ቤቱን ለትኋን ብሎ አያቃጥልም ህመምተኛ ካልሆነ በስተቀር።
በሃገሩ ላይ የማይወዳቸው ስልሚኖሩም ሃገሩን አሳልፎ የሚሰጥም የለም፤
ጽንፈኛ ከልሆነ በስተቀር።
ተከፋይ ሆድ አደር ካልሆነ በቀር።
በውሸት ትርክት አዕምሮው የነሆለለ፤ ያሲያዙትን የማይለቅ ግን አዲስም የማይማር ካልሆነ በቀር።
“..nothing is as painful as staying stuck somewhere you don’t belong”
ሃገርን ለተውሰኑ ግለሰቦች ወይም ቡድኖች አሳልፈህ ከሰጠህ አንተ የአባቶችህ ልጅ አይደለህም። በታሪካችን እየተቀባበለ ኢትዮጵያን ለአኛ ያደረሰ ትውልድ ከውስጥና ከውጭ ጠላት ጋር ተጋፍጦ ነው፤ አልጋ ባልጋ መንገድ አልነበርም። እንደዛሬው ሁሉ ከውስጥ ባንዳዎች ከውጭ ወራሪወች ጋር የማያባራ ግጭት ያሳለፈ ተውልድ ነው። ዛሬ አንዳንዶች እንደሚያስቡት ለተውሰኑ ሰዎች አስረክቦ አልሸሽም፤ አኔ አያገባኝም አላለም፤ ቢሉ ኖሮማ ዛሬ የምንኮራባትን ነጻ ኢትዮጵያ ባላገኘናት ነበር። የመንግስትን ክፍትና ድክመት አየዘመሩ ብቻ ሃገር አንድ ሆና አትቆይም። የምትሰራው ለመንግስት አይደለም ለሃገርህ ለኢትዮጵይ እንጂ። የመንግስትን ጥፋትም ሆነ ተንኮል ትታገልዋለህ እንጂ ሃገርህን አስረክበህ አጆችህን አጣጥፈፍህ አትቀመጥም።
ክህደት ይኖራል አለም የካደችን ኢትዮጵያ አይደለችም። የከዱን የመንግስትን መንበር ይዘው የሚያሳርዱን ናችውው እንጂ ኢትዮጵያማ ክህደት የሚባል አታውቅም፤ ትናንትም ዛሬም ነገም የኛው ናት።
አዎ ቤቴን ትኋን ወረረብኝ ብለህ ቤትህን አታቃጥልም። ትኋኑን ግን ታጠፋለሕ ።
የሃገርህን የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶች ትዋጋለህ፤ ሃገርህን ለምትጠላቸው አስርክበህ ዝም አትልም።
በአንድ ሃገር ውስጥ በተወሰነ የታሪክ ወቅት የተወሳሰቡ ቅራኔውች ሊከሰቱ ይችላሉ፤ ሁሉንም ባንድ ላይ መፍታት የማይቻል ከሆነ ለቅራኔውች ቅደም ተከተል ይበጅላቸውና አንግብጋቢውን ቅራኔ በቅድሚያ መጋፈጥ አስፈላጊ ይሆናል። ይህ ማለት ሌሎች ችግር የለባቸውም የሚል ትንታኔ ስለተደረሰበት አይደለም። ዋናውንና የጎላውን ባይፈታ ጭራሽ ሌሎችንም ችግሮችን የሚፈለፍል ስለሚሆን አስቀድሞ መፍታት አስፈላጊ ስለሆነ ነው።
ዛሬ የህልውና ፈተና ውስጥ ነው ያለነው፤ አለምን ባንድ ቅርጫት ውስጥ አስገብተው እንደህል ሊዎቁን የሚፈልጉ ምዕራባውያን፤ ውስጥ ከፈጠሯቸው የጭነት ከብቶቻቸው ጋር ሆነው ሃገራችንን እየተፈታትኗት ነው። ትልቁና ከሁሉም በፊት መፈታት ያለበት ቅራኔ ይህ ነው። እርግጥ ነው ያሽግረናል ያልነው መንግስት እየተፍረከረከ ወደፊታና ወደኋል የሚዋልልበትን ሂደት እናያለን ግን የዋናውን ቅራኔ ቦት አይወስድም። ለሁሉም ጊዜ አለው ነውና የዋናውን ቅራኔ መፍትሄ ለመስጠት መተባበርንም የግድ ያደርገዋል።
ከቻይና ብዙ መማር ይቻላል፤ ጃፓን ቻይናን እያጠቃች በነበርችበት ወቅት እርስበራሳቸው ይዋጉ የነበሩት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲና ኮሚንታግ(Koumintang) ለሃገራቸው ልዕልና ሲሉ በፈርንጆች 1937 ግንባር ፈጥረዋል። የጋራ ጦራቸውን በጃፓን ላይ አሳርፈዋል። ይህ የአንድነት ግንባር (united front) የቻይናን ነጻነት አረጋግጧል። የጊዜው መሪዎች ማኦና (Mao Tsedung) ቸንግ ካይ_ሸክ(Chaing Kai-shek) ዛሬ የሉም፤ ቻይና ግን አብባ ዘሬም ህያው ናት ለብዙ ሃገሮችም ምሳሌ እየሆነች ነው። ከማይስማሙት ጋርም ቢሆን መተባበር ለትልቁ አላማ ስለሚረዳ እንጅ መሸነፍ አይደለም።
መሸነፍ ሰበብ እየፈጠሩ ሃገር ሲፈርስ ከዳር ቆሞ ማየት ነው።
መሸነፍ ኣባት ያቆያትን ሃገር መሸሽ ነው።
መሸነፍ ሊያፈርሱን ከተነሱ እብሪተኞች ጋር መንግስት ጠላሁ ብሎ መሰለፍ ነው።
“ patritism is a permenent dedication to your country…. Patritism overrules government”
የሃገር ፍቅር በወረት አይደለም conditional ያልሆነ ዘላለማዊ እንጂ።
ሀገሬን እወዳለሁ እያልክ ሀገርህን አሳልፈህ ስትስጥ የምትናገረውን አለማወቅህን ያጋልጥብሃል: የወራሪው ትግሬ ሆነ የታሪክ ቅራሪው ኦነግ ቢናገሩ እውነት አላቸው፤ አጥንታቸው የተዋቀረውና ስጋ የለበሰው በኢትዮዽያ ጠልነት ላይ ተመስርቶ ነውና:
ከጥዋቱ የውጭ ጠላቶቻችን በገንዘብ ገዝተው መርዝ ለውሰው ያጎረሷቸውን ሀገር የመበተን ተልዕኮ ውሻ በበላበት ይጮሀል ነውና ይኸው ዛሬም አቅላቸውን እንዳሳታቸው ይናውዛሉ: ታዲያ አንተ በኢትዮዽያ ስም የምትምል የምትገዘት ምን ቤት ሆነህ አብረህ ተሰለፍክ?
ከምዕራባውያን ኢምፔሪያሊስቶች ጋር አብረህ ቆምክ፤ ከውስጥ አርበኞቻቸው ጋር ተሰልፈህ ያገርህን ውድቀት እንደነሱው ተመኘህ: እውነቱን እንነጋገር፤ አንተ በእርግጥ ማነህ? አያት ቅድመ አያቶችህን በሞታቸው እርፍት የነሳህ ምን አይነት አሪዎስ ብትሆን ነው።
ስብዕናቸውን አውልቀው ለጣሉ ተገዥ መሆን በቁም መሞት ነውና ስይመሽ ስይረፍድ ሃገርህን ታደግ፤ ለሚያልፍ መንግስት ብዙ አትጭነቅ ኢትዮጵያ ዘለዐለማዊት ናትን.።
https://youtu.be/YDWCtnhAqao