September 9, 2023
19 mins read

እናንተዬ ፦ ዉሸት ይጋባልን ወይንስ ይወረሳል ?? (እውነቱ ቢሆን)

Abiy Ahmed Shine OLF 1

ወያኔ በቅዠት የተፈጠረ፣ እየቃዠ የሚኖርና በመጨረሻም ምንም ነገር ሳይሳካለት ቃዥቶ የሚጠፋ ስብስብ ነው፡፡ በአምሳሉ መናጆወቹን ፈጠረ፡  ኢህዴን ቆይቶም ብአደን አሁን ደግሞ የአማራ ብልጽግና ብሎ የሰየመውን የሆዳሞች ስብስብ የአማራ ክልል ብሎ በሰየመው ክልል ውስጥ አደራጀ፡፡ ኦህዴድ አሁን የኦሮሞ ብልጽግና የተባለውን የመንጋወች ስብስብ ኦሮምያ ብሎ በሰየመው ክልልና እንደዚሁም ደቡብ ብሎ በሰየመው ክልል ውስጥም  የደቡብ ህዝቦች ስብስብ የሚባሉ ድርጅቶችን ፈጠረ፡፤ ወያኔ እነዚህን  ድርጆቶች ፈጥሮና ኢህአደግ በሚል ስም ሰይሞ በራሱ ቀመር ለራሱ አላማ ከላይ ሆኖ 27 አመት ሙሉ አሾራቸው፡፡ ድፍን 27 አመት ሙሉ የኢትዮጵያ ህዝብ አለቀሰ፡፡ አዘነ፡፤ ተጎዳ፡፡ በይበልጥም “”ጠላት” ተብሎ በወያኔ ማኒፌስቶ ሳይቀር የተጻፈው የአማራ ህዝብ እጅግ ተጎዳ፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡

ይህ አጭር ጽሁፍ አላማው ስለኢህአደግ ቁጥር አንድና አሁን ብልጽግና ፓርቲ ነኝ ስለሚለውና በማንኛውም መመዘኛ ከቁጥር አንድ ኢህአደግ እጅግ ስለከፋውና በጣም ስለከፋው ስለ ቁጥር ሁለት ኢህአደግ (ብልጽግና) ለመተነተን አይደለም፡፡

ስማቸውን ቢቀያይሩትም ግብራቸው ተመሳሳይ ነው፡፤ ሁለቱም ስብስቦች ጸረ ሰውና ጸረ አገር ናቸው፡፡ የተጋጩትና ህዝቡን ጦርነት ውስጥ አስገብተው ሚሊዮኖች እንዲያልቁ ያደረጉት በስልጣን ኮርቻው ላይ ማን ይቀመጥ በሚለው ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፤  የትም አለም ስልጣን የሚመነጨው ከ”አሸናፊነት” ነው፡፡ በበሰሉትና በሰለጠኑት አገሮች የስልጣን ምንጭ በምርጫ ውድድሮች አሸናፊ በመሆን ይገኛል፡፡ በእኛ አገር አይነቱ ተጨባጭ ሁኔታ ደግሞ ከጠመንጃ አፈሙዝ ነው ስልጣን የሚመነጨው፡፡

ለዚህም ነው ፋኖ አሁን ከኦሮሙማ ወራሪ ጦር ጋር  ተዋግቶ ክልሉን ነጻ ካደረገ በኋላ በአገር ደረጃ ስልጣን ላይ ያለውን የኦሮሙማ  አገዛዝ በማስወገድ የሌሎችን ወንድም  ኢ ዮጵያዊያንን ስብስብ የያዘ የሽግግር ስርእት ተመስርቶ አገሪቱ በመላው ዜጎቿ  ነጻ ተሳትፎና ይሁንታ የሚመረጥ ህዝባዊ ፣ ፌደራላዊና ሉአላዊ መንግስት እንዲመሰረት ለማስቻል አሁን በክልል ደረጃ  ለስር ነቀል የስርአት ለውጥ እየተዋደቀ ያለው፡፡

ይህ ሀቅ መሬት ላይ የሚታይና የሚዳሰስ “እውነት” ሆኖ ሳለ ከላይ እሰከታች ያሉት የወያኔና የኦሮሙማ ባለስልጣናት የሚያነሷቸው “”ሙሉውን ውሸቶች የተሞሉባቸው”” አስቂኝም አስገራሚም የሆኑ ጉዳዮች እየበዙና አንዱ ውሸታም ባለስልጣን ተብዬ ከሌላው ውሸታም ባለስልጣን ተብዬ የማይሻልበትና ዉሸቶቻቸው በትንሹም ቢሆን  ወደ እውነትነት የማይቀራረቡበት ሁኔታ እየበዛ ሄዶ መቆሚያ ያጣ ስለሆነ ህዝቡ ‘እውነትም ውሸት ይጋባልን ወይንስ ይወረሳል?’ ብሎ እንዲጠይቅ አስገድዶታል፡፡

ስለሆነም ይህችም አጭር መጣጥፍ በትንሹም ቢሆን በ””ውሸታምነት ተጋቦሽ/ውርስ””  ላይ እንዲታተኩር ተደርጋለች፡፡

በአብዛኛው ለአንድ ሰው ውሸታምነት ዋና ምክንያቶች ውስጡ ያሉት የሰውየው  ከንቱ ምኞትና ግብዝ ማንነት ናቸው፡፤

ወያኔ ምኞቷ የነበረው እስከቻለች ድረስ ኢትዮጵያን አተርማምሳ መግዛት ነበር፡  አይቻሌው ጊዜ ሲደርስም ለም የሆኑ የወልቃይትንና የራያን  የአማራ መሬቶች በትግራይ ስር በማድረግ ታላቋን ትግራይን መስርቶ ትልቅ አገር ለመሆን ነበር፡፡ ብዙ ዝርዝር ቢኖረውም  በአጭሩ ይህ እስካሁን አልተሳካም፡፡ ኦሮሙማም እንዲሁ በዙሪያው ያሉ የሌሎች ክልሎችን መሬቶች ወረዳወችና ዞኖች እያፈራረሰ ወደ ኦሮምያ በማስገባት ጭምር  በመጠቅለል (በመዋጥ)ታላቋን ኦሮሚያን መስርቶ ትልቅ የኦሮሞ አገር ለመሆን ነበር፡፤  ብዙ ዝርዝር ቢኖረውም  በአጭሩ ይህ እስካሁን አልተሳካም፡፡ የሁለቱም አሽከር የሆነው ትርፍ አንጀቱ የብአዴን ስብስብስም ”ሀ” ብሎ በወያኔ ተጠፍጥፎ ሲሰራ፣ አመሰራረቱ፣ አወቃቀሩና የተፈጠረበት አላማው ሰፊውንና ባለ ትልቅ ታሪክ ባለቤት የሆነውን የአማራ ህዝብ አዋርዶና ተጎጅ አድርጎ  ለመጣው ጌታ ሁሉ ታማኝ አሽከርነቱን ማስቀጠል ነበር፡፡ ብዙ ዝርዝር ቢኖረውም በአጭሩ “አመሰራረቱ” አማራዊ ያልሆነው ብአደን ለመጣው ጌታ ሁሉ አሽከር ሆኖ እንዲሁ ሊቀጥል አልቻለም፡፡

127 ሚሊዮኑ የኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህ ሁሉ ድርጊቶች ባለፉት 32 አመታት ለመፈጸማቸው ምስክር ነው፡ህዝቡ ሁሉንም አይቶታል;፡፡ ሁሉንም ስምቶታል፡፡ ሁሉንም ኖሮታል፡  ታዲያ በእነዚህ ሁሉ ሂደቶች ውስጥ እጅግ አስቂኝም አሳፋሪም የሆኑ የተጋቦሽ ዉሸቶችን ህዝቡ ቢያውቃቸውም፣ ቢታዘባቸውም ለታሪክ ተመዝግበው እንዲያዙ ማድረጉ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፤

የወያኔን ቁና ሙሉ ውሸቶችንና በስልጠና የተወሰዱ እስከሚመስሉ ድረስ የተደረጉ “”መቀደዶችን፣ መበጥረቆችን”  እንደዚሁም ከወያኔ በብዙ እጥፍ በባሰ ደረጃ  የኦሮሙማን ውሸቶች በተለይም የመሪውን የአብይ አህመድን  ቀደዳወች ወደፊት ሰፋ አድርጌ እምለስበታለሁ፡፡ ለዛሬው ዉሸት ከተጋባባቸው የወያኔ ክንፎች ውስጥ አንዱ የሆነው የትምህርት ቢሮው በቅርቡ የሰጠውን አንድ  ውሸት ብቻ ልጥቀስላችህ፡፡

የትግራይ የትምህርት ቢሮ ለ2016 የትምህርት ዘመን ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮን ተማሪወችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ በትንሹ 4 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ቁሳቁሶች ያስፈልጋሉ ብሏል፡፤ ቀጥሎም 7 ሚሊዮን ከሚሆነው የትግራይ ህዝብ ውስጥ “”ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮኑ ተማሪ ነው”” ብሏል፡፡  ይህንን ቁጥር ምን እንበለው?? ወያኔ በጦርነቱ ከአንድ ሚሊዮን ያላነሰ ወጣቶችን አስበልቶ አብይ አህመድ ጉያ ውስጥ በመወሸቅ “’ ወልቃይትንና ራያን በአንቀልባ”” እያለ ነው፡፡  ከእልቂቱ በኋላ አሁን ያለው የትግራይ ህዝብ 6 ሚሊዮንወይንም 6 ሚሊዮን ተኪል ነው ብንል ከ6 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ “”ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮኑ ወይንም  37 እስከ 40 በመቶው ህዝቡ ተማሪ ነው ማለት ነው፡፡  ይህ ቁጥር ከጠቅላላው ህዝብ ቁጥር 40 በመቶ ይደርሳል ማለት ነው፡፡

በአለም ላይ 40 በመቶ ቀርቶ የህዝቡ ቁጥር 30 በመቶ ተማሪ የሆነበት አገር የትኛው አገር ነው?? እጅግ ፈገግ ያደርጋል፡፡

እስኪ ቆም ብለን እናስብና የትኞቹ አገሮች ናቸው በአለም ላይ ከህዝቦቻቸው ውስጥ 20 በመቶ ወይንም  30 በመቶ ወይንም 40 በመቶ ተማሪ የሆነው? በሁሉም መመዘኛወች  ለትምህርት አመቺ በሆነችው በአሜሪካ ውስጥ ከ334 ሚሊዮን የህዝብ ብዛት ውስጥ የተማሪው ቁጥር በመቶኛ ሲሰላ  23 በመቶው ወይንም በቁጥር 74 ሚሊዮን ብቻ ነው፡፡  እንደ ትምህርት ቢሮው ሪፖርት በምናውቃት ትግራይ ግን ሁለት ነጥብ አራት ሚሊዮኑ ተማሪ ነው፡፡ አያሳፍርምን??

እናንተ ህዬ፦ ውሸት ተጋቦሽ ነው ወይንስ ይወረሳል?? ወይንም በደም ይተላለፋል??? ወይንም….ሌላ ሌላ???

ይህንን ያልኩበት ምክንያት ለመቁጠር የሚያታክቱ አያሌ የወያኔ ውሸቶች ለታሪክና ለማስረጃነት በሰነድ ተሰድረው ስላሉ ነው፡  የኦሮሙማ የውሸት ልክ፣ አይነትና መጠንማ አይነሳ፡፤ የወያኔን ያስንቃል፡፡ ልክ በሌለው ዘረፋ ታጅቦ የሚነዛው የኦሮሙማ ማጭበርበርና ማጨናበር ለጆሮ ይከብዳል፡፡ ለአይንም; ይቀፋል፡፤

ከስቃይና ሞት ተርፎ ወደፊት አገሪቱን ለሚረከበው ትውልድ ትምህርት ይሆን ዘንደ ሁሉም  መረጃ ተሰድሮ ከተያዘበት የመረጃ ቋት እየተዘረገፈ ወደፊት ይዘገባል፡፡ ወያኔና  ኦሮሙማ  ሁለቱም በጸረ አማራነት የሰከሩና በኢትዮጵያ የአገርነት ታሪክ ውስጥ የአፍራሽነት ተል እኮ ያላቸው ቢሆንም በምንም መመዘኛና በየትኛውም መስፈርት ወያኔ በ27 አመት ቆይታው ያደረሰው ጥፋት ኦሮሙማ በ5 አመት እድሜው ያደረሰውን ያህል ጉዳት፣ እልቂት፣ ተረኝነት፣ ዘረኝነትና፣ ምንቸገረኝነትን አላሳየም፡፡ ወያኔ ቢያንስ በዚህን ያህል መጠንና ማናለብኝነት ህዝብን በማናቅ በይፋ አላደረገውም፡፡

ነውር ሲደመር ዉሎ ሲደመር ቢያድር እንደ መንጋው የኦሮሙማ ስብስብ  ነውረኛ በአለም ላይ አይገኝም፡፡ለነገሩ መንጋው ኦሮሙማ ነውር መሆኑንስ ያውቁት ይሆን??

ብዙወቹ ኦሮሙማወች  ከከብቶች የማይሻሉ ወላጆቻቸው ከብቶቻቸውን ሸጠው አስኮላ ልከው ያስተምሯቸው ከብቶች ናቸው፡፡ [ኦሮሙማ ስንል የኦሮሞ ህዝብን ሳይሆን የኦሮሞ የሁሉም የባላይነትንና የሁሉ ኬኛ አመለካከትን የሚከተል እሳቤ ፟ንወይንም አይዶሎጂን ማለታችን ነው፡፡]

ኦሮሙማወች እነርሱ እንደሚሉት 60 አመት በትግል? አለም ውስጥ ቆይተው በታሪክ አጋጣሚ አንዴ የስልጣን ማማ ላይ ቢወጡ ምርኮኛ የነበረን 50 አለቃ ሰው አምጥተው በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ እጅግ ብዙ ጀብዱ ለሰሩና ታዋቂና ምርጥ ወታደራዊ መሪወች ተሰጥቶ የማያውቀውን የፊልድ ማርሻልነት ማእረግ ለምርኮኛው በርሀኑ ጁላ ሰጡት፡፡

ይህ ድርጊት በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ የፊልድ ማርሻልነት ማእረግን “”ማን  መቼ ለማን ሰጠ”” የሚል የታሪክ ሽሚያ መሆኑ ነው፡፡ ድርጊቱ ብቻውን ኦሮሙማወች ምን ያህል ርካሾች እንደሆኑም በቂ ማሳያ ነው፡፡

የሁለቱን ስብስቦች መሪወችም ስናነጻጽር የዘረኝነት መርዝን በመላዋ ኢትዮጵያ የዘራው መለስ ዜናዊ  አብይ አህመድን ሽህ ጊዜ ይበልጠዋል፡፡ መለስ ከአብይ ይሻላል ብቻም ሳይሆን ፍጹም ልሙጥ፣ እጅግ አሳፍሪና ባዶ ጭንቅላት ይዞ በማታለል፣ በመዋሸትና በማጭበርበር ወደርየለሽ የሆነውን በህዝብ መቶ በመቶ የተተፋውን አብይ አህመድን መለስ ዜናዊ  ሽህ ጊዜ ጠፍጥፎ እያፈራረሰ መላልሶ ይሰራዋል ፡፡

መለስ ዜናዊ እጅግ ብዙ ስህተቶችን ሳያውቅ ሳይሆን እያወቀ ሆን ብሎ የሰራ ሴረኛ፣ ዘረኛና እብሪተኛ  መሪ የነበረ ቢሆንም አብይ አህመድ ግን በአንድ ቃል ‘መርህ የለሽ’ ሰው ነው፡፤  ስበእናው ከሙሉ ሰው በጣም የወረደ ነው፡፡ ከውሸታምነቱና ከቀዳዳነቱ አንጻር አብይ አህመድን በሁለት በሶስት ወይንም  በአራት ሰወች መንዝሮ ማየት ይቻላል፡፤ ነገር ግን ሁሉንም አብይ አህመዶች አንድ የሚያደርጋቸው ሁሉም እውቀትና ነውር የለሽ መሆናቸው ነው፡፤ ይህ ይበቃል ስለእርሱ ማንነትና የስብአና ደረጃ ፡፡

በአገራችን ኢትዮጵያ ይህ ሁሉ ድርጊት የብዙ ንጹሀንን ህይወት ያስከፈለና ጉስቁልናን ያስከተለ ቢሆንም ማለፉ አይቀርምና ያልፋል፡  እኔ አገራችን እንደዚህ ታርዛ፣ ተሰቃይታ፣ ተጎሳቁላ አትቀርም የሚል ተስፋ አለኝ፡፡ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ  የሰው ፍጡር በመሆኑ፣ ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ተከብሮ በሰላም የትም ሰርቶ ህግ አክብሮና ነጻነቱ ተከብሮለት በእኩልነትና በነጻነት የሚኖርባት ኢትዮጵያ እውን ትሆናለች የሚል ተስፋ አለኝ፡፡ ዞሮ ዞሮ መጨረሻ ላይ የሚሆነውም ይሄው ነው፡፡ በዚህ አይነቱ ችግር ውስጥ ብዙ አገሮች ያለፉ ቢሆንም የእኛው ግን ድንቁርና፣ ምቀኝነት፣ ኋላቀርነት..ወዘተ ተጨማምሮበት  እጅግ በጣም ብዙ ዋጋ አስከፍሏል፡፤ አሁንም እያስከፈለ ነው፡፡ መሪወቻችን ግን ከበፊቱ መሪወቻቸው ተምረውም ይሆን መዋሸቱ ተጋብቶባቸው፣ ወይንም ውርስ ሆኖባቸው፣ ወይንም  የስልጠና ዉጤት ሆኖባቸው፣ ወይንም “”ራሳቸው ዉሸቶች ሆነው”” አሁንም ይዋሹናል፡፡

አሁንም እኛ ሞተን፣ አሁንም እኛ ተርበን፣ አሁንም እኛ ሰላም አጥተን፣ እነርሱ በተቃራኒው ቆመው  ከእውነቱ ርቀው፣ ከሀቁ  ተደብቀው መሬት ላይ ያለውን  እውነታ ክደው አሁንም  ሙልጭ አድርገው ይዋሹናል፡፡

እናንተዬ፦ ውሸት ይጋባልን ወይንስ ይወረሳል???

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከቴዎድሮስ ሐይሌ ትግል ዘርፈ ብዙ ጎኖች አሉት:: ዲፕሎማሲ ሚድያ የፖለቲካ ; ካድሬዎች ; ወታደራዊ ባለሙያዎች ;የሕዝብ አደረጃጀት እና ሌሎችም ተጏዳኝ ዘርፎችን እና ሌላም ብዙ ተቋማዊ ባህሪያት እንደ ትግሉ ጸባይና ሁኔታ ሊያካትት ይችላል::

የአማራ ሕዝባዊ ድርጅት ያደረገው ውይይት ወይስ ድርድር?

January 27, 2025
ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)  ጥር 19፣ 2017(January 27, 2025) ሰሞኑን እስክንድር ነጋ “እመራዋለሁ የሚለውን የፋኖ ክንፍ” በመወከል ከአቢይ አህመድ አገዛዝ ጋር፣ እሱ እንደሚለው ውይይት፣ በመሰረቱ ድርድር እንዳደረገ በተለይም እነ ሀብታሙ አያሌው በሚቆጣጠሩት የኢትዮጵያ 360 ዲግሪ ሚዲያ ሰምተናል። ከመንግስት ጋር

እስክንድር ነጋ በታዛቢዎች አማካይነት ከአቢይ አህመድ ጋር የሚያደርገው ድርድር የአማራውን ህዝብ የተሟላ ነፃነት የሚያጎናፅፈው ወይስ ለዝንተ-ዓለም ኋላ ቀር ሆኖና ኑሮው ጨልሞበት እንዲቀር የሚያደርገው ?

ትግላችንን ለዳግም ባርነት ለሚያመቻቹን የብልጽግና እሳቤ አራማጆች አሳልፈን አንሰጥም!!! ቀን፦ ጥር 18/2017 ዓ.ም ትግላችን የኅልውና፣ የፍትሕ፣ የነጻነት፣ የሰብዓዊ ክብር ሆኖ እያለ ከፋፋይነት፣ ብልጣብልጥነት፣ አወናባጅነት፣ ከምንም በላይ በሕዝባችን ላይ የፖለቲካ ቁማርተኝነት እሳቤዎችን ከጀርባቸው

በወቅታዊ ጉዳይ ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መግለጫ

January 26, 2025 ጠገናው ጎሹ ከቅኝ አገዛዝ (colonial rule) ነፃ መሆንን ከማወጅ ያለፈ የውስጥ ነፃነት ፣እኩልነት፣ ፍትህ እና እደገት/ልማት እውን ማድረግ ባለመቻል ምክንያት በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም የኋላ ቀርነት እና ለመግለፅ

አህጉራችን እና እኛ

ከሰሞኑ ታዛቢዎች በተገኙበት ከመንግስት ጋር ውይይት እንዳደረገ እና ለድርድር ዝግጁ እንደሆነ የገለፀው በእስክንድር ነጋ የሚመራው የፋኖ ክንፍ ድርድሩ በውጭ ሀገራት እንዲሆን እየጠየቀ መሆኑ ታውቋል። የመሠረት ሚድያ ምንጮች እንደተናገሩት ታጣቂ ክንፉ ድርድሩ በአውሮፓ

በእሰክንድር ነጋ የሚመራው ፋኖ’ ከመንግስት ጋር ለመደራደር ተዘጋጅቷል

January 26, 2025
Go toTop