።
Dq

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Abiy Blood Thirsty man
Previous Story

በኦሮሞ እልፍኝ የተደበቁ ሳጥናኤል አብይ እና ጥቂት እፉኞች ፥ የጨነቀለት መከራዉን ሲያሳዩት የነበረውን ኦሮሞ አድነን እያሉ ነው

Amhara Fano Gojjam
Next Story

የአማራ ፋኖ በጎጃም ታሪካዊ መግለጫ

Go toTop