በአለማችን ላይ እንደሰውልጅ በገዛ ፍጡሩ ላይየሚጨክን አውሬ የለም እስከዛሬ የምንሰማቸው አሰቃቂ እና አስነዋሪ በደሎች አንዱ ሰብአዊ ፍጡር በሌላው ላይ የፈፀማቸው ናቸው፡፡እንደዚህ ያሉ ክፉ ተግባራት በፍትህ ሽፋን በዚህ ጊዜ በአደባባይ ሲፈፀሙ ማየት ደግሞ እጅጉን ያማል፡፡
ዘመኑን የማይመጥነውና እና የሚያደርገውን ነገርበአግባቡ ማከናወን የተሳነው በመርማሪነት ማዕረግ ማዕከላዊ የሚገኙት ገራፊዎቻችን በማኅሌት ፋንታሁን እና ጓደኞቻችን ላይ ራሳቸውማስረጃ ማቅረብ ባልቻሉበት ጉዳይ ላይ አስገድደው ‹‹አመፅ ላነሳሳ›› ነበር የሚል ቃል አንዲሰጡ ሲገደዱ ነበር ፡፡ ማሂም በዚህ “ምርመራ” ሂደት አመፅ አነሳሳችተብላ አልፋለች፡፡ ከዱላቸው ውጪ አመጽ ተነሳሳ ብለው ብለው የሚያቀርቡትፅሁፍ ባይኖራቸውም ዜጎች ተገደው ያላደረግነው አደረግን ካሉ ገራፊዎችን ለመጠየቅ ጉልበትና አቅም የሌለው ፍርድ ቤታችን የፍትህስርአቱን ፍርደ ገምድልነቱን ለማስመስከር ከበቂ በላይ ነው፡፡
እያደር አዲስ የሚሆንብን ወለፈንዲው የአገራችንየኅሊና እስረኞች ጉዳይ ሁሉም ንፅኅናቸውን የሚያረጋግጥላቸው የፍትሕ ሥርዓት ባይኖርም ከተጠረጠሩበት ጊዜ ጀምሮ አሸባሪዎች ናቸው፤ማስረጃ ባይቀርብባቸውም አንዴ ተብለዋልና ንፁህ ሆነው እያለ ንፁህነታቸውን ማስመክር ይጠበቅባቸዋል፡፡ አሁን አሁንማ አሰራሩ የማረጋገጥሸክሙን ከከሳሽ ላይ አንስቶ ተጠርጣሪዎቸን ንጹህነታችሁን አረጋግጡ ይላል፡፡ ብዙዎች የፍርድ ቤት ክርክርን የሚያደርጉት ፍትሕንእናገኛለን በሚል ሳይሆን የሚደረገውን ድርጊት ሕዝብ እንዲያውቀው ሥርዓቱን ሁሉም እንዲረዳው ፤ ምናልባት የተጠራጠሩዋቸው ካሉ አንዲያውቁትእድል ለመፍጠርና ይህ እንደማይገባን ለማሳየት አጋጣሚውን መጠቀማቸው ነው፤ እንጂማ በግፍ እንደሚፈረድባቸው እያወቁ ፍርድ ቤቱንም ሆነ አሰራሩን እውቅና መስጠት አምሯቸው አይደለም፡፡ ትሁቱናትኤል ፈለቀ እንዳለው እያደረጉ ያሉት “Judicial activism” ነው፡፡
የምርመራ ሂደቱ ደጋግመው ቢወሩ አንደአዲስ የሚያስገርሙብዙ ጉዶች አሉት ፡፡ ጥፋት አለብህ ብሎ ያሰረህ መርማሪ ‹‹ጥፋቴ ምንድን ነው ትላለህ?›› ብሎ ይጠይቅሃል፡፡ ‹‹ሕገ-መንግስቱተከብሮ እያለ ሕገ-መንግስቱ ይከበር በማለቴ ጥፋተኛ ነኝ›› በል ብሎ ፍዳህን ያበላህ መርማሪ መልሶ ቢሮ አስጠርቶህ ስለሕግ አስጠናኝየቤት ሥራም ሥራልኝ ይልሃል አንተን ‹‹አሸባሪውን›› ከፃፍነው፣ ስንጦምረው ከኖርነው ውጪ ሌላ አላማካላገኘንባችሁ ያሉ ገራፊዎቻችን ‹‹አላማችሁ ምንድነው?›› በተደጋጋሚ የሚያነሱት 24 ሰአት ሙሉ የሚደጋገም ጥያቄያቸው ነበር፡፡ ያላለቀው ግን ያለፈውን ምርመራ ዛሬ ላይ ማሂ ስትቀልድበት እንዲህየምትል ይመስለኛል
አላማችሁ ምን ነበር?
ዓላማችን
· የማዕከላዊ ምርመራን በመጎብኘት የምርመራ ሂደቱን ምጡቅነትእና ዘመናዊነት መታዘብ፡፡
· ክስ ሲመሰረት እንዴት በተልከሰከሰመልኩ እንደሆነ ለዓለም ማሳየት፡፡
· አቃቤ ሕግ እና መርማሪ እንዲሁምዳኛ የጆሮ ጉትቻ እና የአንገት ሃብል መሆናቸውን ማሳየት፡፡
· የሽበር አዋጁ እንዴትabuse እንደሚደረግ በተግባር ማረጋገጥ (አንድ ሰው ከሱቅ ዳቦ ሲገዛ ቢገኝ ዳቦውን በልተህ የሽብር ተግባር ለመፈፀም ልታስብስለነበር ተብሎ የፀረ ሽብር አዋጁ ተጠቅሶ መከሰሰስ እንደሚችል ማሳየት እና ለዚህ ዋናው እና አስፈላጊው ነገር የመንግስት ለመክሰስየማሰብ ፍላጎት መኖር ብቻውን በቂ መሆኑን ማሳየት ነው)
ግባችን ደግሞ፡- የፍትሕ ሚኒስቴር እንጂ ፍትሕእንደሌለ ማሳየት ነው፡፡
በተለያየ አጋጣሚ ሰዎች በራሳቸው ጥፋት ሲቀየሙንአልያም ሲያኮርፉን “ጥፋቱ የእኔ ይሆን?” ከሚል በተለየ አንግል ለማየት እና ለመረዳት ብዙዎቻችን ሞክረን እናውቃለን፤ በአገራችንሃሳብን በነፃነት መግለፅ መንግስትን እንደ መዳፈር፣ መብትን መጠየቅ አሸባሪ የሚል ካባ የሚያስደርብ ኖርም ከሆነ ሰነባብቷል፤ ብዙዎችሃሳብህን በመግለፅህ የሚደርስብንን ነገር በመስጋት ያንን ስጋት የፈጠረውን ስርዓት ከመታገል ይልቅ የአቅማቸውን የሚሞክሩትን ማስፈራራትየእለት ተዕለት ተግባራችን ሆኗል፡፡
ይህ በአንባገነን ሥርዓት ውስጥ ዜጎች ላይ የተጫነውየፍርሃት ቀንበር ራስን ከማስገዛት አልፎ ሌሎችንም ዝም ለማሰኘት እርስ በርሳችን የሸበበን የማይገባንን ሥርዓት ተሸክምን ያለአግባብዜጎች ላይ በደል ሲደርስ ለምን ብለን ከመጠየቅ ይልቅ ‹‹አርፈው አይቀመጡም ነበር›› የሚል በጭለማ ውስጥ ያለ የውሸት እውነትነው፡፡
ማሂን በዞን ዘጠኝ በነበረን ጓደኝነት የራስዋ አበርክቶ ያላት ለብዙ እንስቶቻችንምሳሌ መሆን የምትችል ብሩህ ወጣት ናት ማሂን እኔ ሳውቃት ስልክ ደውላ አዲስ መፅሃፍ ወጥቷል ናና ሸማምት፣ የመፅሃፍት ምረቃ አለለምን አትመጣም፤ እና ሌሎች ይህን መሰል አስተያየቶችን ነበር የምትነግረኝ ፡። የስነጽሁፍ ፍቅሯንም ከራሷ አልፎ ለእኔም ታጋራነበር፡፡
ስርአቱ ስርኣት አልባ ነው፣ ዜጎችን ለማሸማቀቅ በዝምታ እንዲገዙ ለማድረግ የሚታትረውስርኣት የሚሸማቀቁ እና ዝምታን የሚመርጡ እንደሚኖሩ ሁሉ የሕግ የበላይነት የሚባል ነገር እንደሌለ የሚታያቸው ስርዓቱን ለመሞገትዴሞክራሲያዊ መንገድ አማራጭ እንደማይሆን የሚገለጥላቸው ብዙ ዜጎችም መፈጠራቸውም ሊስቱት አይገባም፤ ሥርዓት አልበኛውን ስርዓትመካሪ የለውም በዘር እና በጥቅማጥቅም እና የፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነው የተያዙትም የስርኣቱን ስርዓት አልበኝነት እና ሕገ-ወጥነትን ጀስቲፋይ ሊያደርጉት ይዳዳቸዋል፡፡
የማይቻላቸውን ለቻልሽው ማሂ ይህ የማያልፍ የሚመስለው ክፉ ቀን ቶሎ እንዲያልፍምኞቴ ነው፤ በሰፊው እስርቤትም እስክንገናኝ እናፍቃለሁ፡፡
መልካም ልደት እንኳንም ተወለድሽ፡፡