H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች – ፀሓፊ ፂዮን ዘማርያም

በኢትዮጵያ ማባሪያ የሌለውን የጦርነት ንግድ ሴራ ለመበጣጠስ ጊዜው አሁን ነው!!! መታረድ በቃን!!

ET

current politiciansሦስት እግር በርበሬ መንቀል አቅቷችሁ
የእፉኝት ልጆች ተጫወቱባችሁ!!!

መግቢያ

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት ወንጀል፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal Court)  ባለሰልጣናቱን ለፍርድ በማቅረብ ሰላማችንን ማስጠበቅ ጊዜው አሁን ነው!!!በኢትዮጵያ ማባሪያ የሌለው የጦርነት ንግድ  የሴራ ቀለበት ለመበጣጠስ ጊዜው አሁን ነው!!!

የትግራይ ህዝብ ወደ አማራ፣ አፋር፣ ኤርትራና ሱዳን በመሰደድ ላይ ይገኛል፡፡ ይሄ የሚያሳየው ጦርነቱ በገዢ ዎቻችን መኃል እንጂ በህዝቦች መኃል አለመሆኑን ያስመሰከረ ማባሪያ የጣውን የጦርነት ንግድ  የሴራ ቀለበት የበጣጠሰ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ሠላም ያወርዳል እንላለን፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ በህብረት በየክልላችን ያሉ ወንጀለኞችን አጋልጦ ለፍርድ ማቅረብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን፡፡ ሴት ለደፈረ ጥብቅና አንቆምም! ስብዓዊ መብት  ለጣሰ ወንጀለኛ ጥብቅና አንቆምም!፣ ለጦር ወንጀለኞች ዘብ አንቆምም! ለዘር ማጥፋት ወንጀለኞች አጋልጠን እንሰጣለን፡፡ ወንጀለኞች በዘር ውስጥ አይከለሉም፡፡  የትግራይ ህዝብ የህወሓትን ወንጀለኛ አመራሮችን፣ የአማራ ህዝብ የብአዴን ወንጀለኛ አመራሮችን፣ የኦሮሞ ህዝብ የኦህዴድ ወንጀለኛ  አመራሮችነ እና የደቡብ ህዝብ ደኢህዴን ወንጀለኛ አመራሮች ለፍርድ በማቅረብ የሃያ ሰባት አመታቱን  የኢህአዴግ የግፍ አገዛዝ ዘመን መዝጋት ይኖርብናል፡፡

በመቀጠልም የብልፅግና ኢህአዴግን የአራት አመታት የዘረኛና ተረኛ ሥርዓት ማባሪያ የሌለው የጦርነት ንግድ  የሴራ ቀለበት በጣጥሰን መጣል የህልውናችን ማረጋገጫ ስለሆነ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት ወንጀል፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal Court)  ባለሰልጣናቱን ለፍርድ በማቅረብ ሰላማችንን ለማስጠበቅ ጊዜው አሁን ነው!!!  ጊዜው አራጁን መንግሥት በህዝባዊ እንቢተኛነትና  ህዝባዊ አመፅ ማስወገድ ነው፡፡ የአብይ ኦሮሙማ ዘረኛና ተረኛ መንግሥት ላይ ህዝባዊ የሽምቅ አመፅ ማቀጣጠል ነው!!! ጊዜው ህዝባዊ ሥልጣን በመያዝ ራስን ማስተዳደረ ነው፡፡ ጊዜው የአብይ ወሬ በቃ ነውና!!!

H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች ተቃወምንም ደገፍንም መፅደቁ አይቀርም!!!

በአሜሪካ ጆባይደን መንግሥት ባወጣው H-R-6600 እና S-3199 ረቂቅ ህግጎች በሰሜኑ ጦርነት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት ወንጀል፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል ምክንያት በኢትዮጵያና ኤርትራ ባለሥልጣኖች ላይ የንብረት ማምከንና የመጎጎዝ ነጻነትን ማገድ እንዲሁም በፋይናንስ፣ በደህንነትና በኢሚግሬሽን፣ በመከላከያና በፀጥታው ዘርፍ ራሳቸውን እንዳይችሉ ማድረግ፣ ብድሮችና የብድር ማራዘሚያ እንዳያገኙ ማድረግ፣ እርዳታ እንዳያገኙ ማድረግ እና የቴክኒክ ድጋፎች እንዳያገኙ የሚያደርግ ማእቀብ በኢትዮጵያና ኤርትራ መንግሥቶች ላይ አዋጁ ይፀናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዚህም ምክንያት የዲያስፖራውን ድጋፍ ያጣው  የአብይ ኦነጋዊ አራጅ መንግሥት የዲያስፖራው እግር ስር  ወድቆል፡፡  አራጁን አብይ አህመድ መጣል ጊዜው አሁን ነው!!! አብይ አህመድ መንግሥት ከአሜሪካ ሦስት ቢሊዮን ዶላር እርዳት ለማግኘት ሲል ከትግራይ ጦሩን አስወጥቶ፣ የአማራን መሬት ህወሓት ለማስረከብ ቀና ጎንበስ ባለበት ጊዜ በአሜሪካ ረቂቅ ህጎች ሰማይ ተደፋበት!!!

በዶክተር አብይ አህመድ አራት አመታት የሥልጣን ዘመን  ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ በጦርነትና ግጭት በተለይ በአማራ፣ አፋርና በትግራይ ክልሎች  በህወሓት፣ ኦነግና ብልፅግና  ተዋናዬች ግማሽ ሚሊዮን ህዝብ ህይወቱን አጥቶል፣ ብዙ ሽህ ከብቶችና ግመሎች ታርደዋል፣ ተነድተዋል፤ አስራ አምስት ሚሊዮን ህዝብ ቀየውን ለቆ ተፈናቅሎ እርዳታ ጠባቂ ዜጋ ሆኖል፡፡  አንድ ትሪሊዮን ብር ንብረትና ኃብት ተዘርፎል ወድሞል!!! የህወሓትና የኦነግ ሽብርተኞች ከህዝብ ግብር ይሰበስባሉ፡፡ ‹‹ማንኛውም ሰው በሕይወት የመኖር መብት አለው፡፡ ማንኛውም ሰው በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር ሕይወቱን አያጣም፡፡›› የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት፣ አንቀጽ15 ቢልም የህዝብ ህይወት እንደ ቅጠል በመርገፍ ላይ ይገኛል፡፡ በሃገሪቱ መንግሥት የለም!  የብልፅግና መንግሥት የጦር ግምጃ ቤቱን መሳሪያዎች ታንኮች፣ ሞርታለች፣ ቢኤሞች፣ ብሬኖች፣ ዲሽቃዎች ሚሳኤሎች፣ ሮኬቶች ፣አዘርፎል፡፡ የሃገሪቱን  ባንኮች፣ ፋብሪካዎች፣ ከባድ መኪኖች፣ አዘርፎል፡፡ በምድረ ኢትዮጵያ ዓየር በዓየር የጦርነት ንግድ ተጦጡፎል፣ አንድ ክላሽን አንድ መቶ ሃያ ሽህ ብር ይሸጣል፡፡ ዓየር በዓየር  ንግድ፣  ህገወጥ የጦር መሣሪዎች ዝውውርና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር  ከቁጥጥር ውጪ ሆኖል፡፡

የአብይ አህመድ የብልፅ መንግሥት ህወሓትና ኦነግ ሸኔን በግልፅና በድብቅ የጦር መሣሪያ ያስታጥቃል፡፡ በፍፁም እንዲጠፉ አይፈልግም!!!  የህወሓትና የኦነግ አሸባሪዎች ኢትዮጵያን የመዝረፍ ህብረት ፈጥረዋል፡፡ አብይ አህመድ የአማራና አፋር ክልሎችን ደሃ አርሶ አደርና አርብቶ አደር ያስገደለና ያዘረፈ አለሌ ፖለቲከኛ ነው፡፡ የህወሓትና የኦነግ አሸባሪዎች የሃገሪቱን  የጦር መሣሪያ ዘርፈዋል፣ ባንኮች ዘርፈዋል፣ መሬቱን ዘርፈዋል፣ መኪኖች ዘርፈዋል፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የቴሌኮሙኒኬሽን መገናኛዎች፣ የመብራት ኀይል ስብስተሸኖችና ትራንስፎርመሮች፣ ፋብሪካዎች ፈትተው  ዘርፈዋል፣ የአርሶ አደሮቹን ከብቶች ነድተው ዘርፈዋል፣ የአማራና የአፋር ክልሎች ስብዓዊና ቁሳዊ ጉዳቶች ተጠያቂው አብይ አህመድ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ጦርነትና ግጭት ተጠያቂው ህወሓትና ኦነጋዊው ብልፅግና ፓርቲ ነው!!! በትግራይ፣አማራና አፋር ክልሎች ለደረሰው  ስብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ተጠያቂ ናቸው፡፡ በህዝብ ላይ ለተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal Court) እንዲጠየቁ  ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው!!!

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የአሳራጁ ሽመልሰ አብዲሳ በወለጋ ዞን እና በቤኒሻንጉል ክልል፣ መተከል ዞን በንጹሀን አማራዎችና ኦሮሞዎችና ሌሎች ዜጎች ላይ ለሚፈጸመው ተከታታይ ጥቃት የአራጁ ኦነግ ሽኔ ጃል መሮ እና ሌሎች ታጣቂ ጏይሎች ብቻ ሳይሆኑ ጥቃቱን ባለማስቆም የክልሎቹ መንግስታት እና የፌደራል መንግስቱም እኩል ተጠያቂዎች ስለሆኑ ለፍርድ ይቅረቡ እንላለን። በህወሓት የጦር አበጋዞች  የሚመራው የተቃዋሚው ህብረት ኃይል አሰላለፍ ተዋጊ ኃይል ብዛት፤  የትግራይ መከላከያ ኃይል ሦስት መቶ ሽህ (300,000) ተዋጊ ኃይል ፣ የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሠራዊት ሃያ ሽህ (20,000)፣ የአገው ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ አፋር ሦስት ሽህ (3,000)፣ ጉሙዝ ነጻ አውጪ ሠራዊት አስር ሽህ (10,000)፣ ጋምቤላ ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ ቅማንት ነጻ አውጪ ሠራዊት አምስት ሽህ (5,000)፣ ሲዳማ ብሔራዊ የነፃነት ግንባር አምስት ሽህ (5,000) የተደራጀ አራጅ ወንጀለኛ ቡድን የአማራውን ህዝብ በመጨፍጨፍ ላይ ናቸው፡፡ ልጅ አብይ መንግሥት ‹‹ታጣቂው ከአራሹ ቁጥር በዝቶ የእህል ምርት ሲጠፋ አልገባውም፣ ችግኝ ይተክላል!!! ፓርኮች ያስፋፋል፣ መንግሥቱ እየወደቀ እያየ፣ የፀና መስሎት!!!  ለአሳራጁ መንግሥት ፍርድ እንዲሠጥ መጠየቅ ጊዜው አሁን ነው!!!

ፋኖና የአማራ ልዩ ኃይል ትጥቅ የማስፈታትና የማፍረስ ሴራ በዓይናችን ለማየት ፈጣሪ እድሜ ሰጥቶናል አራጅን የአብይ አጭበርባሪ የቦዘኔ መንግሥት እነ ጀነራል ተፈራ ማሞን ማባረሩና የፖለቲካ ሴራውን ከጀነራሉ አንደበት  ሰምተናል የአማራ ህዝብ ጀነራል ተፈራ ማሞን ፊልድ ማርሻል አርጎ ያነግሳቸዋል፡፡  ፋኖ ዘመነ ካሴ እልፍ አእላፍ ደም መላሽ ፋኖዎች ለእናት ሃገራችን አበርክቷል፡፡   ‹‹ፋኖ ተሠማራ፣ፋኖ ተሠማራ!  በዱር በገደሉ ትግሉን እንድትመራ ›› ጊዜው አሁን!  አብይ ኦሮሙማን በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለመጫን የሰበው ሴራን ለመበጣጠስ በህዝባዊ እንቢተኛነትና በህዝባዊ አመፅ ከአራጆች ዜጎችን መታደግ ጊዜው አሁን ነው!!!   በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተፈፀሙ የስብዓዊ መብት ጥስት ወንጀል፣ የጦር ወንጀልና የዘር ማጥፋት ወንጀል በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (International Criminal Court)  አማፂ ብድኖች ባለሰልጣናቱን ለፍርድ በማቅረብ ሰላማችንን በመጠበቅ፣  ማባሪያ የሌለው የጦርነት ንግድ  የሴራ ቀለበት መበጣጠስ ጊዜው አሁን ነው፡፡ ጦርነት በቃን ከትግራይ ከሃምሳ እስከ  መቶ ሽህ ህዝብ ወደ አማራ፣ አፋር፣ ኤርትራ በሰላም ሲገበ ህዝቡ በደስታ ከሚበላውና ከሚጠጣው አካፍሎት አስጠልሎት በህብረት በመኖር ላይ ነው፡፡ የአብይ መንግሥት መጠለያ ጣቢያዎች መሥራት እንኮን አልቻለም፣ የምግብ እርዳታም አላቀረበም፡፡ በትግራይ ማባሪያ የሌለውን የጦርነት ንግድ ሴራ የትግራይ ህዝብ እየበጣጠሰ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር አብሮል፡፡ ጊዜው አሁን ነው!!! የአብይ የኦሮሙማ ዘረኛና ተረኛ የጦርነት ንግድ ህዝብን በማባላት የኦሮሙማን ኢንፓየር ለሃምሳ አመት ለመገንባት ነበር፡፡   

መደምደሚያ

በትግራይ፤ በአማራና በአፋር ክልሎች  ውስጥ በንጹሐን ዜጎች ላይ ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው አሰቃቂ ጉዳት፤ በሰሜን ዕዝ እና በማይካድራ የደረሱትን እጅግ አሰቃቂ ጥቃቶች ጨምሮ ተጠያቂ መሆን የሚገባቸው በቅደም ተከተል፤

  • 1ኛ/ ህወሓት ኢህአዴግ ለሃያ ሰባት አመታት ግንባር ሆነው የገዙ ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴድ በዋነኝነት አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሎቹ  ም/ሊቀመንበሮች  እና ካቢኔያቸው ውስጥ በፊትና አሁን የሠሩ ሁሉ፤ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡
  • 2ኛ/ ህወሓት፣  በዋነኝነት ህውሃት እና አመራሮቹ፤ በተለይም የክልሉ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጺዮን እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱን ከመለኮስ ጀምሮ እስከአሁን ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡
  • 3ኛ/ ገዥው ፖርቲ ብልጽግና እና አመራሮቹ፤ በዋነኝነት ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድ እና ካቢኔያቸው፤ ጦርነቱ ተጀምሮ እስከ ተጠናቋል በተደጋጋሚ ጊዜ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ በንጹሀን ዜጎች ላይ ለደረሰው የህዝብ እልቂት፣ ሞት፣ መደፈርና ስደትና  ሰቆቃ፣ ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ተጠያቂ ናቸው፡፡
  • በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ላይ በግፍ  የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር (ትህነግ) በተቀናበረ እቅድና ስትራቴጂ ‹‹መብረቃዊ ጥቃት››  በጥቅምት 24 ቀን 2013ዓ/ም በመፈፀም ግጭቱንና ጦርነቱ የቀሰቀሰው በሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት ወታደራዊ መከላከያ ጣቢያና ካንፖችን በመዝረፍ ነበር፡፡ በ‹‹መብረቃዊ ጥቃት››ህወሓት  ከሰሜን እዝ መከላከያ ሠራዊት የጦር መሣሪያዎችን ከተለያዩ  የጦር ግምጃ ቤቶች ዘረፉ፣ ከስድስት ሽህ በላይ የሰሜን ዕዝ ወታደሮችን ጨፈጨፉ፣ ከአንድ ሽህ በላይ ከፍተኛና የመስመር አዛዦችን አግተው አሰሩ፡፡ የሃገሪቱን ሰባ በመቶ የጦር መሳሪያና ክምችት በህወሓት ቁጥጥር ሥር ወደቀ፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 22 ቀን 2013ዓ/ም  በአሸናፊነት መቀሌን ተቆጣጠረ በህወሓት የተዘረፉ መሳሪያዎችን በማውደምና በመማረክ የተጠናቀቀ ድል ነበር፡፡ ከወራቶች በኃላ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መከላከያ ሠራዊት መቐለን ለቆ ወጣ፣ የህወሓት ኃይል መቐለን ተቆጣጠረ፣ ህወሓት የጦር አበጋዞች ጥቃቱን በመቀጠል ወደ አማራና አፋር ክልሎች ወረራ ፈፀመ ፡፡ የአብይ አህመድ መንግሥት በዚህ  ለደረሰው ጠቅላላ የስብዓዊና የቁስ ጉዳቶች፣ ተጠያቂ ናቸው፡፡
  • 4ኛ/ የኤርትራ መንግስት፤ በተለይም ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፎወርቂ፤ በወታደሮቻቸው ለተፈጸመው ዝርፊያ፣ ግድያ እና አስገድዶ መድፈር፤ እነዚህ አካላት በአንድ ወይ በሌላ መልኩ ለተፈጸሙት የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋዎች እና ግጭቶች፤ ማድረግ የማይገባቸውን በማድረግ ይሁን፤ ማድረግ የሚገባቸውን ባለማድረግ ተጠያቂ ናቸው፡፡
  • ጦርነት በቃን፣ ሞት በቃን፣ መደፈር በቃን፣ ስደት በቃን፣ የአብይ ወሬ በቃን!!!

የአዲስ አበባ ወጣቶች ይፈቱ!!!

ህዝባዊ እንቢተኛነት የቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ይጠራ!!!
የዘረኛና ተረኛ የብልፅግና አንባገነን አገዛዝን፣ ሁሉም ክልሎች ይቃወሙ!!!
የብልፅግና የጦርነት ንግድ በቃን!!! ክላሽን ኮቭ መቶ ሃያ ሽህ ብር እየተሸጠ ልማት የለም!!!
ብልፅግና ኦነግ ሸኔን ያስታጠቀ የኦሮሙማ ዘርፍ ነው!!! ልብ የለም እንጂ!!!

2 Comments

  1. If you include more tegreas who are collaborators and architecture of the systems the criminals would have been hand cuffed. It is not clear why did you include Daniel Kibret in this list is it to please the islamist or what. There are numerous tegreas to be tried including former Ambassadors and activists in US and Europe including Alula Solomon and VOA staffs, Awel Alo in Europe….. Unless these people are included the vicious circle of crime continues at larger scale.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Previous Story

ፍልፈሉ ቀበሮና ቁማር የተጫወተባቸው በጎች! – በላይነህ አባተ

abiy Asafariw
Next Story

ተመዝኖ የቀለለ፣ በትንሹ ያልታመነ፣ ለትልቁ አይሾምም – የዘ-ሐበሻ ሳምንታዊ ርእስ አንቀጽ

Latest from Blog

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የውጪ ግንኙነት የቤተክርስቲያኒቱን የሺሕ ዘመናት ታሪክ እና እሤቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርባታል!!

በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) (ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው) እንደመንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው ጽሑፌ መነሻ የሆነኝ- ባሳለፍነው ሳምንት በአፍሪካ ኅብረት ኔልሰን ማንዴላ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለአንድ ቀን የተካሄደው፤ ‹‹የአፍሪካ  መንፈሳዊ ቀን/The African Spiritual

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ | ስለአማራ ክልል ከነዋሪዎች የተሰማው | አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል” | “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |

የአበባው ታደሰ እና የአረጋ ከበደ ፍርጠጣ አበባው ጉ’ድ ሆነ – “አበባውን ሳትይዙ እንዳትመጡ”|“በባህርዳር ተከበናል፣ ከፍተኛ አዛዦች ተመተዋል”| “እጅ ከመስጠት ውጭ አማራጭ አይኖረንም” ፊ/ማ “ፋኖ መንግ’ስት ሆኗል” ጄ/ሉ |
Go toTop