አፍሪካውያን የሚኮሩበትን የነጻነት ፈና ወጊ የኦሮሞ ጽንፈኖች ያፍሩበታል፤ ይጠሉታል። በነሱው ልክ ሊያወርዱት የተገኘውን አጋጣሚ ሁሉ ይጠቀማሉ። በትናንትናው የውሽት ትርክት ላይ እንደቆሙ ዛሬን መኖር ተስኗቸው ነገም እንደጨለመ ያዩታል።
አድዋ ያለሚኒሊክ ለመዘከር መሞከር ልጅን የለናት ተወልደሃል እንደማለት ነው። በአሉ ከሚኒሊክ አደባባይ ወጥቶ አድዋ ድልድይ ላይ ይከበር ማለት ታሪክን ከመሸርሸር የመነጨ የበታችኝነት ስሜት የወለደው መድሃኒት የለሽ በሽታ ነው። የአድዋ ድልድይ ትንሽ መንገድ ላይ ናት፤ ምኒልክንና ታሪካችንን እንዲሁ ለማሳነስ የተወጠነ የኦነጋውያን ቀቢጸ ተስፋ ነው። ይህን የወሰነው የጫካው ኦነግ አይደለም በመንግስት ውስጥ የተንሰራፋው ባልጊዜው ኦነግ እንጂ። ሽኔ ኦነግ ነው ኦነግም በብልጽግና ፓርቲ ውስጥ ሃገር ለማፍረስ ከውያኔ ጋር የሚሰራ አካል ነው።
እኒህ የታሪክ ስንኩላን ዛሬ ከሚኒልክ አደባባይ ውጭ ይከበር ሲሉ ነገ ምናላባት ስንዳፋ ያደርሱታል ቀጥለውም የምን አድዋ ሊሉን እየተዘጋጁ እንደሆነ እንረዳለን። ታሪክን እያለዘቡ እየሽረሸሩ ማፍረስ ማለት ይህ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በማያዳግም መልኩ እምቢታውን የሚያሳየው ሁልጊዜም ወደሚከበርበት አደባባይ በእቢተኝነት ሄዶ ሲያከብር ነው። ኦነጋውያን በተለያየ መልክ ታሪክን ለማጥፋት የራሳቸውን የውሸት ትርክት ለመትከል ጥረት ማድረጋቸው ይቀጥላል። መልሳችን ግን ወይ ፍንክች ነው።
የኦዴፓ ቀንደኛ ብልጽግናዎች ልባቸውን አሁንም ለኢትዮጵያ እንዳልሰጡ ብዙ ማሳያወች አሉ። ይህ አንዱ ነው። መገንጠሉ ቢቀር አሁንም የበላይነቱን በጥብቅ የሚቆሙለት እንደሚሉትም ከሆነ የሚሞቱለት አላማቸው ነው። በህዝብ እኩልነት ላይ የተመሰረተች ኢትዮጵያ ህልማቸው አይደለችም። ዛሬ ግብግቡ በአድዋ አደባባይ ነገ መስቀል አደባብይ ከዚያም ፊንፊኔ ኬኛ ይቀጥላል።
ለዚህ ነው ስለ እኩልነትና ስለሰወች መገፋት ሲወራ የሚያንቀጠቅጣቸው። የታሪክ አንካሳወች የሚሆኑት። ሃሳብን በወጉ ከማቅረብ ይልቅ በድብቅ ተንኮል ላይ ተኝተው በበታችነት ስሜት የሚዋኙት። የበላይነትና የማጠቃለል ስሜታቸውን የጠበቁ እየመሰላቸው ታሪክን ሲገዳደሩና ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካዊ ድንቅ ስም ያላቸውን ዝቅ ለማደርግ የተለመድ ለቅሶ የሚያሰሙት።
ወያኔ በመከፋፈል የገዛውን፣ የበዘበዘውን ኦነጋውያን የቁጥር የበላይነት አለን ብለው ስለሚያምኑ በመጨፍለቅ እውን ሊያደርጉት እየባከኑ ነው።እንደአስተማሪወቻቸው ታሪክን ፤ዘርን ለማጥፋት የሚባዝኑትም ለዚሁ ነው። ብዙሃን የሞቱለት የእኩልነት፤ የነጻነት ትግልና ታሪክ ለኦነጋውያን የሚዋጥ አይደለም።
የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን አድሃሪና ሁሉ ኬኛን ስግብግብነት በመተባበር ማምከን አለበት። ዛሬ የአድዋ በአል ይሁን እንጂ የታሪክ ሽሚያውና ትርክቱ እግር እየሰደደ ነው። ዝም ከተባሉ የዛሬዋ አዲስ አበባን ነገ ላይ አናገኛትም። ይህ ደግሞ የሁሉም ትግል ነው።
ትግሉ የጋራ ነው። እምቢተኝነቱ የውል ነው። በተናጠል የሚገኝ ድል የለም በእብሪተኞች መዋጥ እንጂ። ኦነጋውያን ተስፋ የሚያደርጉት ወያኔ በቀደደላቸው በዘር የተከፋፈል ህዝብ ምንም አያደርግም ነው። አድዋ ዘር የለውም ከኢትዮጵያ አልፎ ለሁሉም ጥቁር ህዝቦች የድል ኩራት ነው።
አንዳንዶች የትስ ቢከበር ምን ችግር አለው ይሉናል። ታሪክን ቀስ በቀስ መሽረሽርና ብሎም ማፍረስ ችግር የለውም ካሉን እነሱ ኦነጋውያን ናችው። ዛሬ አንድ ጫማ ከሰጧቸው ነገ በሜትር ይወስዱታል። ማስቆም አሁኑኑ ነው።
የአድዋ በዓላችንን በምኒልክ አደባባይ እንዘክራለን