የጠቅላይ ሚኒስትሩ አምላክ

ጠ/ሚ አብይ ለ2016 ዓ.ም. ዘመን መለወጫ በጽሁፍ ባስተላለፉት መልእክታቸው ውስጥ “…ጽኑ መርህ፣ ብርቱ ህዝብና የማይሸነፍ አምላክ ስላለን እዚህ ደርሰናል…” ብለውናል፡፡ ይህን ካነበብኩ በኃላ እሳቸውን የሚረዳቸው አምላክ፣ ጠላቶቻቸውን የሚያስገዛላቸው፣ ተቀናቃኞቻቸውን ከእግራቸው በታች የሚጥል፣ ለጦርነት ሲወጡ አብሯቸው የሚወጣው፣ እሳቸው የማይሸነፍ አምላክ አለን የሚሉት አምላክ የቱ ነው ስል እራሴን ጠየቅሁ፡፡

በእርግጥ ጠ/ሚሩ ከዚህ በፊት አመት በእልን አስታከው በሚያቀርቧቸውም ሆን በንግግራቸው ውስጥ በእየሱስ ታሪክ ትይዩ እራቸውን እያመሳጠሩ ሲጽፉ አንብበናል ጽፈንባቸዋለንም፡፡ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንግዲህ ብልጽግና የራሱ የሆነ አምላክ እንዳለው እየነገሩን ነው፡፡  በህዝቦች መካከል ክርክር፣ጠብና ጦርነት ቢኖር እንኳን መገፋትና ብሶትን ተከትሎ የሚመጣ እንጂ አንዱ አሸናፊ አምላክ ስላለው ሌለው ደግሞ የዳቢሎስ ሰራዊት ስለሆነ አይደለም፡፡

አሁን ደግሞ ስለ ጠ/ሚሩ ሴይጣኖች አንዳንድ ነገር እንበል፡፡ከዚህ በፊት ጠ/ሚ ስለ ድርድርና ውይይት ሲናገሩ እንዲህ ብለው ነበር “…በየግዜው ግድያ በየግዜው ምናምን በሚሆንበት ሰዓት ለውጡን በህይወታቸው ተወራርደው ያመጡት ግለሰቦች ሳይቀሩ፣ አይ እነዚህን ሰዎች አንችላቸውም ተስማምተን ካለቀጠል በቀር፣ እንዴት ሰው ከሴይጣን ጋር ሊሰማማ ይችላል? ለይተህ ቆርጠህ ካልሰራህ በቀር…”

እንግዲህ ጠ/ሚሩ ላይ በተቃውሞ የሚሄዱ ሁል ከሳቸው ወገን በኩል ያልሆኑ ሴይጣኖች ናቸው፡፡ የሸኔን አላውቅም ምክነያቱም እንደ ሂንዱ ስላሴዎች ከመንግስት ጋር ሚና ተካፍሎ ሲሰራ አይተንዋልና፡፡ እነ ዶ/ር ሃንጋሳ አህመድ እንደመሰከሩት ሁሉ፡፡ ወያኔ ግን ለሆነ ግዜ ያህል ሴይጣን ነበር፡፡ የትግራይ ህዝብ በርሃብ የተቀጣውም የሴይጣን ተከታይ ስለነበረ ነው ማለት ነው፡፡ አሁን ደግሞ ትልቁ ሴይጣን ፋኖ ነው፡፡

“…ለይተህ ቆርጠህ ካልሰራህ በቀር..” የሚለው የጠ/ሚ አብይ አባባለ ፋኖ ላይ ሲሰራ አይተናል፡፡ አማራ ክልል ውስጥ የአብይ መንግስት ጦርነት ከመጀመሩ በፊት ፋኖዎችን ከፋፍሎ ለመምታት ይመቸው ዘንድ ለተወሰኑ ፋኖዎች ሽልማት ሰጥቶ ነበር፡፡የጠ/ሚ አስታርቆ ማጋጨት የፖለቲካ ቢህላቸው በኦርቶዶክስ፣ ሙስሊሙና በፕሮቴሰታነቱ ዘንድ እንኳን ሳይቀር ሲተገበር ተመልክተንዋል፡፡

ፋኖዎቹም ይሁኑ የአማራ ክልል ህዝብ በአብዛኛው የሚያመልከው አብርሐማዊውን አምላክ ነው፡፡ ክርስቲያኖቹም ይሁኑ ሞስሊሞቹ እንዲሁም አይሁዶቹ ስለ አለም አፈጣጠር ስውና እግዚአብሄር ሊኖራቸው በሚገባው ግኑኝነት በመ/ቅ ኦሪታዊ ታሪኮች ላይ የጋራ የሚያደርጓቸው ነግሮች አሉ፣ አዲስ ኪዳን ላይ ቢለያዩም፡፡ ታዲያ እንዴት ባለው ትርክት ነው ፋኖ ሴይጣን የሚሆነው?

ተጨማሪ ያንብቡ:  ወያኔ ቅዠት እንጂ ራዕይ የለውም! በመቅደስ አበራ (ከጀርመን)

አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች ጠ/ሚ የአፍ ድጥ(ፋዎል) ይሰራሉ ይላሉ፡፡ ነገር ግን ሃበሻ በቢህሉ እንደሚለው፣ ከልብ ሞልቶ የተረፈው በአፍ ይወጣል ነውና ነገሩ ከጠ/ሚሩ ድብቅ ማንንት የሚመነጭ ነው፡፡ የጠ/ሚሩን መጽሐፍ እርካብ እና መንበር ላነበበ ሰው፣ ሰውዬው በዲሰኩራቸው ለኢትዮጵያ ህዝብ ደጋግመው የአምላክን ቃል የሚጠሩት ለራሳቸው አላማ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

ስልጣን ላይ ከመውጣታቸው በፊት የጻፉት መጽሐፍ ስልጣን ላይ ከወጡ በኃላ የሚተገብሯቸው ነገሮች ሁሉ አስቀድሞ የታሰበበት (premeditated, deliberate ) እንጂ ድንገቴ(spontaneous) አለመሆኑን ናገራል፡፡ ጠ/ሚ ቀጥለው ኤርትራ ውስጥ ሰለሚገኝ ጭራቅ ወይንም ሴይጣን ቢያወሩ አይገርምም፡፡ ምክነያቱም እየዞሩ ሰሜናዊውን ስልጣኔ ከማጥፋተቸው በፊት አያቆሙምና፡፡

ከኤርትራ ጀምሮ እሰከ አማራ ያለው ሴማዊ ስልጣኔ ምን አደረገ? ፊደል፣ የሙዚቃ ኖታ፣ ስእልን ጨምሮ ለአፍሪካ ያሰተማረ ህዝብ ነው፡፡ ፍልፍል ቤተ እምነቶችን ለሺህ አመታት እስከ ዛሬ ድረስ ከኤርተራ እሰከ ባሌ ድረስ ስርቶ ለታሪክ ያሰቀመጠ ነው፡፡

ጠ/ሚሩ በእረካብና መንበር መጽሐፋቸው “ሞዐ አንበሳውን” እንዴት የማይረባ ትርክት እንደሆነ አስነብበውናል፡፡ የነገስታቱንም ጭካኔ ሊያስነብቡን ሞክረዋል፡፡ ነገሩ ግን በየዘመናቸው መስፈርት ሲለካ የሳቸው ግዜ ብሶና ከርፍቶ ይገኛል፡፡

እናቴ በሰባት አመቴ ሰባተኛው ንጉስ እንደምሆን ነግራኛለች፡፡ ንጉስ የምሆን እኔ እንዴት ፈረንሳዊት አገባለሁ(የሚመጣው ቴውድሮስ ለመባል ጎንደሬዋ ጋር ሄዱ እንጂ)፡፡ ነገሩ ኦሪታዊ ክርስቲያን የሆነው ኦርቶዶክስ፣ እንዲሁም ሱፊው ሞስሊም በትንቢቱ ይመጣል የሚለውን ደግ ንጉስ ለመምሰል ሁን ብለው ያደረጉት አዲስ ትርክት ነበር፡፡

ነበር ያልኩት ይመጣል የተባለው ንጉስ የሰላም እንጂ እንደሳቸው የመአት ስለአልነበረ ነው፡፡እሳቸውን ለስልጣን ያዘጋጅ የነበረ አካል፣ የኢትዮጵያን ታሪክ በደንብ አጥንቶ ያን መረማመጃ በማድረግ አዲስ ሴማዊ አልባና የተዋጠ ደቡብና ምሰራቅ በፀረ ሴማዊነት ጉግ ማጎግንት መፍጠር ነበር፡፡

ነበር ያልኩት መደመርም ሆነ ሰውዬው ታሪክ ለመሆን ጫፍ ላይ በመድረሳቸው ነው፡፡ አንዳንድ ግዜ ጠ/ሚ እኔ ምንም ያፈረስኩት ቤት የለም ሲሉ ይሰማሉ፡፡ ያ ማለት ደግሞ ከቁጥጥሬ ውጭ የሆነ አካል አለ ለማለት ይመስላል፡፡ ማን ነው ጠ/ሚሩን ያሰራቸው? ውሸት ነው ማንም ያሰራቸው የለም፡፡ ባጠገባቸው የተኮለኮሉት ባለስልጣናት ሁሉ በዘረፋና ወንጀለኝነት እሳቸው ያሰሯቸው ናቸው እንጂ፡፡

የፕ/ት ሺመልስ አብዲ አሰምኖ ወይም አደናግሮ(convince or confuse ) መርህም ቢሆን እርካብና መንበር ውስጥ በደንብ ተሰተጋብቶ ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ሁሉ አስቀድሞ ታሰቦበት የተለያዩ የፖለቲካል ጽንሰ ሃሰቦችን አጋጥሞ የተቀናበረ ነው፡፡ ለምሳሌ በፖለቲካ ኀይል(political power) ንድፈ ሃሳብ ውስጥ coercion and persuasion  ቃላትን ይመስላል የነሺመልስ አብዲሳ ወይ ኣሳምን ወይንም አደናግር የሚለውን ሃሳብ የቀዳው፡፡ ነገር ግን ኮሪሺን(coercion) በሚለው ውስጥ ኃይልና ውጥነቅጥ(disorder) ሊገኝ ስለሚችል ይሄን ግዜ ቄሮን ልታመጣው ትችላለህ፡፡ ይህን ተከትሎ ነው እንግዲህ ኦሮሙማ ብለው የሚገልጹት፣ የአብዮታዊ ዲሞክራሲን ትክ፣ ርዕዮት እንደ ጦስ ዶሮ ወዲያ ወዲህ እየተንደፋደፈ ምስራቅ አፍሪካን ቀውጢ ሊያደርግ የተነሳው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ብአዴንና ሌሎቹ ኢትዮጵያን በማጥፋት ላይ ከሚገኘው ሕወሃት ጋር እየተባበሩ ያሉት ወገኖች በድንቁርና ነው

መቼም እንደ የቀድሞው የኮንጎ(ዛየር) አምባገነን መሪ ሞቡቱ ሴሴሴኮ ስራቸውን በወታደርነትና ሰላይነት ጀምረው፣ ለውጥ ያመጡ ጓዶቻቸውን መስዋት በማቅረብ ለስልጣን የበቁት ዶ/ር ኮሮኔል አብይ አህመድ ለሰልጣን የሚያበቃቸውን እርካብ ወደ ላይ ሲጎዘጉዙ፣ ከሞቡቱ ትንሽ የቀላቀሏት ሃሳብ አያጡም፡፡ ግብጻዊው መሐመድ ሙርሲ በህዝብ ቢመረጥም ደህንነት ሴክተሩ ላይ ስላልሰራ ነው የተገለበጠው፡፡ እኛ አሁን ወታደሩንና ደህንነቱን መልስን እያዋቀርን ነው ያሉን ጠ/ሚ አብይ ከሞቡቱ አልተማሩም ማለት ያስቸግራል፡፡

ሞቡቱ እነ ፓትሪስ ሉሙምባን በግዜው የነበረውን ጠ/ሚ ካጠፉ በኃላ ስልጣናቸውን ያጠናከሩት ያልተወለዱ ልጆች እንኳን ስለእሳቸው ፓረቲ ከእራስ በላይ ብለው እንዲምሉ በሙዚቃና ዳነስ ሚኒስተሮቻቸው በማሰጨፈር ነበር፡፡

ሚኒስተሮቹ አሰጨፋሪ ነበራቸው፡፡ ሞቡቱም ይህን ቁጭ ብሎ ያያል፡፡ሞቡቱ ፈጣሪ ነው ይላል፣ ሞቡቱ ዋነኛው ገንቢ ኃይል ነው፣ ሞቡቱ ከሁሉ አደጋ የሚተርፍ ሰው ነው…ታዲያ ጀማው ኮነጎ አዎ ነው፣ አዎ ነው ይላል፡፡ ከዚያም ሞቡቱ በየ ቴሌቪዥንና ጋዜጣው ከሰማይ ከዳመና ውስጥ ሲወርድ የሚያሳይ ምስል ይለቀቃል፡፡ አብይ አህመድስ?

የሚገርመው ነገር ሞቡቱ የአሜሪካኖቹ (ሬገንና ብሾች) ድጋፍ ቢኖረውም ቀኝ ገዢዎቹን ቤልጄሞችን ይቃወም ስለነበር አውትነቲሲቲቲ በሚል ፕሮግራም ወደ ኃላ በመመለስ ፀረ ክርስትና እሴቶች አድርጓል፡፡ የቦታ ስሞችን ወደ ድሮ ዛየራዊ ስሞች ቀይሯል፡፡ ኮነጎንም ወደ ቅድመ ጥንት ስሟ ዛየር ቀየረ፡፡ እንዲህ ናት ኦሮሙማ፡፡ ግን ኦሮሞን እንደ ኢትዮጵያዊ ያዳነ፣ የራሱ ወንድም እንጂ ቀኝ ገዢ አልነበረውም፡፡ ስርአታዊ መሐበራዊ ጭቆና በመደብ ትግል የሚገለጽ እንጂ ሌላ አይደለምና፡፡

ኢትዮጵያ ላይ ጣሊያን ቀኝ ገዢ ኃይል ሆኖ መጣ፡፡ ህዝቡን ከፋፍሎ ለመግዛት ሲባል ዘሩን ዘርቶ ሄደ፡፡ ያን ፍሬ እየበላን የምስራቅ አፍሪካ ህዝቦች ይኸው እንጋደላለን፡፡ ፋሺዝምን ተከትሎ ደርግ የስታሊን በትር ይዞ መጥቶ ህልቁመሳፍርቱን ጨረሰ፡፡ ወያኔ- ኢህዲግ ያንኑ የሰታሊንን በትር አቀበለን፣ ተጨፋጨፍንበት፡፡ አሁን ደግሞ ኦሮሙማ…

ተጨማሪ ያንብቡ:  ”የራሷ እያረረባት የሰው ታማስላለች” (ዘ-ጌርሣም)

አሁን በአማራ ክልል እየተደረገ ያለውን ጦርነት ሳስብ አንዳንድ ሐይማኖታዊ ታሪኮች ትዝ ይሉኛል፡፡ይኸውም በሰማይ ተደርጎ የነበረው ጦርነት ነው፡፡ በመለአክቱ ማለትም በእግዚአብሔር መንግስትና በሳጥናኤል መካከል በተደረገው ጦርነት፣ በመጨረሻ ሴይጣን በጭለማ ተጠቅልሎ ወደ እንጦሮጦስ ሲወረወር እንዲህ ብሎ ነበር አሉ፡፡

ሌሎች ከእሱ ጋር የነበሩት አማጽያን ወደ ላይ አሸቅበው ሲያዩ እነርሱ ወደ ታች እየወረዱና ሊቀ መልአኩ ሚካኤል ግን ከላይ ጸንቶ እንደቆመ ሲገናዘቡ፣ አረ ጌታው ወደ ታች እየወርድን እኮ ነው አሉት፡፡ ያን ግዜ ሳጥናኤል ቀና ብሎ አይቶ አይ እሱ እየሸሸ ነው አላቸው፡፡ እንግዲህ ይኼው ነገሩ፣ ሴማዊውን አጥፍቼ ሌላው ለቁጬ እኖራለሁ የሚለው ኀይል መጨረሻ፡፡

ጠ/ሚ ብዙ ነበያት እንዳላቸው መገንዘብ ብዙ አሰቸጋሪ አይደለም፡፡ እሳቸው አምላኬ የሚሉት ግን ለተቃዋሚዎቻቸው አምላክ ከልሆነ ግነ ማን ነው? እስኪ ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እንመልከት፡፡

መጽሓፈ ዜ/መ 2ኛ 18 የሚነበበው ታሪክ እንዲህ ይላል፡፡ የእስራኤል ነጉስ የነበረው አክዓብ የይሁዳውን ንጉስ ይዞ በሶሪያዎች ላይ በሬማት ዘገለድ ስልፍ መውጣት ፈለገ፡፡ አራት መቶ የሚሆኑ ነብያቱ ውጣ እስራኤል አምላክ ሁሉን በእጅህ ሰጥቶሃል አሉት፡፡

በይሁዳው ንጉስ ወትዋችነት፣ ሁል ግዜ ጥሩ አይናገርም የተባለው ነብይ ሚኪያስ ወደ እነሱ ተጠራ፡፡ እሱም እግዚአብሔር ፈርዶብሃል፣ የሚያታልል መንፈስ በአንተ ነብያት ላይ አውርዷል፣ በምትሄድበት ስፍራም ትወድቃለህ ብሎ ነገረው፡፡ እንዲያም ተፈጸመበት፡፡

ክቡር ጠ/ሚ ሆይ ከዚህ በኃላ ምን ተብለው እንደሚጠሩ ባላውቅም…ግን አንድ ነገር አውቃለሁ “ኃይልና ስልጣን የሰፊው ህዝብ ነው!” ትግራዩ ያለቀበት ኢትዮጵያ፣ አማራው እያለቀበት ያለው ኢትዮጵያ፣ ኦሮሞው የነፈረበት ኢትዮጵያ፣ ዜግነት ትረጉም አልባ የሆነባት ኢትዮጵያ፣ ዘረፋና ቀማኝነት የሰፈነባት ኢትዮጵያ ይዘው ቄሮ፣ ቃሬ ቢሉ ትርጉሙ ምንድን ነው? እንዲህም ተብሏል “ከወደቁ በኃላ መገላበጥ ለመላላጥ” አበቃሁ፡፡

አስቻለው ከበደ አበበ

ሜትሮ ቫንኩቨር ካናዳ

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ሞቡቱ ሴሴሴኮ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share