ዘሐበሻ ድህረ ገጽ ሰሞኑን በብልጽግና ፓርቲ አመራሮች መካከል የተነሳውን የውስጥ ቅራኔ አስታኮ የአብይ ቡድን ተላላኪ በመሆን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ነጥሎ የተከፈተው ሥም ማጥፋት አካል እንደሆነ ተደርጎ በስህተት ሲጠቀስ አይተናል። አቶ ገዱን አስመልክቶ በዌብሳይታችን የተጠቀሰው አይነት ተልዕኮ ያነገበ ሥም ማጥፋት ዘመቻ አካል አይደለንም። አላደረግንም።
በቅንነት የዘሐበሻ ዌብሳይት የከፈተው ዘመቻ መስሏችሁ የወቀሳችሁን አንባቢያን ስለ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ምንም አይነት የስም ማጥፋት ዘመቻ አካል እንዳልሆንን በዚህ ማስታወሻ እንደምትረዱ ትስፋ እናደርጋለን። ዌብሳይትችን እንደ ሁልጊዜው የተለያዩ ነገሮችን እያስተናገደ ለአገር እና ሕዝብ ጥቅም እንጂ ገዢዎችን ለማስደሰት ወይም ለማስከፋት የቆመ አለመሆኑን ዛሬም ለክቡራን አንባቢያን ያሳውቃል።
አልዩ ተበጀ
የዘሐበሻ ዌብሳይት ማኔጂንግ ዳይሬክተር
https://zehabesha.com/contact/