የአሜሪካ መንግሥት HR 6600 የሚባል ኒኩለር በአገር ና በህዝብ ላይ ሊወረውር ተዘጋጅቶል ። የኢትዮጵያ ህዝብ ምን በድሎት ሊያጠፋው እንደተነሳ ግን የሚታወቅ ነገር የለም ። በዚህ ሚሊዮኖችን በችግር ና በችጋር የሚጨርስ ፤ በሺ ማዕቀብ የተሞላ የ666 ቦንብ ይኽንን የእግዜር ፍጡር የአሜሪካ መንግሥት ለማጥፋት መነሳቱ በምን ሰበብ እንደሆነም ግልፅ አይደለም ።
የአሜሪካ መንግሥት የቆመው ለአሜሪካ ቱጃሮች በመሆኑ ለእነሱ ብዝበዛ ሲባል የአፍሪካን ህዝብ በድህነት በበሽታ አማቆ መጨረስ ግቡ እሥካልሆነ ጊዜ ድረሥ ይኽን የመሠለ አረመኒያዊና ኢ ፍትሐዊ ፣ ኢ ዴሞክራሲያዊ ተግባር ለመፈፀም ባልተነሳሳ ነበር ። ለአንድ ፐርሰንቱ ቱጃር አግበሥባሽነት ሲል ኢትዮጵያን ከህዝቦ ውጪ እንጂ እሥከ ህዝቦ አልፈለጋትም ። ዩክሬንን ከነ ህዝቦ እንደማይፈልጋት ሁሉ ማለት ነው ። ዛሬም ሆነ ትላንት አሜሪካ በከፋ መልኩ ያልተሳተፈችበት ጦርነት በዓለም የለም ። …
በነገራችን ላይ ፣ ዩኩሬንን ከነህዝቧ ቢመለከት ኖሮ ፣ ዩክሬን ከነሙሉ ክብሮ ከሩሲያ ጋር ተከባብራ እንድትኖር ፣ የኔቶ አባል እንዳትሆን ትሁት ምክሩን ይለግሥ ነበር ። ከቶም ሩሲያን ለማሸነፍ በማይቻልበት መንገድ ዩክሬንን አጋፍጦ እንድትፈራረሥ ማድረግ፤ ለህዝብ ደንታ ቢሥነት ነው ። ሶቬቶችን አንድ ጊዜ ማታለል ችለናል ፣ ሁለተኛም እናሞኛቸዋለን ማለትም በኒኩለር መጫወት ነው ። ሩሲያ አሜሪካ በሄሮሽማ ና በናጋሳኪ እንዳደረገችው ብታደርግ ማነው ተጠያቂው ? አሜሪካንን እንደዓለም አለቃ የቆጠሩት ምእራባዊያን ናቸው ።
በዓለም የተካሄዱ ና የሚካሄዱ ጦርነቶች ሁሉ ፣ የአሜሪካ መንግሥት እጅ ያለባቸው ናቸው ። እነዚህ በአሜሪካ ቀጥተኛ ና ሥውረ ድጋፍ የሚደረግላቸው ጦርነቶች ፣ በዴሞክራሲ ሥም የሚካሄዱ ፤ በአሜሪካ ጥቅም ላይ ያነጣጠሩ ፀረ ዴሞክራሲ ጦርነቶች ናቸው ። በአፍሪካ በተዘዋዋሪ በምትመራው ጦርነት የአሜሪካንን የወደፊት ብዝበዛ ማፋጠን እና ነጭ ዜጎቿን በአፍሪካ በማስፈር አፍሪካን መቀራመት ነው ። አላማዋ ።
በዓላማዋ መሠረትም ፣ በኢትዮጵያ በመለሥ ዜናዊ አማካኝነት የጀመረችውን ኢትዮጵያን የመበታተን ልዩ ኦፕሬሽን ለማሳካት በዴሞክራሲና በሰብዓዊ መብት መሸቀጦን ገፍታበታለች ። በቢሊዮን ዶላር በእንግሊዝ ፣ በአሜሪካ እና በሌሎች የአውሮፓ አገራት ያሥቀመጡትን ዘራፊ የቀድሞ ባለሥልጣናትን በማሥተባበር ፤ ተመልሰው በኢትዮጵያ ህዝብ ጀርባ ላይ እንዲፈናጠጡ በማድረግም ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር ለማድረግም በታላቅ ሴራ ላይ ተጠምዳለቾ ። ይህ ሴራዋ የማይሳካ ከሆነ ግን የራሷን አሻጉሊት መንግሥት በኢትዮጵያ አሥቀምጣ በእጅ አዙር አገሪቱን በመቆጣጠር እንዳሻት በምድሪቱ ሀብት ላይ ለመፈንጨት ትፈልጋለች ። HR 6600 ሌላውም ተጎዳኝ የማአቀብ ህግ ፣ ከዚህ አንፃር ነው ፣ ዛሬ የመዘዘችው ።
ይኽ ህግ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ ፣ የአሜሪካ መንግሥት ፣ ከአሜሪካ ህዝብ ተነጥሎ ብቻውን የኢትዮጵያ ህዝብ ጠላት መሆኑን በማሥመሥከሩ ከአሜሪካ ህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ ይገጥመዋል ብዬ አሥባለሁ ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ህዝብ ወያኔን ወደፈቀደው ሰዖል ለመክተት ጫፍ ላይ ሲደርስ ፣ ወደትግራይ አትግቡ ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑንን አሣምረው ያውቃሉ ። በአናቱም እጅግ የሚዘገንን ግፍ በአማራክልል ህዝብ እና በአፋር ክልል ህዝብ የፈፀመው ወያኔ / ትህነግ እንደሆነ ከአሜሪካ ህዝብ የተሰወረ አይደለም ።
ከዚህ አንፃር የአሜሪካ መንግሥትን እኩይነት የአሜሪኬ ዜጎች ግምግመው የዓለም ፖሊሥነትህ ይበቃል እንደሚሉት አሥባለሁ ።
የአውሮፓ ህዝብም የአሜሪካንን የእብድ ፣ እብድ ጫወታን ማሥቆሞ ይኖርበታል ። በበኩሌ ኒኩለር ከታጠቀ መንግሥት ጋር እልህ ውሥጥ መግባት የእብድ ጫወታ ነው ።
በመጨረሻም ፣ በኢትዮጵያ ላይ ሊተገብረው ያሰበው ፣ በእብድ ሴኔት የተረቀቀ ድህነትን አባባሽ ኒኩሌር ነውና ወደ ተግባር ሳይገባ በፊትመታገድ አለበት ። HR6600 ማለት ፣ ሁለቱ ዜሮ ጠፍቶ አንድ 6 ቢጨመርበት 666 የሚሆን የሤጣንን ተግባር አመላካች ነው ። ለሤጣናት የተመቻመቸ ዕድል በመፍጠርም ከዚህ በፊት ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የእርስ በእርስ ጦርነት ማዋለድ ነው ። ኢትዮጵያ ላይ ኒኩለር እንደመተኮስም ይቆጠራል ።