ዲያስፓራ የሚለው ቃል ከግሪክ የፈለቀ ቃል ሲሆን ቃሉ ከመነሻው የተሰጠው ለእስራኤላውያን ስደተኞች ነው። እስራኤላውያን ከአገራቸው በተለያየ ምክንያቶች መስደዳቸው በአምላክ ፍቃድ፣ ምክንያታዊ በሆነ ህሳቦትና ቀመር እንደነበረ ቃሉ ያመለክታል። ይህ ዲያስፓራ የሚለው ቃል ለእስራኤላውያን መግለጫቸው ሆኖ ሲያገለግል አንድ ቀን ወደ ተስፋዋ ምድራቸው ተመልሰው ምድረ እስራኤልን የከንሃን ምድር ያደርጓታል በሚል ትዕንቢታዊ መንፈስ ስያሜው የተሰጣቸው እንደሆነ እውነታውና ታሪኩ ያሳያል። የአምላክ ፍቃድ በሙሴ መሪነት ልጆቹን እስራኤላውያን ለቃሉ አልገዛ ስላሉ እንዲሰደድ አደረገ። የአይሁዳዊያን በአለም መፍለስ የኦሪት ሃይማኖት ተስፋፍቶና ገኖ ከዚያም የተስፋዋ ምድር እስራሄል እንደገና በልጆቿ ዲያስፓራዎች መመለስ የከንሃን ምድር ትሆናለች የሚል ፅንሰ ሃሳብ ምንነት ዕድምታ እንዳለው ከክዋኔው እንረዳለን። ይህ ትንቢትም እየሆነ ፣ እያየነውም ነው።
ይህን ፅንሰ ሃሳብ በእጭሩ ካስቀመጥኩ በኋላ እኛ ኢትዮጵያዊያን የመጀመሪያዎቹ ስደተኞችን ተቀባዮች ሁነን አሁን ግን በስደተኝነት ብዛት አለምን ማጨናነቃችን ግራ ሞትን የሚፈጥርና ግራ የሚያጋባ ክስተት ነው።
ሰሞኑን ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከላይ የተዘረዘረውን የእስራኤሎችን ተሞክሮና የአምላክ ጥሪ ተንተርሰው በውጭ ሃገር የተሰራጨውን ኢትዮጵያውያንንና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ያንን “ወደ ቃል ኪዳን ሃገራችሁ ግቡ”’ ብለው ያወጁት።
ነገር ግን በዚህ ጥሪ በተቃርኖ በለንደን የተፈጠረው ወከባ ፣ መተረማመስ፣መካካድና መወነጃጀል ፣ መሰዳደብ ወ.ዘ.ተ አጃኢብ የሚያስኝ ነበር።
ከዚህ ባለፈ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሃገር ቤት እንዲገቡ ጥሪ ሲቀርብላቸው ትኩረታቸው ኢትዮጵያዊነትን የአማከለ መሆን ሲገባው ወደ ብሄር ኮሮጃቸው ለመሸጎጥ ተፍ ተፍ ማለታቸው ያለፈው ስርዓት አይደለም በሃገር ቤት የሚኖረውን ዜጋ ስልጡን ነው በሚባለው ሃገራት ንዋሪ የሆኑትን ዲያስፓራዎች ተፅህኖ እንዳሳደረባቸው ፍንትው አርጎ ያሳያል።
ወደዋናው አተታና ክሳቴ ከማግባታችን በፊት የሃገራችንን መልካምና አንቱ የተባሉ ቱፊታዊ ንግግሮችን መቸቶችን እንጠቃቅስ።ከልቤ እምንወደው ፣ ፈትፍቶ ፣ አጉርሶ ያሳደገን ገበሬው የሃገር ሰው ለሴት ልጆች ሲቀኝና ሲያቆለጳጵሳቸው እንዲህ ብሎ ነው ”ሴት ልጅ ሃገር ናት፣ እናት ናት ፣ ሚስት ናትና እህት ናት” ይላታል።
ይህ አባባል በለንደኖቹ “ዲያስፓራ “ ለምዶብኝ ነው ይቅርታ “ በነ-ኬኛ” ክልላዊ መስተዳድር ውስጥ አይሰራም። ለምን ቢባል ሃገርንና ህዝብን ለገንዘብ ሲሉ ለመሸጥና ለመለወጥ ወደ ኋላ የማይሉ ለእናት፣ ለእህትና ለሚስት መቆርቆርና ማክበር አርማቸው ነው።
ከዚህ ዲያስፓራ ከሚባል ክልል ውስጥ ምትሃታዊ የሆነ የከፋፍልህ አባላውና አተራምሰው የሚባል /Machevilian policy”/ አለ ። እሱም “የማይመችህና አላዘርፍህ የሚልህን ግለሰብ ወይም ቡድን በወረሱት የቆረጣ የማሸማቀቂያ ስልት መሰረት ባገኘህው የመገናኛ ብዙሃን ተጠቅመህ እየከፋፈልክ አጥቃው ፣ አሸማቀው ፣ አፉን እዲዘጋ አርገውና መድረሻ አሳጣው” የሚል የፀደቀ የመተዳደሪያ ደንብ አላቸው።
እኔ እኮ የሚገረመኝ አንዳንዴ በተመስጦ ሁኘ ሳሰላስለው “ይህ አይነት ቅጥ ያጣ ባህሪና ብልግና ከየት መጣ” ብየ የማስብበት ቀናቶች አሉ። እኛም ስናድግ ችግር ካለ “ፊት ለፊት ተጋፍጦ እውነትን ከማወጣጣትና “ሂስና ግለሂስ” እንደሚሉት በግልፅ ተነጋግግሮ ከመተራረም ባለፈ እንዲህ ጎልቶ የሰውን ሰብአዊ ማንነት አልቦ ማድረግ ባለፈው ትውልድ አይታሰብም።
አንዳንዴ በዚህ ወልቀ-ሰባዊነት ማንነት በተለከፉ /ዲያስፓራዎች/ ባህሪ ዙሪያ አብሮ በመዋል የምርምር ስልት ስንደርስበት ከቅደመ አያቶቻቸው ተሸክመው ያመጡብን ኢትዮጵያዊ ፣ ኢትዮጵያዊ የማይሸት የደም ውርስ አለባቸው ለማለት ያስገድዳል።
ነገርን ነገር ያነሳዋልና “ሕወሃት” “መሃት” ቢባል ይሻላል ሆዱ በጥጋብ ተነፍቶና የማሰቢያው ላይኛው አካሉ በመጠጥ ብዛት ነፍዞና ላልቶ በሽወዳ ቤተ-መንግስቱን ለተረኞቹ ያስረከበበት ኩነትናሎንዶን እንግሊዝ የሚገኘው ዐፄ ኃይለሥላሤ ለኢትዮጵያዊያኖች ይበጃል ብለውና ገዝተው ጀባ ያሉን የሳስት ፎቅ ውብ የኢምባሲ ሕንፃ ወረራ ተምሳሎታዊነት ያስደምመኛል።
ዋናው ቁም ነገር እንደ አራት ኪሎው “ ይገባዋል ጠጅ ቤት” አምቡላ ፣ አምቡላ በሚል ሽታ ካልሰነፈጠ ፣ ለነገሩ በአንድ ወቅት የኢትዮጵያን የተከበረ ባንዴራ አውርደው፣ የኦነጉን ግብፅ ያበደረቻቸውን ባንዴራ ሲሰቅሉ እነሱ “ ያ -ደበሌ” እያሉ እንደሚገቡ ጥቂቶቻችን ታይቶን ነበር። መቸም ጀሮ “የማይሰማው የለም” የሚለው ጥቅስ ከተሰቀለበት ግድግዳ ወርዶ ፣ “ ቸር አስማኝ “ የሚለው ጥቅስ ቦታውን ሊለቅ የተንጋደደበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
የእምየ የኢትዮጵያ መናገሻ፣ የአለም አቀፍ ድርጅቶች መናህሪያና የአፍሪካ ሃገራት መዲና በሆነችው አዱ ገነት ሁሉ ነገር “ኬኛ” ተብሎ አልቋል።
የሎንዶኑም ኢምባሲ “ኬኛ” ብለው “እንደ ከቡቡሽ” ከከበቡት ውሎ አድሯል። ሰሞኑን ደግሞ “ወሎ” “እራያ ኬኛ” ከማለት አልፈው “ ደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች “ ኬኛ ማለት ጅምረዋል። ወገኖቼ የ18ኛው ምዕተ ዓመት “የኦሮሞ መስፋፋት” ትብዕል “ በኬኛ ዘመቻ” ስልታዊ ውቅር ህሳቤ ተቀየረ እንዴ? መልሱን ለእናንተ እተወዋለሁ። “ ከማን ጋር ልታጣላኝ ነው” ብሏል አቤ ጉበኛ።
“ኧረ የጉድ ሃገር” እንዲሉ ላነሳው ያሰብኩትን ዋና ጉዳይ ትቼ ጉዳይ ከዚያው ዙሪያ ባያልፍም ሆድ ብሶኝ ብዙ አልኩ።
ነገሩ እንዲህ ነው ለእሁድ አጥቢያ ቅዳሜ እቤቴ ፣ ወይ ጉድ የሃገሬን የአባትና እናቴን ጎጆ አሸቀጥሬ ጥየ መጥቸ በሰው ሃገር የከተሙኩበትን ዛኒጋባ ቤቴ ማለት ነውረኝነቴን ቢያመላክትም ፣ የእጅ ስልኬ
“ ጠውጠው” የሚል ድምፅ ያሰማኛል።
ለአንድ አፍታ አይኔ ከአተኮረበት መፅሃፈ ንባብ ገታ ብየ በሞባይሌ የተላከልኝን መልዕክት ያውም በቪዲዮ የታጀበ ጉድ መስማት ጀመርኩ።
ከጅምሩ “ አበስኩ ገበርኩ” አልኩ ፣ “ሃገር ናት ፣ እናት ናት ፣ እህት ናትና ሚስት ናት” ያቆለባበስናትን ሴት ልጅ ፣ “ምንም እራሷን ከአርያም ዘር ነኝ ብላ ብታውጅ፣ ይሄን መሆን ሻትኩ ብላ ብትመኝ ፣ ተምሬ ተመራምሬ በቅርቡ ቀን ወደ ማርስ ለመንጎድ /ሻትል/ ላደርግ ህሳቤ አለኝ “ ብላ ብታወጅ መብቷ ነው፣ ያውም በሰለጠነው ዓለም።
ያም ሆኖ በወረደ ቃል መሳደቡና የዘመኑን ቴክኖሎጂ ተጠቅሞ በቪዲዮ አጅሎ ፣ አቀነባብሮና ቀጣጥሎ ማሰራጨቱ እንኳን “ ኢትዮጵያን አናድን /Defend Ethiopia/ ከሚባል መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ ቡድን ከባዕድ ጠላትም የሚጠበቅ አይመስለንም።
በቪዲዮ የተሰራጩትን የወረዱ ቃላቶች ለመናገር ባልዳዳም፣ ቢያቅለሸልሸኝም ዙሪያ ሃሳቡ ግን ሲነበነብ እንዲህ ይላል “ እንቺ ምን ቃላቱን አልገልፀውም የሴት ልጅ በኖሮ መቸገርና ቤተሰብን ለመደጎም ብላ የምትፈፅመው የስራ መስክ ነውና ፣ ምን እየሰራች አስተማሪ ነኝ የምትል ለነገሩ በስደት ምድር ማንም ይሁን ማን መጀመሪያ እግሩ የባዕድ ሃገርን እንደረገጠ የሚሰራው ያገኘውን ስራ መሆኑ እየታወቀ፣ ውብ አርጎና ተጨንቆ አምላክ በአምሳሉ የፈጠራትን የሰው ልጅነት የመልከ ገፅታ እንዳልሆነ አርጎ ማንቋሸሽ ያውም አቅፏት የሚውለውንና የሚያድረውን ውብ እርጎ ባለቤቱ የሰራትን የሴት ልጅ ገላ አውርዶ ፣ አንቋሾ ፣ ጥሎና ከማይገባው አካል ጋር አማስሎ” ማቅረብ በእውነት ይህ ድርጊት በሰማይም ይሁን በምንኖርበት ምንሃቡ ዓለም የሚያስጠይቅ ነው።
የሚገርመው የእነ-አቧራ
/ዲያስፓራ/ ጉድ እኮ ተዘርዝሮ አያልቅም ። ምድረ ኢትዮጵያን እናድን /Defined Ethiopia/ና አባይን እንገባ ብለው አብረው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሃቀኛና ታማኝ ወንድሞቻቸውን “እነ አቤልን” “ የቃየል” ተምሳሎቶች “የኢትዮጵያዊያን ገንዘብን አትበሏትም፣ አትዘረፏትም” በማለታቸው ብቻ “ አቋም የለሽ፣ የሌላ ኢትዮጵያዊ ብሄር ቋሚ ተጠሪ” እያሉ መወረፋቸው እንደ አበደ ውሻ ሁሉን ከመልከፍ ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸው፣ መላ ስብህናቸው የወረደና የማንነታቸው መገለጫ ነው። ዘይገርም የሚያሰኝ የዘመኑ የማይድን ስደት ያመጣው በሽታና ደዌ ተጥቂዎች መሆናቸውን ያሳያል።
መቼም እምየ ኢትዮጵያን በሴራ ፓለቲካ ተብትበው ከማማዋ ወደታች ሊያወርዷት ያሰቡትን እርስ በርስ እንደዚህ ቀደሞቹ መንግስታት ዘመን ሰደድን ከደርግ፣ ኢሕአፓን ከምኤሶን፣ ወያኔን ከሻቢያ አሁን ደግም ኦነግና ከኦነግ ሸኔ ጋር እርስ በርሳቸው በዓላማ አለያይታ እያተረማመሰቻቸው ትገኛለች። የኢትዮጵያ አምላክ ታላቅ ነው።
የነ ኬኛ “ኦነግ ሸኔና ኦነግ “ ቡድኖች በለንደን ኢምባሲ የፈፀሙት እርስ በርስ መፋጨትና መከዳዳት በሰሞኑ የአንድ ሚሊዮን የዲያስፓራ ጥሪና ለጥፈው ካሰራጩት የብልግና ጥግ ቪዲዮ ጋር በውስጥ አዋቂያችን በደረሰን ዘገባ መሰረት ሲጋለጥ የሚከተለውን ይመስላል። አጃይብ ነው ወገን።
የለንዶኖቹ ኦነግና ኦነግ ሸኔ በኬኛ ዘመን አመጣሽ ፍልስፍና ተጠምቀው በቅጡ ወደ እማያውቋት አድ -ገነት /አዲስ አበባ/ ለምንጎድ ሽርጉድ ይላሉ።
የኦነግ ሸኔው የለንደን የቡድን መሪ የተጎድትንና የተፈናቀሉትን ወገኖች ለመርዳት በሚል መሪ ሃሳብ ከፍ ያለ ገንዘብ በማሰባሰቡ ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዘውን ቡድን ባንዴራ አንግቦ በመምራት እንዲጓዝ በሚመለከተው አካል ታጭቶና የይሁንታ የድጋፍ ደብዳቤ ተፅፎለት ጉዞው የሰመረ ይሆንለት ዘንድ መልካም ምኞት ተችሮት ሹመቱን ይረከባል።
በዚህ የተበሳጩት፣ እንጀታቸው ያረረውና በቅናት የተንፈረፈሩት የኦነግ ጋሻ ጃግሬዎች ስልታዊ የመልሶ ማጥቃትና ይህን ጃባ የተባለ ሹመት ለማኮላሸትና ወደ እራሳቸው ለማስገባት ሴራቸውና ተንኮላቸውን ያጧጡፋሉ ፣ ይሸርባሉ። አንዳድ በባላቸው፣ በሚስታቸውና በልጆቻቸው አባት በማንነት መላሸቅ / Identity Crisis/ ምክንያት ግራ የተጋቡ አማሮች የኦነግ ቡድን አፍ ቀላጤ ሆነው አሴሩ፣ ተባባሪ ሆኑ።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተቀብለው ከእንግሊዝ የሚጓዙትን ዲያስፓራዎችን ባንዴራ አንግቦ እየመራ ሊጓዝ ኃላፊነት የተቸረው የኦነግ ሸኔ ተጠሪና ዘለዓለም የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች የጭን ገረድ መሆን ልብሱ የሆነው የኦነጉ የለንደን ጋሻ ጃግሬ ታላቅ የመሸኛና የእንኳን ደስ ያለህ ፓርቲ አዘጋጅ።
የአራት ዓመት ልምድ ብቻ ያለው የኦነግ ሸኔ የሎንደን ተጠሪ “የድመትና የአይጥ ግብዣ” ተረት ተረት አይነት እንዲሉ ግብዣውን በስነ-ልቦና ጊዚያዊ የበላይነት ስሜት የተጠመደለትን ውጥመድ አልታየው ብሎ በግብዣው ይታደማል። የለንደን የኦነግ ክንፍ ጦር ሃይል ዘመናዊ የሞባይል ማቅጃ ስናይፐሩን በድብቅ ደቅኖ ፣ መጠጥ እያስጋተ የኦነግ ሸኔውን ተወካይ ያናዘው ጀመር። ከላይ የገለፅኩትን የሴት እህቶቻችን ስብህና የሚነካ ንግግር ተናገረ ፣ በኢትዮጵያዊነት ስሜት ልባቸው የሚንቦገቦገውን የደቡብ ብሄር ፣ ብሄረሰብ፣ ሕዝቦችና የአማራ ተወካይ ተጓዦችን ስም እንዳይሆኑ እርጎ አጠፋ፣ አጎደፈ።
“አያ በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ ገደሉን ሳታይ” እንዲሉ ከነፈዘበት መንፈሱና ከስካር ቅዠቱ ባኖ በበነገታው ሞባይሉን ሲኮረኩር ያ የዘላበደው የስድብና ስብህናን የነካበት ናዳ ቪዲዮ ቅጂ በዘመናዊ ቴክኖለጂ ተቀነባብሮ አየር ላይ ውሏል።
አዳሜ ተቀባበለው ፣ ከተከበሩት አምባሳደርና ከሚመለከታቸው የአምባሳደሩ ጀሮ ጠቢ አካላት ዐይንና ጀሮ ገባ።
ከዚያ የለንደን የኦነግ ጋሻ ጃግሬ ሻጥሩና ሴራው እውን ሆኖለት የሸኔውን ተወካይ እንክትክቱን አውጥቶ ፣ የተሰጠው ባንዴራና ሹመት ተገፎ ለኦነግ ተወካዮ ሹመቱና ባንዴራውን ጀባ ተባለ ፣ የጉዞውም መሪ ተብሎ ተሰየመ። ለንደን በፓሪቲና ፌሽታ ተደበላለቀች።
“በድር በምድር” እንዲሉ የኦነግ ሸኔው የእንግሊዝ-ለንደን ተወካይ በኦነግ ክንፍ የደረሰበትን ሽፍጥ ሃገር ቤት ላለው የሸኔ ሰራዊት ቡድን አስታወቀ። ከዛም ዘለዓለሙን በሴራና በተንኮል ተኮትኩቶ ያደገው የለንደን ኦነግ ግርፍ ባዴራውን ይዞ ፣ ቡድኖችን አሰልፎ ከለንደን ኤትሮ/Hetrow/ ተነስቶ “ውሮ ወሸባየ” እያለ ቦሌ አየር ማረፊያ ደረሰ።
ከዚያም “ብድር በምድር” እንዲሉ ለወትሮዎ ለግለሰብ የዲያሰፓራ ሳይቀር የተደረገው በማርሽ የታጀበ አቀባበል ፣ የአበባ ጉንጉን ማበርከት ስነ-ስርዓት፣ የባለስልጣናት አጀባ ፣ የእንኳን መጣችሁ የአቀባበል ስነ-ስርአትና የጋዜጠኞች የቃለ-መጠየቅ ወከባ “ስንቶሽ ባዶሽ” ሆነ። በዚህ ያልታሰበና ያልተጠበቀ ኩነት አናቱ የፈለሰውና በንዴት የተንተከተከው የኦነግ የለንደን ቡድን መሪ በጭንቀት ሲታመስ ከርሞ ለአንድ ወር በሃገር ቤት ሊንፈላሰስ ያሰበው ህልም አልቦ ሁኖበት ውደ ስደት ሃገሩ ተመልሶ መጣ።
እንደ ደረሰን መረጃ መሰረት የእዕምሮ ህክምና ተደርጎለት እስከ አሁኑ ደቂቃ ድረስ ከአልጋ ላይ ተጣብቆ እንዳለ መረጃዎች ደርሰውናል። እኛ ጨካኞች አይደለንምና “እግዚአብሔር ይማርህ” እያልን የሚቀጥለውን የውጊያ ስልትህን “በአስተውሎት ፈፅም” እንላለላን።
በዚህ አጋጣሚ የእንግሊዝ አምባሳደር፣ ደንባራና ሻንጣ ያዥ ዲፕሎማቶች በዮኬ እነዚህ የከንቱ ከንቱዎች ፣ በህቶቻችንና በወንድሞቻችን የፈፀሙት ወንጀልና ስም ማጥፋት “ Defamation “ ሆነ ስሜት የሚነኩ ቃላቶች /Verbal abuse and bulling” በቀላሉ ታይቶ የማይታለፍ መሆኑን እየገለፅን፣ አስፈላጊውን ቅጣት እንዲያገኙ በኢትዮጵያ ስም እንጠይቃለን ።
በመጨረሻም “ኧረ ሰው ሰው እንሽተት” በማለት እንመክራለን።
ከእፎ ያስይሃፍር ከከንሃን ምድር- ከምድረ እንግሊዝ።