ለ ዕዉነት እና ዕዉቅና ንፍገት ከክህደት በምን ይለያል  

በአገራችን ለዕድገት በሚደረግ ጉዞ የኋላ የመሆን ሚስጥር የህዝብን ስሜት እና ብሶት ከለመስማት እና መረዳት መሆኑን የሚመለከተዉ ህዝባዊ እና መንግስታዊ አካል የሚረዳዉ ቢሆንም በምን ቸገረኝ የተጠያቂነት አሰራር አለመኖር እና ቢኖርም በተግባር አለመዋል በተቃራኒዉ ለህዝብ እና ለአገር ለሚሰሩት ዕዉነትን እና ዕዉቅናን ለመንፈግ የሚያስችል ከለላ እና ምሽግ ሆኗል፡፡
ለወትሮዉ ማንኛዉም የሚመለከተዉ ዜጋ በግል ይሁን በወል አቤት ሲል ከእኛ በላይ ለህዝብ ብሶት የሚታመም የለም ስንናገር ስማን ፤ የምንልህን ዐሜን በል መባል በኢትዮጵያ አዲስ አልነበረም ፡፡

ዛሬ ደግሞ ለህዝብ ያለሳለሰ ዕንባ እና ዕሮሮ ዕዉነተኛነት በመመስከር ለህዝብ እና አገር መዳን ከሚመሰክሩ ባለስልጣን  የምንረዳዉን መሬት ላይ ያለ ዕዉነት ሀሰት ነዉ የሚሉ ሌሎች መኖራቸዉ ስንሰማ ቀናት ተቆጠሩ፡፡

ህዝብ ስለ አገር እና ስለ ራሱ አያዉቅም ስለ ሁሉ እኛ ነን የሚሉት ሁሉ ከመኃላቸዉ ስለ ዕዉነት እና ርትዕ የሚያዉቅ ሲነሳ የነሱ አዳኝ እና ተከላካይ ሆኖ መሬት ላይ የወረደዉን ጉድፍ  ማሳየቱ እንደ ጥፋት ከማሳየት አልፎ  እርሱም አያዉቅም እኛ ነን ስለ ርሱ የምናዉቅ ለማለት መሞከር አስከየት ይሆን፡፡

በአገራችን ህዝብን የሚሰማ ለህዝብ እና ለአገር የሚኖር ሊከሰት ሲል በጩኸት እና በማን አለብኝነት እኔን ስሙኝ ባዮች የሚረባበሹት አስከ ምን ድረስ ይሆን ፡፡

በ፴(ሠላሳ ) ዓመት ለአገር እና ለህዝብ ዕድገት የሰሩትን በስራ ቢገልጡት እንኳንስ ራሳቸዉን እና መንግስትን ሊታደግ የሚችል ህዝባዊ ከፍተኛ ባለስልጣን ፤የድርጅት አባል ወንድም ቀርቶ ዓለም ቢተባበር ባልሰጉ ነበር ፡፡

ህዝብ ከዓመታት የቃላት ጋጋታ ይልቅ የአንድ ጊዜ የተግባር ሠዉ እንደሚረዳ ከጥንት እና ከትናንት የአገራችን ታሪክ ወደ ኋላ ዞሮ ማየትን ይጠይቃል ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  "… አላውቅም ! የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን … ? " ባዮቹ ፤ ቃየንአዊያን እና ባቢሎናዊያን አኛ  አይደለንምን? - መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

ዳሩ እንዳለመታደል ሆኖ እና አገር ከራስም ሆነ ከቀደመ መከራ እና ችግር እንዲሁም ከወዳጂ እና ጠላት ዉድቀት በስተጀርባ ከነበሩት ህፀፆች የሚማር እና የሚያስተምር  የፖለቲካ ልሂቅ  ሾተላይ አገር ምድር ላይ መሆናችን ነዉ ፡፡

ስለ ራስ እና አገር ዕዉነት እና ትዝብት መናገር እና ማስተማር ዉጉዝ በሆነባት አገር ስለ መጪዉ ዘመን ብሩህ ተስፋ ለማለም ከንግግር ወደ ተግባር ለመንደርደር ለዕዉነት እና የዕዉነት( ተግባር ) ባለቤቶች ቦታ መስጠት እና ዕዉቅና መቸርን ይጠይቃል፡፡

በዕዉነተኛ ስራ ታሪክ ሰርተዉ ያለፉትን ሆነ ያሉትን ዕዉቅና በመንፈግ እና በክህደት ታሪክ በመመስረት ዘላቂ እና ዕዉነተኛ አወንታዊ ለዉጥ መሻት ከታሪካዊ ስህተት አይለይም፡፡

በሁላችንም ዘንድ እንደሚታወቀዉ በብሄራዊ ደረጃ ከንግግር እና ከመደነጋገር ባሻገር አንድም ጠብ ያለ ፈቅታ እና ከፍታ በህዝብ እና አገር ላይ ጠብ የሚል የለም ፤ አልነበረም ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ እና ሉዓላዊነት አሳልፎ በመስጠት ህዝቧን ለሁለንተናዊ ዉስብስብ ዕልቂት እና ስደት  ለዓመታት ለሚሰሩት ዕሬት ወተት  በማለት ከሰሩት ክፉ ስራ በተቃራኒ የመልካም ስም እና ዕዉቅና መስጠት እና ይህም ለአገራቸዉ አንድነት እና ዕድገት ሲሉ ራሳቸዉን መስዋዕት ያደረጉትን መረሳት ወይም መካድ በትልቁ እንደ ህዝብ ዋጋ እያስከፈለን ነዉ ፡፡

ለዓብነት ለቡድን እና ለፖለቲካ ጥቅም ትርፍ ሲባል አገርን ለባዕድ ፤ ህዝብን ለድህነት ፣ ስደት እና ለሞት በመመማገድ የሰሩ እና ያሰሩ  መታሰቢያ ፣ ዕዉቅና እና የቁም ሀዉልት በመስራት ተጠምደን እና ተተብትበን ኖረናል ፡፡

አሁንም ከመከራ የማንማር የመከራ እና የሙት መንፈስ ከዳሚነት አባዜ ዉስጥ እንዳለን የሚያሳይ ሁነት ዉስጥ ስላለመሆናችን ምንም ፍንጭ የለም ፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  እምቢ ለአፋኝ ወታደራዊ አገዛዝ፤ የሽግግር መንግስት አሁን ይቋቋም !!

እንዲያዉም ካለፈዉ ተነስተን ስለ ሀገር እና ፍቅር  ብለዉ ራሳቸዉን አሳልፈዉ ለሰጡት ቀርቶ በዚህ ሰዓት ስለዕዉነት ፤ ፍትህ እና ርትዕ  ሲባል ዕምቢ ለአገሬ ፤ዕምቢ ለክብሬ ፤ ለዳር ድንበሬ የሚሉትን የሚገባዉን ክብር እና ዕዉቅና መስጠት ቢቀር ዓላማቸዉን ዓላማ ብለን ለመረዳት ዳተኞች ሆነናል፡፡

ይህ ዳተኝነት ከዉርደት፣ ስደት እና ሞት እንደማያድነን እያወቅን እያየን ለሶስት አስርተ ዓመታት ሁላችን ኢትዮጵያዉያን በተለይም ኢትዮጵያን ለማጥፋት በጥፋት ቃብድነት የተያዙ ኢትዮጵያዉያን በኢትዮጵያዊነት ማንነት በቁም የሞት ሞት ዓሜን ብለዉ እንዲያስተናግዱ የተሰሩ አስኪመስሉ አሁንም የክፉዎች የጥፋት ሲሳይ ሆነዉ እያስተናገዱ ሲሆን ድረሱልን የሚሉት ደረሱብን የሚሏቸዉን ነዉ   ፡፡

ለዚህ ሁሉ መከራ እና ስቃይ ዘመን መራዘም አይነተኛ ምክነያት የህዝቦች በተለይም በማንነታቸዉ ሞትን ዓሜን ብሎ መቀበል ልማድ ሆኖ ለአንድነት እና ነፃነት ዕምቢ ከማለት እና በአንድነት ከመደራጀት ይልቅ በምን አገባኝ ዳር እና ዳር በመቆም  ሞት እና ዉርደት መጠበቅ ሆኗል፡፡

የዚህ ዘመን ዋኖችን ብንጠቅስ እነ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ፤ ኮ/ል ደመቀ ፣አስማረ ዳኜ ፣ ዘመነ ካሴ ፣ ፻  ዓለቃ  ማስረሻ ሰጠኝ ፣ ሻለቃ መሳፍንት፣  ሊቀ ጳጳስ ኤርማያስ፣ ሊቀ ጳጳስ አበርኃም እና ዛሬም እነ ክቡር ፀጋ አራጌ የከፈሉትን እና እየከፈሉ ያሉትን ብሄራዊ ታሪካዊ ዋጋ ህዝብ እና አገር በማዳን ትዉልድ እና ነፃነት ለማስከበር እና ከማስተግበር  ጋር የማስቀጠል ትግል መሆኑን ህዝብ የሚረዳ ቢሆንም ጥቂቶች ግን ይህን ልዩ መልክ ሊሰጡት ይፈልጋሉ ፡፡

ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሆነ ሁሉ ለራሱ እና ለአገሩ ክብር እና ዳር ድንበር መከበር ለሚደረገዉ ሁሉን አቀፍ ተጋድሎ በአስተሳሰብ እና በገቢር ለዕዉነት እና ለርትዕ ዕዉቅና መስጠት ይኖርበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  ስለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምክክር ጉባኤ አንዳንድ ነጣጥቦች - ኘሮፌሰር ኀይሌ ላሬቦ

ለራስ እና ለአገር ክብር ዕምቢ ማለት ለዕዉነት እና ለዕዉነተኛ ዋኖች መታሰቢያ ከማድረግ በላይ ዕዉቅና በመስጠት ለትዉልድ ንቃተ ህሊና ከታሪክ በመማር ዓይነተኛ የራስ ማንነት እና ነፃነት በመገንባት እና በማስቀጠል ዕዉነተኛ እና ዘላቂ ብሄራዊ አንድነት እና ዕድገት ለማስገኘት ብርቱ ፍኖተ ኢትዮጵያ ነዉ ፡፡

የራሳችን ህልዉና እና ነፃነት ከፈለግን ለራስችን እና ለአገራችን ያለንን ዋጋ ከፍ በማድረግ ለአገራቸዉ እና ለህዝባቸዉ ብሎም ለራሳቸዉ ማንነት እና ሁለንተናዊ መብት መከበር ዕምቢኝ ባይ የአገር ባለዉለታወችን መልካም ተጋድሎ መመርመር ፣ መመመስከር እና መዘከር ይኖርብናል፡፡

ዕዉነተኛ ማንነትን እንዳንረዳ ወይም እንድንክድ ምክነያቱ ድንቁርናችን  በመሆኑ ከድንቁርና ጉድጓድ ለመዉጣት ብቸኛዉ በድንቁርና ጭለማ ዉስጥ መሆናችንን ተረድተን ለዕዉቀት እና ዕዉነት ፍለጋ ስንተጋ ነዉ ፡፡ ጥበብ እና ማስተዋል በድንቁርና ጭለማ ጥላ ስር ሆኖ ማሰብ ራሱ በባርነት ቀንበር ሆኖ ነፃነት ከመጠበቅ አይለይም ፡፡ ለሁላችንም በሆነች እናት አገር ምድር ለሁላችብ ዕረብ የሚያስገኘዉ ለዕዉነተኛ የተግባር ሠዎች ዕዉነተኛ ዕዉቅና እና ክብር ስንሰጥ እና ለዚህም ለዕዉነት ከልብ ለለዉጥ ስንቆም እና ስንለወጥ ብቻ ነዉ ፡፡

የዕዉነት እና ዕዉቅና ንፉግ በመሆን   ለሀሰት እና አስመሳይነት አድር ባይ ልማድ ሰለባ ሆነን በራሳችን ላይ የምናስበዉ ክህደት በሚያልፍ ጊዜ የማያልፍ ሠባራ ስም ከማስከተል አልፎ ለተዉልድ እና አገር ዕዳ እና ፍዳ ማዉረስ እንዳይሆን  እንደ ህዝብ አሁንም ሊታሰብበት ይገባል፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ

ማላጂ

ይሄ ቅድስተ ስላሴ የሚገኘው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ መበቃብር ነው።ጉዳት ደርሶበት ነበር።በአብይ አህመድ ትእዛዝ እንዲታደስ ሆኖአል።(ዳፍ)

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share