ብልፅግና ወያኔ የጎደለው ኢህአዴግ ነው:: አቤል ወንድሙን ወያኔን ገሎ ወያኔን መሆን ያማረው ቃኤል ነው:: ብልፅግና ኦነግና ኢህአዴግ ወያኔ ስልቻና ቀልቀሎ መሆናቸውን ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምዕራብ እስከ ምስራቅ ያሉ ኢትዮጵያውያን አሳምረው ያውቃሉ::
ጠ/ሚ አቢይ አህመድ አጭበርባሪና ውሸታም (deceptive & liar) መሆናቸውን የማያውቁት እራሣቸው ብቻ ናቸው:: ለዚህ ነው ዴሞትፎር ጠመንጃ ከግምጃ ቤት በማውጣትና በመደርደር “ሸወድኳቸው” እያሉ ጅል መንጋዎቻቸውን በጅልነት የሚያዝናኑት!
ጋሽ ፀጋዬ ገ/መድህን ‘እንቁራሪቶች አብዝተው ስለጮሁ ባህሩ ውስጥ ሌሎች እንሠሣት የሉም ማለት አይደለም’ ያለው ትዝ ይሏል!
አጨብጫቢ አክቲቪስቶችን ብቻ ሣይሆን ሆድ አደር ጋዜጠኞችን እያየን ነው::
ይሄው ነው!/ HT