February 22, 2024
25 mins read

ወጣት ሆይ! እንደ ቀደምቱም ሆነ  እንደ አድዋና አምስቱ ዘመን አርበኛ ፋኖዎች ሸለል ፎክር!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)

Adwa

አንዳንድ ባህላቸውና ማንነታቸው ሸጠው የዘቀጡ አህያውን ቢፈራ ዳውላውን አይነት ምሁር ተብዮዎች ተጭራቅ ወሮበላ ገዥዎች ጋር በጓዳ በር እየሰሩ “ወደ ሁላ ያስቀረን ባህላችን ነው” እያሉ እንደ በፊቱ ድፍን አፍሪካ፣ ኤሽያና ደቡብ አሜሪካ ባርያ ሊያደርጉህ ሲዳዱ ይስተዋላሉ፡፡ ተጭራቅ ገዥዎች በተጨማሪ አገሪቱን ወደ ሁዋላ ያስቀሩ እነዚህ የራሳቸውን ባህልና ሃይማኖት አሽቀንጥረው ጥለው የምእራቡንም የምስራቁንም እድፍ በጭንቅላታቸው የተሸከሙ ምሁር ተብዮዎች እንደሆኑ ይክዳሉ፡፡ ወጣት ሆይ! ለእንደዚህ ዓይነት ራሳቸውን የሸጡ ድስኩራም ከሀዲ ምሁራን ጆሮህ ጥጥ ነው፡፡ አትስረቅ፣ አትዝረፍ፣ አታታል፣ አታወናብድ፣ ሰውን በዘሩ አትለይ፣ እሬሳ አትጎትት፣ ሳይነኩህ አትንካ፣ ጥቃትን አትታገስ፣ ከመለኮት በቀር ለማንም ላለመገዛት ሸልልና ፎክር የሚል ባህል ወደር የሌለውና የተቀደሰ ባህል መሆኑን የምታውቀው ነው፡፡ ስለዚህ ከመለኮት ውጪ ለማንም ላለመገዛት እንደ እንደ ቀደምቱም ሆነ እንደ አድዋና አምስቱ ዘመን አርበኛ ፋኖዎች ዝንተ ዓለም ሸልል! ፎክር!

 

የካቲት፣ መጋቢትና ሚያዚያ አርበኞች ደማቸውን እንደ ጅረት አፍሰውና አጥንታቸውን እንደ እሾህ ከስክሰው በድል አገር፣ ነፃነት፣ ክብር፣ ሃይማኖትና ባህልን ያስጠበቁባቸው ወራቶች ናቸው፡፡ እነዚህ አርበኞች ልቡ እንደ እንቧይ ያበጠበትን ተስፋፊ በመርፌ እንደተወጋ ፊኛ እያስተነፈሱ ለበርካታት ድሎች የበቁት በሃይማኖታቸው ተጠምቀው፤ ሽለላ፣ ፉከራና ሰምና ወርቅ ዘፈኖችን እንደ ማርና ወተት እየተመገቡ ስላደጉ ነው፡  ሽለላ፣ ፉከራና ባህላዊ ዘፈኖች የጀግና መፀነሻ ማህፀኖች፣ የፋኖ መወለጃ ወለሎች፣ የአርበኛ መጠመቂያ ባህሮችና የፋኖ ማደጊያ መስኮች ናቸው፡፡

በዋንሽንት ቀዳዳዎች የሚንቆረቆሩት ሽለላ፣ ፊከራና ባህላዊ ዘፈኖች የጀግናን አካል እንደ ብረት የሚያጠነክሩ፣ የአርበኛን ወኔ እንደ እሳተ ገሞራ የሚያስገነፍሉና ፋኖን  ተአንበሳና ተነብር ጋር የሚያሳድሩ በጠቢባን የተረቀቁ ብርቱ መንፈሳዊ ሀይሎች ናቸው፡፡

 

ወጣት ሆይ!

እነዚህን ረቂቅ መንፈሳዊ ሀይሎች ተባህልህ እንዲጠፉ ተውጪ ቅድመ አያቶችህ እየቀለጠሙ የመልሷቸው ተስፋፊዎች፣ ተውስጥ እነሱ የመለመሏቸው ባንዳዎች ያልሸረቡት ሴራ የለም፡፡ አብዛኛው ዓለም እንደ አራዊት በሚኖርበት ዘመን ጠቢባን ቅደመ አያቶችህ የጠበቧቸውን ጥበቦች በኃላ ቀር ባህልነት እየፈረጁ ለመቅበር ያልቆፈሩት የሸር ጉድጓድ የለም፡፡ ይህ አድግ የተባለው የባንዳ ጥርቅም እነዚህን ረቂቅ መንፈሳዊ እሴቶች በመጤ የባህል አረም አስወርሮ አማራን በጀግናና በአርበኛ ድርቅ ለማስመታት ያልቀላወጠበት መንገድ የለም፡፡

 

ወጣት ሆይ አጢን! የቱርክን እብሪት ያንበረከኩት ቀረርቶና ሽለላ ናቸው፡፡ የግብጥን እብጠት ሲያስተነፍሱት የኖሩ ባህላዊ ሰምና ወርቅ ዘፈኖች ናቸው፡፡ የጣሊያንን ታንክ፣ መርዝና እሮቢላ አፈር ድሜ ያስጋጡት ሽለላና ፉከራ ናቸው፡፡ የሽለላ፣ ፉከራና ባህላዊ ዘፈኖች ባይኖሩ ሥምህ ሮማኖ፤ የምትጽፍበት ፊደልም ላቲን ሆኖ ያርፈው ነበር፡፡ ስለዚህ ባንዳዎች እንደሚሉት ፉከራ ጉራ ሳይሆን ነፃነት ነው፡፡ ሰምና ወረቅ ዘፈን ኃላ ቀር ባህል ሳይሆን ጥበብ፤ ክበርና ፀጋ ነው፡፡ ሽለላ ያልሰለጠነ ሕዝብ ወግ ሳይሆን እጅግ የረቀቀና የሰለጠነ ነፃ ሕዝብ ባህሪ ነው፡፡ ሽለላና ፉከራ ወኔ ነው፡፡ ወኔም የነፃነትና የክብር ባህር ነው፡፡ ስለዚህ ይኸንን ባህልህን ሲያጣጥሉብህ የወኔና የጀግንነት ባህሪህን ማድረቃቸው ነው፡፡ ባህላዊ ዘፈንህን በቅናት ጦዘው ሲያናንቁት ጥበብህን፣ ክብርህንና ፀጋህን እንድትጥል ተፅእኖ ማሳደራቸው ነው፡፡ ሽለላና ፉከራህን ሲነፍጉህ ወኔህን፣ ክብርህንና ነፃነትህን መንጠቃቸው ነው፡፡

ወጣት ሆይ! እንደምታውቀው ሃይማኖትህ ዓለም በቅዱሳን የምትመራ የፍትህ ምድር እንድትሆን ያዝዛል፡፡ ዳሩ ግን የትናንትናዋም ሆነ የዛሬዋ ዓለም ለጉልበተኞች እንጅ ለቅዱሳን ተመችታ እንደማታውቅ ታሪክ ይመሰክራል፡፡ ድርሳናትም ዓለም የጉልበተኞች እንጅ የቅዱሳን ሐብት የሆነችበት ዘመን እንዳልነበረ አስረድተዋል፡፡ ጉልበተኞች ጉልበትን በጠመንጃ፣ በስብከትና በገንዘብ እንደ ጆፌ መጭልፈው ዓለምን እንደ ኳስ እያነጠሩ ሲያሽከረክሯት ኖረዋል፡፡ ዓለም እስከ ዳግም ምጣትም ተጉልበተኞች መዳፍ መውጣቷ ያጠራጥራል፡፡ ይህ እውነታ ጉልበት ለህልውና ያለውን ወሳኝ ሚና ያመለክታል፡፡ ጉልበት ለህልውና ያለው ወሳኝ ሚና በዳርዊን ምርምር ተረጋግጧል፡፡ ዳርዊን “ሰው በአዝጋሚ ለውጥ ተፈጠረ” ያለው ስብከት ውሀ ባይቋጥርም “ጉልበታም ደካማውን አጥፍቶ ዓለምን ይቆጣጠራል!” የሚለው ክርክሩ ትክክል እንደነበር ያለም ታሪክ ይመሰክራል፡፡

 

ወጣት ሆይ! ጉልበት ሲኖርህ ጀሮውን ከፍቶ የሚሰማህ ታገኛለህ! ጉልበት ሲኖርህ በድርድር ታሸንፋለህ! ጉልበት ሲኖርህ በጦር ውሎ ታሸንፋለህ! ጉልበት ሲኖርህ ህልውናህን ታረጋግጣለህ! ጉልበት ሲኖርህ እየመረጡ የሚያሳድዱህን ባለ ሁለት እግር አውሬዎች ታንበረክካለህ! ጉልበት ሲኖርህ የውጪ ሀይሎችን ዝምድናና ወዳጅነትም ታተርፋለህ፡፡ ጉልበት ሲኖርህ በዚች ከንቱ ዓለም የሚገባህን አግኝተህ ትኖራለህ፡፡ ጉልበት ከሌለህ ደግሞ ትጠፋለህ!

 

ጉልበት ለህልውና የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና አያቶችህ ተረድተውት እንደነበር የፈጠሩት የባህል ዘፈን፣ ሽለላና ፊከራ ይመሰክራል፡፡ አያቶችህ በአጥንታቸው ካስማነትና በደማቸው ምርግነት ገንብተው በጠበቋት አገር እንደ ጠላት የምትገደለው፣ የምትፈናቀለውና የምትሰደደው ያሁኑ አማራም እንደ አያቶችህ ከአውሬዎች ራስህን ተከላክለህ ትውልድን ለማስቀጠል የጉልበትን ጠቀሜታ መገንዘብ ይኖርብሃል፡፡ በጉልበት ለመጠንከርም የባህላዊ ዘፈንን፣ የሽለላንና የፊከራን አስፈላጊነት ማጤን ግድ ይልሃል፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ ፈጠረው” ከሚለው የድስት ሺህ ዘመን እምነትህ በተጨማሪ በዚች ከንቱ ዓለም ለህልውና ጉልበት አስፈላጊ መሆኑን መረዳት ይኖርብሃል፡፡ እግዚአብሔር “ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጥ”ን ያዘዘው አምላክ በመልኩ የፈጠረው ሰው ሲመታህ እንጅ ሰይጣን ተእግዚአብሔር ፈልቅቆ በተንኮልና በጭካኔ ያደቆነው አውሬ ሲነክስህ አለመሆኑን ማወቅ ይኖርብሃል፡፡

 

ሰይጣን ተእግዚአብሔር ጉያ ነጥቆ ያደቆነው ወራሪ ቀኛቸውን ሲመታቸው ግራቸውን በመስጠት ፋንታ አያቶችህ ወራሪውን እንደ አውሬ በመቁጠር እንደ አንበሳ አግስተው ከአናቱ ተጎምረው እስተንፋሱን እየዘጉ ዘርረውታል፡፡ እንደ አያቶችህ ተአውሬዎች ራስህን ተከላክለህ በክብር ለመኖር ያያቶችህን ፈለግ መከተል ይኖርብሃል፡፡ ሁለት እጅ፣ ሁለት እግር፣ ሰላሳ ሁለት ጥርስና እሚናገር ምላስ ያለውን ሁሉ እግዚአብሔር በመልኩ እንደፈጠረው ሰው በመቁጠር “ለኢትዮጵያ ህልውና ስል ቀኝ ፊቴን ሲመቱኝ ግራ ፊቴን ሰጠሁ” የሚል በምድር የመኖር መብትህን የሚነሳ በሰማይም ከገነት የሚያርቅህን ጅል ዐመል ማቆም ይኖርብሃል፡፡ ለግማሽ ክፍለ ዘመን የዘር መጥረግ ወንጀል እየተፈጠመብህና በእየ አስር አምቱ በሁለት ሚሊዮን እየጎደልክ ህልውናህ እንዳያከትም ያያቶችህን ፈለግ መከተል ይኖርብሃል፡፡ ያያቶችህን ፈለግ መከተል እንድትችልም ወደ ባህልህ መመለስ ግድ ይልሃል፡፡

ከባህሉ ያፈነገጠ ማህበረሰብ ከባህሩ እንደሸሸ አሳ በህልውናው አደጋ ይጋረጥበታል፡፡ አማራ በጀግና አፍላቂ ባህሩ በሚዋኝበት ዘመን ከዱር አራዊት አንበሳና ነብርን፤ ከሰው አራዊትም ቅኝ-ገዥዎችንና ተስፋፊዎችን አንድ ለአምስት የሚገጥሙ ጀግኖችን እንደ ብርቱካን እያንዠረገገ ሲያፈራ ኖሯል፡፡ ከባህሩ ባፈነገጠባቸው ግማሽ ክፍለ ዘመናት ወዲህ ግን በክብሩ ብቻ ሳይሆን በህልውናውም አደጋ ተጋርጦበት ይገኛል፡፡

 

ወጣት ሆይ! ስንዴ ጉዛም እስተ ሆድ ዕቃው በርቅሶ ታረሰው ለም መሬት ተዘርቶና ታርሞ እንደሚያፈራው ጀግናም በጀግንነት መንፈስና ወኔ ከለማ የባህል ማሳ ሲተከልና ሲኮተኮት ፍሬው ይጎመራል፡፡ ጠላትን እንደ ፍልጥ ተርክከውና እንደ ማገዶ አንድደው ድል ስልነሱ የምትዘፍንላቸውና የምትኮራባቸው አርበኞችህ በተፈጥሯቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ እነዚህን ሰዎች ከአላህ በቀር ማንንም የማይፈሩ ጀግኖች ያደረጋቸው ሲወለዱ የተነቀሩበት በጀግንነት ባህል የታሸ ቅቤ ሲያድጉም የበሉት በጀግንነት መንፈስ የተቦካ የባህል እንጀራ ነበር፡፡

 

በጀግንነት ባህል የተቦካ እንጀራን ጀግና አፍሪነት የተገነዘቡ ምዕራባውያን ከአምስቱ ዘመን ዳግም ሽንፈታቸው በኋላ ባህልህን በተለያዬ መንገድ ማጥቃት ጀመሩ፡፡ ብፁእ ቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ እንዳሉት ያገራቸው ባህልና ታሪክ ያልተቀዳበትን የጭንቅላት ቶፋ ይዘው ወደ ምዕራብ የተላኩትን ድስኩራም ተማሪዎች በምዕራባውያን ርዕዮተ ዓለም እያጠመቁ የራሳቸውን ባህል እንደ አተላ እንዲደፉት አደረጉ፡  እነዚህ የራሳቸውን ባህል እንደ አተላ የደፉ “ስልጡን” ተማሪዎችም ጠጉራቸውን እንደ ጫጉላ ሙሽራ እየከፈከፉ በባህላቸውና በሃይማኖታቸው ዘመቱ፡፡ ጀግና እንደ ደን የሚያፋፉ ቀረርቶዎችና ፉከራዎችን እንደ አልሰለጠነ ባህል ቆጥረው “ዘመናዊ” በሚሉት የምዕራባውያን ዳንስ እንደ ጋማ ከብት መራገጥ ጀመሩ፤ እርግጫቸውን ለሌሎችም አስተማሩ፡፡ ፉከራና ሽለላን እየተመለከቱ እንደ አባቶቻቸው ነፃ ሕዝብ መሆነ ትተው በውጪ ሲኒማ ፈዘው የእጅ አዙር ቅኝ ተገዥ ሆነው አረፉ፡፡

እነዚህ የዳንስ እርግጫና ሲኒማ ወረርሽኝ ተጠቂዎች ቅረርቶንና ፉከራን በዳንስ ኮቴ ስብርብር ከማድረግም አልፈው የቅኔን ፍልስፍና ማስተማሪያ የሆኑትን የባህል ዘፈኖች እያጠፉ የምዕራባውያንን ሙዚቃና ሲኒማ አስፋፉ፡፡ በእነዚህ ወራሪ ሙዚቃዎችና ሲኒማዎች ወጣቱን እያነፈዙ ለአገሩ ባህል ባይተዋር አደረጉ፡  በዚህም ምክንያት የቆንጆ ወንድ መለኪያው ጀግንነት መሆኑ ቀረና ሱሪን ከጪን ታጥቆ መዥገር እንደ ሸበባት ግታም ላም እየተውለደለዱ መራመድ ሆነና አረፈው፡፡

 

ይህ ጀግና አምራች ባህል ከአምስቱ ዘመን ድል ማግስት ጀምሮ በምዕራባውያን የባህል ጎርፍ እንደ ዓባይ ሸለቆ ዳገት መሸርሸር ቢጀምርም ጭራሹን የተጠረገው አማራን በጠላትነት የፈረጀ የወንበዴዎች አገዛዝ ከመጣበት ሶስት አስርተ ዓመታት ወዲህ ነው፡  ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ቀረርቶና ፉከራ በሬዲዮና በቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን በሰፈርና በመንደርም እንዳይሸለል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተከለከለ፡፡ በዚህ ክልከላ ምክንያትም ይህ ጀግናን እንደ አሳ ገንዳ የሚያራባው ባህር እንደ ጣና በእምቦጭ ተመጦ እንዲደርቅ ትልቅ ሴራ ተሸረበ፡፡ በዚህ ሴራም አዲሱ ትውልድ በቀረርቶና በፉከራ አይምሮንን በጀግነት እንዳያንፅ በምዕራባውያን አጉል ሱስ ተጠምዶ በባህል ሸቀን እንዲቆሽሽ ተደረገ፡፡

 

ወጣቱ እንደ አያቶቹ በጀግንነት እንዲታነፅ ይህ የባህል ቆሻሻ በሕዝባዊ ዘመቻ መጠረግ ይኖርበታል፡  የባህል ቆሻሻው በበረኪና ታጥቦ ወጣቱ በራሱ የባህል ባህር መዋኘት ሲጀምር እንደ አያቶቹ እንኳን ራሱን ሌሎችንም በጎርፍ ከመጠረግ ያድናል፡፡ ከሸረኞች ደባ የፀዳ ባህል እንደ አያቶችህ ቆራጥ፣ ታማኝና ሩህሩህ ጀግኖችን ያፈራል፡፡ ባህልህ ከቆሻሻ ሲፀዳ በእግዚአብሔር ሚዛን የሚፈርዱ ሽማግሌዎችና ዳኞችን ይፈጥራል፡፡ ከተንኮለኞች ሸቀን የፀዳ ባህል ሲኖርህ እንደ ጥንቱ ለቆባቸው የሚያድሩ ሼሆችና መነኩሴዎች ይኖሩሃል፡፡ ከባህል እድፍ የፀዳ ባህል ሲኖር የሰው የማይነካ የራሱንም የማይሰጥ ኩሩና ሙሉ ትውልድ ይገነባል፡፡

 

ወጣት ሆይ! ስለዚህ ለህልውናህም ሆነ ለክብርህ ወደ ባህልህ መመለስ ይኖርብሃል፡፡ ሱሪህን ከጪንህ ከፍ አድርገህ ከወገብህ በቀበቶ ማጥበቅ ይጠበቅብሃል፡  በባዕዳን ዳንስ እንደ ማይክል ጃክሰን እንደ ጥንዚዛ መፈናጠሩን ትተህ እንደ ሞላ ሰጥአርጌ በሽለላና በፉከራ መንጎራደድ ይኖርብሃል፡፡

 

ወጣት ሆይ! ወደ ባህልህ ተመልሰህ የቅድመ አያቶችህን ዱካ ስትከተል የማትወጣው ተራራና የማትሻገረው ባህር አይኖርም፡  ከፊትህ የተገተረው ተራራ ከኦቶማን ኢምፓየዬር ወይም ከአውሮጳውያን ቅኝ ገዥዎች አጠገብ የሚደርስ አይደለም፡፡ በባህልህ ዳግም ታንፀህ ይኸንን ዳገት ሜዳ ማድረግ አቅቶህ ሕዝብህንም ሆነ ቅርሶችህን ማስፈጀት አይኖርብህም፡፡

 

ዓለም በሚያንቀላፋበት ዘመን ቅደመ-አያቶችህ የጠበቡትን ላሊበላን ማደስ አቅቶህ እንደ አይምሮ በሽተኛ ፈረንሳይን እየለመንክ ክብርህን እንደ ድሪቶ መጣል የለብህም፡፡ እሳት ማጥፋት አቅቶህ በአያቶችህ እርዳታ ትናንት ነፃ የወጡትን ደቡብ አፍሪካውያን እጅና እግሩን እንዳጣ “በእይነተ-ስመዓለማርያም” እያልክ የዓለም መሳቂያ መሆን አይኖርብህም፡፡ የሙሴ ጽላት ለስምንት መቶ ዓመታት የተጠለለበት፣ የብዙ የሃይማኖትና ፍልስፍና መዛግብት የሚገኙበትና የእልፍ አእላፍ ፍጥረታት መኖሪያ የሆነው ጣና ሲደርቅ እንደ ባዕድ ቆመህ ማየት የለብህም፡፡

 

ከአያቶችህ ባህል በማፈንገጥህ የምዕራባቡም የምስራቁም ሎሌ በሆኑ ለማኝ ገዥዎች ሥር ስትማቅቅ መኖር የለብህም፡፡ የወኔና የጀግንነት የባህል ባህርህን አድርቀው ሊያጠፉህ የሚሹ ጭራቆች እንዳሉ ለሰከንድም መርሳት የለብህም፡፡

 

አንዳንድ ባህላቸውና ማንነታቸው ሸጠው የዘቀጡ አህያውን ቢፈራ ዳውላውን አይነት ምሁር ተብዮዎች ተጭራቅ ወሮበላ ገዥዎች ጋር በጓዳ በር እየሰሩ “ወደ ሁላ ያስቀረን ባህላችን ነው” እያሉ እንደ በፊቱ ድፍን አፍሪካ፣ ኤሽያና ደቡብ አሜሪካ ባርያ ሊያደርጉህ ሲዳዱ ይስተዋላሉ፡፡ ተጭራቅ ገዥዎች በተጨማሪ አገሪቱን ወደ ሁዋላ ያስቀሩ እነዚህ የራሳቸውን ባህልና ሃይማኖት አሽቀንጥረው ጥለው የምእራቡንም የምስራቁንም እድፍ በጭንቅላታቸው የተሸከሙ ምሁር ተብዮዎች እንደሆኑ ይክዳሉ፡፡ ወጣት ሆይ! ለእንደዚህ ዓይነት ራሳቸውን የሸጡ ድስኩራም ከሀዲ ምሁራን ጆሮህ ጥጥ ነው፡፡ አትስረቅ፣ አትዝረፍ፣ አታታል፣ አታወናብድ፣ ሰውን በዘሩ አትለይ፣ እሬሳ አትጎትት፣ ሳይነኩህ አትንካ፣ ጥቃትን አትታገስ፣ ከመለኮት በቀር ለማንም ላለመገዛት ሸልልና ፎክር የሚል ባህል ወደር የሌለውና የተቀደሰ ባህል መሆኑን የምታውቀው ነው፡፡ ስለዚህ ከመለኮት ውጪ ለማንም ላለመገዛት እንደ እንደ ቀደምቱም ሆነ እንደ አድዋና አምስቱ ዘመን አርበኛ ፋኖዎች ዝንተ ዓለም ሸልል! ፎክር!

 

ከአያቶችህ ባህል በማፈንገጥህ የምዕራባቡም የምስራቁም ሎሌ በሆኑ ለማኝ ገዥዎች ሥር ስትማቅቅ መኖር የለብህም፡  የወኔና የጀግንነት የባህል ባህርህን አድርቀው ሊያጠፉህ የሚሹ ጭራቆች እንዳሉ ለሰከንድም መርሳት የለብህም፡፡ ወጣት ሆይ! ህልውናህም ሆነ ክብርህ የሚቀዳው አያቶችህ ከጠበቡት የባህል ባህርህ!

 

ወጣት ሆይ! ከመለኮት ውጪ ለማንም ላለመገዛት እንደ እንደ ቀደምቱም ሆነ እንደ አድዋና አምስቱ ዘመን አርበኛ ፋኖዎች ዝንተ ዓለም ሸልል! ፎክር!

 

የካቲት ሁለት ሺ አስራ ስድስት  ዓ.ም.

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop