ግሩም ጫላ ጋዜጠኝነትን መሸቀጫ ያደረገ የአብይ አህመድ ካድሬ

እንጂ በስነምግባር የሚመራ ባለሙያ ጋዜጠኛ አይደለም!!!

girumለቻይናው የዜና ጣቢያ #CGTN_Africa በሰሜን ሸዋ ምንጃርና ሸኮራ የከሸፈው አሸባሪዎቹ ጭፍጨፋ ጉዳይ ዜና የዘገበው ግሩም ጫላ ከመሰረታዊ የጋዜጠኝነት ሙያ ህግና ደንብ ባፈነገጠ ሁኔታ ልክ እንደ አንድ መንግስታዊ ካድሬ ክስተቱን ከአንድ ወገን ብቻ የተሰጠውን ፕሮፖጋንዳን ዜና ነው ብሎ ሲዘግብ ታዝበናል።

የግሩም ጫላ አዘጋገብ በምንጃር ሸንኮራ ያሉ ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች የኦሮሚያ ጸጥታ ኋይሎች ላይ በወሰዱት እርምጃ በርካታ የጸጥታ አባላቱን ገድለዋል በማለት የአማራን ሕዝብ ጽንፈኛ በማለት ፍረጃ የገለጸበት አገላለጽ እንደ አንድ ጋዜጠኛ በስፍራው ሄዶ ያየውን እና የሰማውን አጠናቅሮ የዘገበ ሳይሆን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የሰጠውን መሰረት የለሽና እረሰበርሱ የሚቃረን መግለጫን እንዳለ የተጠቀመ በመሆኑ በጋዜጠኝነት ሙያ የሚሸቅጥ ወገንተኛ ካድሬ መሆኑን አሳይታል።

በእርግጥ እኛም ከእንደነ ግሩም ጫላ አይነት ከስርዓቱ ጋር ጡት የተጣቡ ባለሙያ ነን ባይ ጭምብላም ካድሬዎች እውነትን የማንጠብቅ ሲሆን በተለይም ግሩም ጫላ በአፍሪካ ግዙፉን የቴሌቪዢን ጣቢያ እገነባለሁ በማለት በቅርቡ በስርዓቱ መጠነ ሰፊ የመሬት ስጦታ በአዲስ አበባ ተቀብሎ ባለ ስድሳና ሃምሳ ፎቅ ለመገንባት የሚዋትት ጥቅመኛ ካድሬ ስለሕዝባችን እና ስለሀገራችን እውነተኛውን ተጨባጭ ክስተት ይዘግባል ብለን ቅንጣት ታህል እንደማንጠብቅ ግልጽ ነው።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና በአቢይ መራሹ ብልጽግና ስር ያሉት እንደነ OBN እና ዋልታ እና ፋና ሚዲያዎች በመጀመሪያ ዘገባዎቻቸው ማንነቱ ያልታወቀ ታጣቂ በሰሜን ሸዋ ምንጃር ሸንኮር አውራ ጎዳና መንገድ ላይ ጉዳት አደረሰ ብሎ መግለጫዊ ዜና ሰርቶ የነበረ ሲሆን በኋላ ላይ ግን ሕዝባችንን በኦነግ ሸኔ ስም እንዲጨፈጭፍ የተላከው የኦህዴድ ኢ-መደበኛ ገዳይ ታጣቂ በአካባቢው ሕዝብ በፋኖና በልዩ ኋይላችን አይቀጡ ቅጣት መቀጣቱ እንደታወቀ የተገደሉት የኦሮሚያ ጸጥታ አስከባሪ ናቸው የአማራ ክልል ሕዝብም ገዳይ ጽንፈኞች ናቸው የሚል ይዘት ያለው መግለጫ ማውጣታቸው ይታወቃል።

በዚህም መሰረት ፋኖ ሸዋ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የኦሮሚያ ክልል ወደ ምንጃር የተላከው የኦሮሚያ ጹጥታ አስከባሪ ነው ብሎ እስካመነ ድረስ ይህንን ሃይል ያሰማራው አመራር በአስቸኴይ ለፍርድ ይቅረብልን ሲል ጠይቌል።

እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ እንዲገደል የተፈረደበት የሰሜን ሸዋ ጀግና ሕዝብ ከመገደል ይልቅ ገዳዮቹን አጋድሞ በመመለሱ ግሩም ጫላን መሰል ጋዜጠኛ ነን ባይ ጥቅመኞ ካድሬዎችና የሽመልስ አብዲሳ ቡድን ወደ ምንጃር የዘመተው የኦሮሚያ ጹጥታ አስከባሪ ናቸው ገዳዮቹም የአማራ ጽንፈኞች ናቹው እያሉ በማላዘን ላይ ይገኛሉ።

የሰሜን ሸዋ ጀግና አማራ እኛ ለበርካታ ጊዜያቶች ደግመን ደጋግመን ስንገልጽ የነበረውን የጨፍጫፊ ገዳዮችን የኦህዴድ ኢ-መደበኛ ታጣቂነትን በይፋ አደባባይ ጭምብላቸውን አውልቆ ያሳወቀ ጀግና በመሆኑ በጣም ሊመሰገን እና ሊደነቅ የሚገባው መሆኑን ነው በዚህ አጋጣሚ መግለጽ የምንፈልገው።

በመላ ኦሮሚያ እና በሰሜን ሸዋ እየተንቀሳቀሰ አማራዊያንን በማንነታቸው እየለየ በመጨፍጨፍ ተግባር ላይ የተሰማራው በዳቦ ስሙ ኦነግ ሸኔ ተብሎ የሚጠራውና በጃልመሮ የሚመራው ቡድን ሳይሆን በአቢይ አህመድ በሽመልስ አንዲሳና በአባዱላ ገመዳ የሚመራው የኦህዴድ ኢ-መደበኛ ገዳይ ታጣቂ ቡድን መሆኑን በተጩባጭ ማስረጃዎች ጋር አስደግፈን በማቅረብ ደጋግመን ስንገልጽ የነበርነው እውነታ መሆን አይዘነጋም።

ዛሬም ሆነ ነገ መላው የአማራ ሕዝብ ማንም ሆነ ማን በህልውናው ላይ ጥቃት ሊፈጽም የሚመጣን ማንኛውንም ዓይነት ሃይልና ቡድንን መክቶ መደምሰስ እንዳለበት አበክረን እያስገነዘብን ዛሬ በሰሜን ሸዋ ላሉት ጀግኖቻችን ለፈጸሙት አስደናቂ ጀብድ የተሰማንን ኩራትና አድናቆትን ለመግለጽ እንወዳለን!!!!

. ጋሻ መልቲ ሚዲያ

5 Comments

 1. “ግሩም ጫላ ጋዜጠኝነትን መሸቀጫ ያደረገ የአብይ አህመድ ካድሬ እንጂ በስነምግባር የሚመራ ባለሙያ ጋዜጠኛ አይደለም!!!” የምትለዋን ዘሐበሻ ለጥፎ አንብቤ ስቄ ማቆም አቃተኝ! መስተዋት የሚባል ከቤት የላችሁም?

 2. የሰው ቆዳ ለብሶ የሰይጣን ስራን የሚያካሂደው አውሬው ኮሎኔል አብይ አህመድ አሊና በእርሱ የሚመራው የኦሮሙማ ቀንደኖች ስብስብ ስልጣን ላይ ከወጡ ጀምሮ ላለፉት አራት አመታት በአገሪቱ አራቱም ማእዘናት እየጠፋ ያለው የሰው ህይወትና የንብረት ውድመት መንግስት ተብየው የዱርየወች ስብስብስ ማስቆም ሲችል ሊያስቆመው ስላልፈለገ ብቻ ችግሩ ተባብሶ ቀጥሏል፡፤ በአዲስ አበባ ውስጥ በተረኞቹ ኦሮሙማዎች የተሳሰረው የአገር ዘረፋና የንብረት ገፈፋ ስራ በሰፊው ተጧጧፎ ቀጥሏል፡፡ ለዚሁ ዋናውን ሚና የምትጫወተው ከንቲባ ተብዬዋ የፖለቲካ ቁማርተኛው አብይ አህመድ ቀንደኛ ተላላኪ አዳነች አበቤ ነች፡፤

  አማራው በትህነግ በተፈጸመበት ወረራ፣ጭፍጨፋና ዘረፋ ሳያገግምና በራሱ የአማራ ሆዳም ሹመኞች ጭምር እጅግ እንድዋረድና አንገቱን እንዲደፋ በተደረገበት በዚህ ወቅት ድብቁ የኦሮሙማ ካውንስል ‘ጊዜው አሁን ነው” በሚል ስሌት ይመስላል የኦሮሚያ መንግስት ነኝ የሚለውን ስብስብና በሁሉም የኦሮሚያ ዙሪያ ካሉ ክልሎችና ህዝቦች ላይ እንዲዘምትና ኦሮምያ እንዲትሰፋ፤ እንድታብጥ እያደረገ ነው፡፤ ልብ በሉ፡፡ በዚህ ለህዝብ ድብቅ በሆነው የኦሮሙማ ካውንስል ውስጥ አብይ ትልቁን ሚና እንደሚጫወት አትርሱ፡፡
  ይህ በዚህ እንዳለ በቅርቡ ሁለት አድስ የኦሮሙማ ዲታወች ሰፊውን የኦሮሙማ የዘረፋ ካምፕ ተቀላቅለዋል፡፡ አንዱ ኦቦ አልማው ጋሪ የሚባል ሲሆን ኦሮሙማወች “ህገ መንግስታችን” ከሚሉት በተቃራኒው ቆመው “ፊንፊኔ” እያሉ በሚጠሯት በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ‘GOJO BRIDGE HOUSING’ በሚል ስም በአመት መቶ ሽህ ቤቶችን ለመገንባት በሚል ሰበብ በከንትባ ተብየዋ ድጋፍና ከህጋዊ አሰራር ውጭ ተሰማርቶ ዘረፋውን ተያይዞታል፡፡
  ሌላው ደግሞ አፍሪካ ራሷን የቻለ ሜድያ ያስፈልጋታል በሚል ሰበብ በኦቦ ግሩም ጫላ አማካይነት የአፍሪካ ሜድያን ለማቋቋም እየዘረፈ ያለው የዘረፋ ማእከል ሲሆን አሁንም ከህጋዊ አሰራር ውጭ ግሩም ጫላ በአዳነች አበቤ ድጋፍ 5000 ስኩየር ካሬ ሜትር ቦታን ተረክቦ በኬኛዎች የሚመራውን የዘራፊወች ካምፕ ተቀላቅሏል፡፡
  በመሰረቱ ግሩም ጫላ ፍጹም የጋዜጠኝነት መርህን በሚጋፋ መልኩ ለቻይና አለምእቀፍ የቴሌቪዥን ዜና አገልግሎት መረጃን እያዛባ የሚሰጥ ግለሰብ እንደሆነ ማንም ሰው ያውቃል፡፡ ግሩም ጫላ ዘር ከልጓም ይስባል እንዲሉ ይሄውና እየታረደ ባለው አማራ ላይ እንደጌቶቹ ማለትም እንደ አብይ፣ ገተቱ ሽመልስ አብዲሳና የአብይ ቀበሮ የሆነችው አዳነች አበቤ ሁሉ እርሱም ጣቱን በአማራ ላይ በመቀሰር ሙሉውን ውሸት የሆነ አማራን የሚወነጅል ዜና በማሰራጨት ላይ ይገኛል፡፡
  ይህ ሁሉ ውጣ ውረድ ኢትዮጵያዊንትን አጥፍቶ አገሪቱን ኦሮማዊት ለማድረግ የሚሰራ የሸፍጥ ፖለቲካ ሲሆንነ ሄዶ ሄዶ ይከሽፋል፡፡ ይተነፍሳል፡፤ በዘረፋ ላይ የተሰማሩት ዘራፊወችም ሆኑ በወንጀል የተጨማለቁት ወንጀለኞች ሁሉም ፍርዳቸውን ያገኛሉ፡፡

 3. አለም ሰው በካድሬነቱ ሲወቀስ አንተን ይመስልሀል። እንዲህ ሁነህ የምትበላው እንጀራ።ጌታህም ስር እትም እድሜ የለውም ለነገሩ ሸርተት ሲል ቀድመህ የምትከዳው አንተ ነህ።

 4. ግሩም ጫላ አለም አቀፍ መስፈርትን ያሟላ ተገዳዳሪ ሚዲያ ይገነባል ብለህ ነበር ሰይፉ ሾው ላይ ገና ሳትጀምረው ኦነግነትህ ጠልፎ ጣለህ ማለት ነው? ካንተ የጁዋሩ ኦቢኤን ተሻለ ማለት ነው? ፈንጩበት እስክንኮታኮቱ መቼም አላወቃችሁበትም።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Alemayehu Timotiwos Sidama Peace Security Bureau Head
Previous Story

በኦሮሚያ እና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በተቀሰቀሰ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ተገደሉ

OLF Shine
Next Story

ትኋን ቤቴን ወረረው ብሎ ቤቱን የሚያቃጥል የለም – ጥሩነህ

Latest from Blog

ህገ መንግስታዊ ዲዛይን ምርጫዎቻችን የትኞቹ ናቸው?

ኤፍሬም ማዴቦ (emadebo@gmail.com ) እኛ ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን ስንገለጽ የረጂም ግዜ ሥልጣኔና ታሪክ ያለን፣በነጭ ያልተገዛን፣ከ2000 አመት በላይ ተከታታይ የመንግስት ሥርዓት ያለን፣የሦስቱ ዘመን ያስቆጠሩ አብርሃማዊ ሃይማኖቶች አገር ነን እያልን ነው። ነገር ግን ባለፉት ሃምሳ አመታት

የኢካን ዓላማ በኔዘርላንድ የሚኖረውን ትውልደ ኢትዮጵያውያንን እና ኢትዮጵያውያንን ኮምዩኒቲይ የማሰባሰብ ሳይሆን የመከፋፋልና የማዳከም ተልኮን ያነገበ ነው።

አገር ! ለየአንድ ሠው ቋንቋው፣ ልማዱ፣ ባሕሉ፣ እምነቱ፣ አስተሳሰቡ፣ ወጉና በአጠቃላይ እሱነቱና ማንነቱ የሚከበርበት ብቸኛ ሥፍራ ነው። ኢትዮጵያውያንም በስደት በሚኖሩባቸው አገራት ሁሉ እነኝህን በስደት ያጧቸውን የግልና የጋራ ማንነቶቻቸውን በአንድ ላይ ሆነው ለመዘከር
Go toTop