February 22, 2022
18 mins read

ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሆይ! የኢትዮጵያን ህዝብ ለምን ያህል ግዜ ይከዱታል? – ፊልጶስ

የእፍሪካ አምባገነኖች ወደ ስልጣን ሲመጡ ለህዝባቸው  የማይገቡት ሰናይ  ቃል የለም፤ ጦርነትን ወደ ሰላም፣ ድህነትን ወደ ሃብት፣ ኋላቀርነትን ወደ ሥልጣኔ፤ በአጠቃላይ ለህዝባቸው “ምድራዊ ገነትን” እንፈጥራለን እያሉ ይምላሉ፤ ይገዘታሉ። ይህን ሲሉ ደግሞ ከ´ነርሱ በፊት የነበሩትን “በዳቢሎስ” መስለው፤ ‘ራሳቸውን ደግሞ “መላዕክት”  አድርገው ነው።  ውለው ሳያድሩ ግን´ምድራዊ ገነትን´ እንፈጥራለን ያሉ ገዥዎች ፤ ታግሎና መስዋአት ከፍሎ ለሥልጣን ባበቃቸው ህዝብ ላይ “ምድራዊ ሲኦልን”  ይፈጥሩለታል። መከረኛ የእፍሪካ ህዝብ እንደ ገና እንደ አዲስ ትግልን  ¨ሃ´ ብሎ ይጀምራል።

ዛሬ አገራችንን የገጠማት ደግሞ ከአፍሪካ አምባገንኖች የባሳ  የህልውና እና  የአገር አንድነት ጥያቄ ነው። የመኖርና ያለመኖር።

ለስር-ነቀል ለውጥ  የተካሄደው ትግል፤ መሪ ድርጅት አ’ቶ፤ ወያኔም ወደ መቀሌ ተሸኝቶ፤  በአቋራጭ እነ ኦዲድ ተረኞቹ መምበሩን ሲይዙ፤ ጠ/ ሚ አብይ አህመድ ብዙ ተስፋ ሰጭ ቃል ገብተውልን ነበር፤ በተለይም  በኢትዮጵያዊነት ላይ፤  ያለፈው የወያኔ አገዛዝ ጸረ-ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት መሆኑን አብስረው። አብረው ያቦኩና ይጋግሩ እንዳልነበር ሁሉ።

የኢትዮጵያ ህዝብም የተደገሰለትን ሳያውቅ፤  ´እግዚአብሄር በቃችሁ ሊለን ነው¨ ብሎ ፤ ከዳር እስከ ዳር ድጋፋን አሳየ። ህዝብ ለወያኔ ተላላኪ ሆነው የሰሩትን ግፍና የዘረፋትና ሃብት  ሁሉ ወደ ጎን ትቶ መጭውን ግዜ  አስቀድሞ  ´እኛ እናሻግራችኋለን እመኑን´ ሲባል አመነ። እውነቱን ለመናገር በወቅቱ የተጥራጠሩ ስዎች በጣም ጥቂቶች ነበሩ።

“ውሻ እንደ አሳዳጊው ነው” እንደሚባለው ውሎ ሳያደር ግን እንደማንኛውም የአፍሪካ እምባገነን መሪዎች ሁሉ የተገባው የኢትዮጵያዊነት ቃል ወደ ኦሮሙማ -የተረኝነት አገዛዝ ተሸጋገረ። ያሳደጋቸውን የጡት አባታቸውን የወያኔን  የጎሰኝነትና የመንደርተኝነት መንገድ  ተከትለው መንጎድ ጀመሩ።

ዜጎች በኦሮሙማ አዝማችነት በማንነታቸው ከያሉበት ማጽዳቱና ማረዱ  ተፋፍሞ እስከዚህ ሰዓት ድረስ ቀጠለ።

በጎሳ ላይ የተመሰረተው  ህገ- መንግሥት ምንም ዓይነት ዶሞክራሲ እንደማያመጣ እየታወቀና ምንም አይነት ነጻ ተቋማት በሌሉበት፤ ኦሮሙማ ብልጽግና  ከአጫፋሪዎቹ ጋር ብቻውን ተወዳድሮ ፤ ብቻውን አሸንፎ ፤ ጠ/ሚ አብይ አህመድ “ግግም”  ብለውና የገቡትን ቃል ሁሉ ቅርጥፍ አድርጎው በልተው  ´ህጋዊ መንግሥት ነኝ´´ አሉ።
 ይህ ሁሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ መከዳቱንም እያወቀ፤ ሌላው ቢቀር፤ ” ከዛሬ -ነገ በሰላም ውየ እገባለሁ” ፣ “በማንነቴ መገደሌ ይቆማል”  ብሎ ተስፋ በሌለበት፣  ተሰፋ ቢያደርግም ፤ “ነፍጥኛን ሰበር ነው” እየተባለ ባደባባይ መታዎጅ ጀመረ።  ብዙ የሚደሰኩኮርለት የኢትዮጵያዊነት ተስፋም እንደ ጎም ተነነ፤ እንደ ማለዳ ጤዛ ´ረገፈ።
 የዳቦ ስም በተሰጠው በኦሮሙማ የሚመራው የኦነ ሸኔና አጫፋሪዎቹ  ከወለጋ እስከ ቢንሻንጉል፣ ከሰሜን ሸዋ እስከ መተከል ድረስ የሚፈጸመው የዘር ማጽዳትና ማሳደድ  አልበቃ ብሎ፤ ´ፊንፊኒ ኬኛ´ ተብሎ የአዲስ አበባ ህዝብ ዘመናት ሙሉ ተዋህዶ በገነበው ከተማ ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ መኖር ጀመረ።  ከስቃይና ከመከራ አትውጡ የተባልን ይመስል ፤ እሹሩሩ ሲባል ከነበረው ወያኔ ጋርም ጦርነት ተጀመረ፤

ታዲያ ጠ/ ሚ አብይ አህመድ ፤ የገቡት ቃልና  የብልፅግና ቱርፋተዎት፤ በመደመር ፋንታ ተቀንሰን፣ በሰላም ፋንታ ጦርነት ገብተን፤ መንግሥት አለበት በሚባል አገር ውስጥ ወያኔና ኦነግ-ሸኔ የተባሉ የ’ርሰዎ ባልጀሮች  በሰው ልጅ ደም ይራጫሉ።

ከወያኔ ጋር የሚደረገው ጦርነት  እርሰዎ ጠ/ ሚ አብይ አህመድ እንዳሉት የህልውናና ኢትዮጵያን የመታደግ ጦርነት ነው። ለኢትዮጵያዊያን ግን ይህ የህልውና ጦርነት ኦነግ  ሸኔንም ይጨምራል።   ከርስዎ በበለጠ ደግሞ ህዝብ ይህን እውነታ ጠንቅቆ ያውቃል፤ ምክንይቱም የጦርነቱ ገፈት ቀማሽና በታሪካችን ተሰምቶ የማያውቀው ጭቃኔ  በወያኔና በኦነግ ሸኔ ወይም በኦሮሙማ ብልፅግና ተፈጽሞበታልና።

ታዲያ ወያኔን በመንግሥተዎ  አመራር ሰሜን ሸዋ ድረስ ሰተት አድርገው ካስገቡ በኋላ፤  “በመደበኛ ጦር  ወያኔን ማሸነፍ አይቻልም፤ ጦርነቱ ህዝባዊ መሆን አለበት።”´ ስላሉ ፤ መከረኛ   ህዝብ በተለይም በአፋር፣ በጎንደር፣ በውሎ፣ በጎጃምና በሸዋ የሚኖሩ  ፋኖዎች  በ ጦርነቱን ተቀላቅለው፤ ቤተ-መንግሥተው የተጠጋውን ወያኔን ፤ በበዙ የህይወት መሰዋአትነት፤ ሌላው ቢቀር ለ´ርሰዎ ስልጣን ስጋት እንዳይሆን አድርገው ወደ መጥበት ሸኙት።   ነገር ግን አሁንም እንደ አለመታደል ሆኖ  የ´ርሰዎ መንግሥት  ከወያኔ ጦርነት ጋር በተያየዘ ሶስት ግዜ የኢትዮጵያን ህዝብ ከዱት፣ ዋሹቱ፣ አውናበዱት፣ ግራ አጋቡት ወይም አዘናግተው አስጨረሱት ወይም  ለሌላ ዙር የወያኔ ወረራ አጋላጡት፤ ይኽውም፤
1/ በመጀምሪያ ዙር ጦርነት ´  ዱቄት ´ ላደረጋችሁት ወያኔ  ትግራይን እስረክባችሁ ስትወጡ ፤ የሰጥችሁት ምክንያት እስከ አሁን  በየግዜው የሚጣረዝ ብቻ ሳይሆን ህዝብ ራሱን እንዳይከላከልና እውነቱን የማወቅ መብቱን እንኳን ነፍጋችሁ፤ በታሪክ ውስጥ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቀውን የምድራችንን ስቃይ ሁሉ እንዲፈፀምበት አደረጋችሁ።
2/ እንደነገሩን፤ በ´ርሰዎ መሪነት  በተደረገው ወያኔን የማጥቃት ዘመቻ  በህዝብ ትብብርና መሰዋአትነት ወያኔን እስከመጨረሻው ይደመሰሳል ሲባል፣ ጎንደር፡ ወሎና አፋር እንኳን ሙሉ በሙሉ ከወያኔ ነጻ ሳይወጣ ፤ የጦሩን ጉዞ እንዲገታ አድርገው ´ድል አደርገናል´ አሉ። እውነታው ግን ወያኔ ግዜ አግኝቶ ዳግም በየአቅጣጨው በየግዜው ወርራ እያካሄደና ህዝብ እያፈናቀለ ነው። በተለይም የአፋር ህዝብ ወያኔን ብቻውን እንዲዋጋ የተተውበት ሁኔታ የሚያስተዛዝብ ብቻ ሳይሆን፤ ሆን ተብሎ በኢትዮጵያዊነቱ  ጥቃት እንዲደርስበት እየተደረገበት ነው።
3/ በስንት መሰዋትነት የታሰሩትንና የስሜኑን ጦር እንዲመታ ያቀዱና ያሰፈጸሙ፤ ብሎም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሊረሳ የማይችል ግድያና ዝርፊ እንዲደረግ ያደረጉትን፣ ማንኛውንም መንገድ  ተጠቅመው ኢትዮጵያን ከማፍረስ ወደ ኋላ የማይሉትንና  አሁን አገራችን ላለችበት ምስቅልቅል የጎሰኝነት መርዘኞች፣ ጎምቱ የወያኔ መሰራቾችና ባለስላጣናትን ከእስር ፈተው ሲለቁ ፤ ምን አልባትም  የኢትዮጵያን ህዝብ የመከዳት ስሜት መግለጽ ስለማልችል ´´ርሰዎ ሲሰሙ እንደደነገጡት ሁሉ እኛም ” ደንግጠናል” ።

ታዲያ በዚህ ሁሉ መወናበድ፣ የአቋም እጦትና፣  ህዝብን የመካድ  “የፓለቲካ ቁማርና ሴራ”  ውስጥ ፤ ከወያኔ ጋር ለመደራደር ሽር-ጉድ እያሉ መሆነዎትን ብቻ ሳይሆን ፤  በ’ራሰዎ አንደበት ” ተሸንፋል ” የተባለውን የወያኔን ፍላጎት ለማሳካት፤ ወልቃይትንና ራያን  ከህዝቡ ነጥቀው በፌደራል ስር ሊያደርጉ መሆነዎ እየተሰማ ነው። ይህ ´ርሰዎን ብቻ ሳይሆን አገሪቱንና መላውን የኢትዮጳያ ህዝብ የምን ያህል ዋጋ ሊያስከፍለው እንደሚችል ሳስብ፤ ወደ አንድየ አንጋጥጣለሁ።ጠ/ሚ አብይ አህመድ ሆይ! እንደ ኢትዮጵያ ያለ ለዘመናት ያልተደፈረ ነጻነትና ብዙ ታሪካዊ ጠላቶች ያሉት፤ ውስብስብ ችግር ያለበት ህዝብ መምራት ምን ያህል ከባድ መሆኑን ማንም ጤነኛ ሰው ይገነዘባል። በሌላ በኩል ግን ከወያኔና ከኦነግ -ሸኔ ጋር የሚደረገውን ጦርነት  ለዚህ ያበቁት የ´ርሰዎ መርህ አልባ አመራርና  ዛሬ ተናግረው ነገ የማይደግሙት ሁሌም  በጭብጨባ የታጀበው ንግግረዎትና መሬት ላይ ያለው እውነት  ያለመገናኘቱ ነው።

እንደሚያውቁት ወደ ሥልጣን መመበሩ እንደ ወጡ የነበረዎት የህዝብ ድጋፍና አሁን ያለውን ለመገመት ሞክረው ከሆነ፤  እንደ ´ርስዎ የህዝብ ድጋፍ ያለው መሪ፣  ነገር ግን ደጋፊውን በየመንገዱ እያንጠባጠበ ፤ የኢትዮጵያን ጠላቶች እያጠናከረና በር እየከፈተ ፤ የህዝብንና የአገርን ህልውና ፈተና ውስጥ የከተተ የለም።

አሁንም በእውነት -ለእውነት፤  የሁላችን መዳኛ የሆነችውን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ካስቀደሙ ፤ በተለይም ወያኔንና ኦነግ ሸኔን ለማስወገድ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ትላንቱ አሁንም ከጎነው ለመሆኑ ማረጋገጫ አያስፈለግዎትም።

ምክንያቱም አገርና ህዝብ ከ´ርሰዎ ትላንት ከመጣው መንግሥተዎም  ሆነ ከፓለቲካ  በላይ መሆኑን ለሺ ዘመናት ያስመሰከረ ህዝብ ነውና ።

የኢትዮጵያ ህዝብ “እንደገና ዳቦ ” ከውጭም ከውስጥም እየነደደ ያለው፤ በ´ርሰዎ አቋም ወይም መርህ አልባ አመራርና  በጦርነት የተገኘውን ድል በፓለቲካም  ለማስጠበቅ ባለመቻለዎ ነው። የውጭ ኃያላንም የሚቀልዱብን የ’ርስዎን አቋምና መርህ አልባ  መንግሥተዎን ጠንቅቀው ስላወቁ ነው።

አሁን የውጩ ጣልቃ ገብነት ጋብ ያለ ቢመስልም ወያኔ እስከአልጠፋ ድረስ ችግሩ ነገ – ከነገ ወዲያ ተባብሶ ይቀጥላል፤ ወያኔም  ኢትዮጵያን ለማፍረስ መቸም ቢሆን እንቅልፋን አየተኛም።  በተግባርም አሳይቷል።
የኢትዮጵያ ህዝብ  እንደ ትላንቱ  ማንኛውንም መሰዋአትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው፤  ከመንግሥተዎ  የሚጠብቀው ግልጽ፣  ቆራጥና መርህ ያለው  የማዳግም ´ርምጃ  ነው። ከአሁን በኋላ የጎንደርም ሆነ የውሎ ወይም የአፋር ህዝብ በወያኔ ስር እንዲወድቅ የሚፈቅድ ኢትዮጵያዊ የለም። እየኖርምም።  ትግራይም ከወያኔ ነጻ መውጣት እንዳለባት መንግሥተዎ ለህዝብ በመያሻማ ቋንቋና በተግባር ማሳየት አለበት።

ኦነግ ሸኔን በተመለከተም እንደ ወያኔ ሁሉ የማያዳግም ´ርምጃ መወሰድ አለበት። ለኢትዮጵያ ህዝብ ኦነግ ሸኔ ማለት በመንግሥተዎ የሚመራና ትዕዛዝ የሚቀበል የኦሮሙማ ብልጽግና እካል ነው። ስለዚህም  ተቀበሉትም፣  አልተቀበሉት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እየተገደለ ከሚጠፋ፤ እየገደል መታገልን ይመርጣልና። ከዚህ በኋላ መንግሥተዎ ኃልፊነቱን ከተወጣ፣ ተወጣ፤  እሰየው። ያለያ ግን እንዳለፈው ግዜ ሬሳ እየቆጠረና በማንነቱ እየተሳደደ ወይም በ’ርስዎ ማባባያ ቃላት እየተታለለ ይቀጥላል ብለው  አያስቡ።  ህዝብ  ማንኛውንም መንገድ ተጥቅሞ ራሱን እንደሚከላከል ግልጽ ሊሆንለዎ ይገባል።  መንግሥት ነኝ ካሉ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ የማንም ሳይሆን የመንግሥተዎ ቀዳሚ ተግባር ነው።በማጠቃለያም አንድ መቶ ሃያ ሚሊዮን የኢትዮጵያን ህዝብ ይዘው፤ የዳቦ ስም የሰጡትን ኦነግ-ሸኔንም  ሆነ ወያኔን የማያሸንፋበት፣ እንዲሁም የውጩን ጣልቃ ገብነት የማይቋቋሙበት ምክንያት የለም፤ እንደሚባለው የኦርሙማ ዓላማ ከሌለዎት።  ´ “ስለ ኢትዮጵያ ከሆነ አንገቴን እሰጣለሁ ” አይደል ያሉት?

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!
———–//——-ፊልጶስ
የካቲት 2014

E-mail: Philip Osman gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop