March 24, 2022
14 mins read

ሕዝብ ሆይ! በእርዳታና በምጽዋእት ስም የሚዘርፍህን ሌባ አስተፋው! ተማህበራዊ ግንኙነትም አርቀው!

በላይነህ አባተ ([email protected])

እንደ አለመታደል ዛሬም እንደ አለፉት ሰላሳ ዓመታት ሕዝብ ያዋጣው ገንዘብ ተዘረፈ፤ የወጪ ገቢ ስሌት (ኦዲት) ተደርጎም አያውቅ የሚል ጩኸት ሕዝብ እየሰማ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምስት ሺህ ዘመናት በላይ ታደበራቸው መልካም ባህሎች አንዱ የተቸገረን መርዳትና የሰው ገነዘብ መንካትን የመፀየፍ ባህሪ ነበር፡፡ ዳሩ ግን አማራ ለብዙ ሺህ ዓመታት የመለኮትን ትዕዛዛት የመከተሉና ሕግ አክባሪ ሕዝብ መሆኑ ሰልበው ወይም በመድሃኒት ለሚያመክኑና ሆድ ቀደው ሺል ለሚገድሉ ዘር አጥፊ ጭራቆች ጥቃት እንደ ዳረገው ሁሉ የለጋስነት ባህሪውም ለነፃነትና የተቸገሩንትን ለመርዳትና ያዋጣውን በርሃብ ጣረሞት ተሚሰቃይ ጉረሮ ሞልቅቀው እንደ ጪልፊት ለሚበሩ አረመኔ ከርሳሞች አጋልጦታል፡፡

Thiefለጋሱ ሕዝብ ለተቸገረ፣ ለነፃነት፣ ለአገር ዳርድንበር፣ ለሕዝብ መገናኛ ወዘተርፈ እያለ ተእለት ጉርሱ እየቀነሰ ያዋጣል፤ ሰይጣን የሚያበረው ጩልሌ ይልፈዋል፡፡ ለማኝ ለምኖ ታገኘው እየቀነሰ አስራት ይከፍላል፤ የሳጥናኤል አገልጋይ ጪልፊት ካህን ሞጭልፎ በእህት በወንድሙ ልጅ ስም ፎቅ ይሰራል ወይም የቅንጦት ኑሮ በመኖር ቅዥት ይዳክራል፡፡

እነዚህ ነገ የሚበሰብሰውን በኅጥያት የቆሸሸ ሥጋቸውን አንደ ቅሪላ ለመንፋትና ገደብ የሌለውን ፍላጎታቸውን ለማርካት የሚራወጡት ጪልፊቶች ባለፉት ሰላሳ ዓመታት እንደ አሸን ፈልተው “የሰው ገንዘብ ቁንቋን ነው” እያለ ያሳደገንን ባህላችንን ጭምልቅልቅ አድርገውታል፡፡

በሰባት ዓመት እድሜዬ አካባቢ ተቤታችን አጥር ግቢ ውጪ ስጫወት ሁለት አስርና አንድ አምስት ሳንቲሞች አገኘሁ፡፡ የአገኘኋቸውን ሳንቲዎች በቀኝ እጄ ያዝኩና ወደ ቤታችን ሮጬ እናቴን “እቴቴ ሃያ አምስት ሳንቲም አገኘሁ!” ስል ጮህኩ! ተዚያም የልጅ ጣቶቼን ፈልቅቄ ሳንቲሞቹን አሳየሁ፡፡ እናቴ ተእጆቼ ያሉትን ሳንቲሞች ላለመንካት እግዜርን እንደሚለማመን እጇን ወደ ሰማይ ዘረጋችና ሁለት ሜትር ያህል ወደ ኋላ ተስፈነጠረች፡፡ እጆቿን ወደ ጣራው እንደዘርጋችም “የሰው ገንዘብ ቁንቋን ነው!! ሂድ ታገኝህበት ጣልና እጅህን በሳሙና ሶስት ጊዜ ታጠብ!” ስትል አዘዘችኝ፡፡ በታዘዝኩት መሰረት ሳንቲሞቹን ታገኘሁበት ጣልኩና ሶስት ባለችው ላይ አራት ጨምሬ ሰባቴ ታጥቤ ቁንቋኑን ተእጆቼ አጸዳሁ፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ የአብዛኞቻችን ወላጆች ሃይማኖትና ባህል እንደዚህ የተቀደሰ ነበረ፡፡

ከብዙ ዓመታት በኋላ ዛሬም “የሰው ገንዘብ ቁንቋን ነው!” የሚለው የእናቴ ድምጥ እንደ ቤተክርስቲያናችን ደወል ይሰማኛል፡፡ በዚህ የእናቴ ቅዱስ ቃል የቤተክርስቲያንን ገንዘብ የሚዘርፉ ወሮበላ ካህናትን ስመዝናቸው ዲያብሎስ ያሰገዳቸው ውቃቢዎች መስለው አንደ አባጨጓሬ በሃምሳ እግር አፈር ላፈር ሲርመሰመሱ እንደ ምስጥም የሰው ሥጋ እያነከቱ ሲበሉ ይታዩኛል፡፡ እነዚህ ለዲያብሎስ የገበሩ ካህናት እንኳን የሰው ገንዘብ ቁንቋን መሆኑን አምነው የሰው ኪስ ሊምሩ ተክርስቶስ ኪስም እየዘረፉ ምድራዊ ፍላጎታችውንና ስስታቸውን ሊያረኩ ተገዳማቸው ወጥተው እንደ ፓስተሮች በየከተማው ሲቅበዘበዙ ይታያሉ፡፡

እንደሚታወቀው ወንበር የተቆናጠጡት ነፍሰ-ገዳይዎች በድሃ ጉረሮ እንጨት እየሰደዱና የአገሪቱን ሀብት እየዘረፉ የውጭ አገር ባንኮችን አድልበዋል፡፡ ባደኸዩት ጎስቋላ ሕዝብ ሥም እየተበደሩና እየለመኑ ልጆቻቸውን በውጪ አገር ሽቅብ እስተመሽናት አድርሰዋል፡፡ ሚስቶቻቸውን በሰዓታት ውስጥ እስከ አንድ ሚሊዮን ያሜሪካ ዶላር ለሸቀጥ ሺመታ እንዲያጠፉ አስችለዋል፡፡ የጎሰጎሱት ቁንጣንና ቁርጠት በሆናቸው ቁጥር “በቻርተር” አውሮፕላን  እየበረሩ አሜሪካ፤ አውሮጳ፣ ኤሽያ፣ እስራኤልና ደቡብ አፍሪካ መታከሚያ አድርገውታል፡፡ የንግድ መርከብ እስከመግዛትም ደርስዋል፡፡ ቁንቋኑ የሰው ገንዘብ እንደ ሂትለር፣ ኢዲ አሚን፣ ጋዳፊና ለገሰ ትቢያ ተመሆን የማይድነውን ገላቸውን ንሶላቸዋል፡፡

እነዚህን ነፍሰ-ገዳዮች ለማስወገድ ተደራጀን ተሚሉት ተቀዋሚዎች ብዙዎቹም ቁንቋኑ የሰው ገነዘብ ቦርጫቸውን እንደ ድርስ እርጉዝ ሲገፋውና መቀመጫቸው እንደ እማማ ታንቺ ወዲያ ጋን ሲያሰፋው ይታያል፡፡ እነዚህን ያዩ አንዳንድ ግልገል ዘራፊ ሕዝብ አደራጅ ነን፣ የሕዝብ መገናኛ ሬዲዮ ወይም ቴሌቪዥን ከፋጭ ነን ወዘተርፈ ባዮችም “ጎፈንድ” እየከፈቱ ገንዘባችንን ሞጭልፈው የቁንቋን ኑሮ መኖርን ብልጠት አድርገውታል፡፡

ለቤተክርስቲያን የሚያስገባው አስራት በዘራፊ ካህናት እንደሚሞጨለፍ ሕዝብ ያውቃል፡፡ ዳሩ ግን ይህ ሕዝብ ተቤተክሲያን መልስ በእየቤቱ ያማና ዝም ይላል ወይም “እግዜር ይቅጣቸው!” ይልና የራሱን ሐላፊነትና ግዴታ ለእግዚአብሄር ሰጥቶ ለእግዚአብሔር ሳይሆን ለገንዘብ የሚገዙ ዘራፊ ካህናትን እየቀለበ ይኖራል፡፡ ለመንግስት አፍንጫውን ተይዞ ግብር ይገብርና በከፈለው ግብር ባሩድ እየገዙ ሲጨፈጭፉትና ሲገርፉት ለጥ ብሎ ይገዛል፡፡ ተሞት የተረፈው እንደገና መረሸኛውንና መገረፊያውን ግብር ይገብራል፡፡ ተቃዋሚና አደራጅ ነን ለሚሉትም መልካም ነገር የሚያመጡ እየመሰለው ያዋጣል፡፡ ዳሩ ግን ገንዘቡን ተቀብለው ለምን እንዳዋሉት ለመጠየቅ ይሰንፋል፡፡ ይህ እየተለመደ የመጣ ከንቱ ባህል የሰው ገንዘብ ቁንቋን መሆኑን ለማያምኑ የሰይጣን ተከታዮች ሰርግና ምላሽ ሆኗል፡፡

መጣፉ እንደሚለው ሰይጣን ክርስቶስን ወደ ተራራ ወስዶና ንብረት አሳይቶ “ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ ማቴ 4፡9” ሲል ክርስቶስን የፈተነው በገንዘብ ነው፡፡ ይህ የሚያሳየው ሰይጣን ምን ያህል ገንዘብን በመሳሪያነት እንደሚጠቀምበት ነው፡፡ ገንዘብ የሰይጣን መሳሪያ መሆኑን የካዱ የሃይማኖት አባቶች የድሃን አስራት አግበስብሰው ተፎቅ ሲያድሩ አስራት ከፋዩ ቤቱ እየፈረሰበትና በቦንብ እየጋየበት ተመንገድ ጦሙን እያደረ ነው፡፡ ባለስልጣኖች ተመንገድ የጣሉትን ሕዝብ ንብረት እየዘረፉና በሥሙ እንደ ዓለም ባንክ፣ አይ ኤም ኤፍ፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይና እንግሊዝ ያሉትን ባንኮችና አገሮች እየለመኑ የራሳቸውን ቤተሰቦች በውጪና በአገር ውስጥ እያንደላቀቁ ነው፡፡ እናቴ ቁንቋን ያለቸው የሰው ገንዘብ ለሰይጣን ተከታዮች ምቾችና ቅንጦት እየሆነ ነው፡፡

ቅዱሱ መጽሐፍ “ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም። ማቴ 6፡24“ ባለውና እናቴም በዚህ ተመርኩዛ “የሰው ገንዘብ ቁንቋን ነው” ባለቸው በሚያምኑ ቤተክርስቲያንም ሆነ አገር ካልተመራች ሰይጣን በገንዘብ የሚያማልላቸው አረመኔዎች ሲያተራምሱን መኖራቸው ነው፡፡ ሰይጣን በገንዘብ የሚያማልላቸውን አሪዎሶች ተቤተ-መንግስትም ሆነ ተሃይማቶች ተቋማት እስካልወጡ ድረስ የአገራችንም ሆነ የቤተክርስቲያናችን መከራ እየከፋ መሄዱ እማይቀር ነው፡፡

እንኳን በገንዘብ ሊታለሉ ነፍሳቸውን እየገበሩ አርበኞች በአጥንታቸው በገነቧት አገር ባለስልጣን፣ ተቃዋሚ ወይም ህዝብ አደራጅ ተመሆን በፊት የሰው ገንዘብ ቁንቋን መሆኑን ማመን አስፈላጊ ነው፡፡ ብፁአን ሰማእታት አንገታቸውን ተቀልተው በአለት ተመሰረቷት ቤተክርስቲያን ፓትርያቲክ፣ ጳጳስ፣ መነኩሴ፣ መሪጌታ፣ ቄስና ዲያቆን ከመሆን በፊት “ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አለመቻሉን” ማመን አስፈላጊ ነው፡፡

የሰው “ገንዘብ ቁንቋን ነው!” የሚለው ቅዱስ ባህል ፈተና ውስጥ በገባበት በዚህ ዘመን ሕዝብ ለሃይማኖትም ሆነ ለዓለማዊ ተግባር ያወጣው ገንዘብ የት እንደ ደረሰ የመጠየቅ፤ ዘራፊዎችንም ተሕግ ፊት የማቅረብና ተማህበራዊ ግንኙነት የማራቅ ባህል ማዳበር አስፈላጊ ነው፡፡ ይኸንን ዘራፊን የሚቀጣ ባህል የማይገነባና ያዋጣው ገንዘብ የት እንደ ደረሰ እማይጠይቅ ሕዝብ ዘራፊዎችን እያበረታታና የሳጥናኤልንም ግብር እያስፋፋ ነው፡፡ ስለዚህ ሕዝብ ሆይ የዘራፊዎች ቁጥር ይበልጥ እንዳይበረክትና ሳጥናኤልም ደስ እንዳይለው በእርዳታና በምጽዋእት ስም የሚዘርፍህን ሌባ አፍንጫውን ይዘህ አስተፋው! ተማህበራዊ ግንኙነትም አርቀው! አመሰግናለሁ!

 

መጀመርያ የካቲት ሁለት ሺ አስራ ሁለት ዓ.ም. እንደገና መጋቢት ሁለት ሺ አስራ አራት ዓ.ም.

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop