February 13, 2022
12 mins read

ሥልጣናችሁን አስረክቡ!   ለጥንቱ  ኢህዲን፣ ለትላንቱ ብአዴን፣ ለዛሬው የአማራ ብልጽግና

Biaden 1ከዚህ በታች  የማሰፈረው ሃሳብ እንደመነሻ ነው። ስለዚህም  በሃስቡ የሚያምን እንዲደግፈው፣ የማያምን  ደግሞ እንዲተችበት ወይም አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብ  እንዲሰጥ፤ በአጠቃላይ  ለአገራችን  በተለይም  ለአማራ ብልጽግና  መፍትሄ  የሚሆንና ገንቢ ሃሳብ ለማሸራሸር  መሆኑ  በቅድሚያ ማስገንዘብ እወዳለሁ።

በኔ እምነት ይህ ስልጣንን ለህዝብ አሳልፋ የመስጠት ምክረ-ሃሳብ ለአማራ-ብልጽግና ብቻ ሳይሆን ለማዓከላዊ አገዛዝ  ለብልጽግናዎች  ብሎም ለመላው አገሪቱ  የሚበጅ ነው ብየ አምናለሁ። ነገር ግን  ወያኔም ወያኔ ነው። ተረኞቹ  ኦሮሙማዋችም ‘”ኢትዮጵያን ተቆጥጥረናል፣ የማይነቃነቅ ልዩ ኃይልም ገንብተናል፤ ነፍጠኛንም ከግራ-ከቀኝ እያጠቃናቸው ግራ -እያጋባናቸው  ነው።”’  ስላሉና ፤ ወያኔ ራሱ ጠፍጥፎ የሰራቸው  ኦሮሞን እንወካላለን የሚሉትንና ለአማራ እንታገላላን የሚሉትን በተላላኪነት እያባላ ሃያ ሰባት ዓመት እንደገዛ ሁሉ ፣ ተረኞችም በተራቸው  አማራንና ወያኔን እያባላን እስከቻልን ደረስ እንገዛለን፡ ካለያ ” ማርና ወተት የሚፈስባትን ኦሮሚያን እንገነባለን።  ብለው  ከብዙሃኑና ከሰላም ወዳዱ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎትና ዓላማ ውጭ ፤ በስሙ የሚምሊና ይሚገዘቱ በመሆናቸው ብቻ ሳይሆን፤ ከዚህ በፊትም  ለቁጥር የሚያስቸግር አገራዊ ምክር ቀርቦላቸው ያለተቀበሉና በአገራዊ ምክክር ስም እድሚያቸውን እያውናበዱ፤ የፓልቲካውን ቁማር በልትነዋል ብለው ያመኑ  በመሆናቸው ነው።

ቅንነት፣ ህዝብንና አገርን ማስቀድም ቢኖርማ የአሁኖቹ ተረኞች ከጡት አባታቸው ከወያኔ አወዳደቅ በተማሩ ነበር።  ሃቁማ ማንም በጎሳ ተደራጅቶና በጎሳ ተከልሎ ፤ አንዱን የበታች፣ ሌላውን የበላይ አድርጎ የዘር ማጥፋት ወንጅል እየፈጸሙ የሚጸና አገዛዝ  የለም፤ የግዜ ጉዳይ እንጅ  እንደተለመደው አገርን እና ህዝብን ለመከራ ዳርጎ መሸኘት አይቀርም፤ ያውም ከውርደትና ከሃፍረት ጋር።

የሄደው ሲመጣ፣ የመጣው ሲሄድ
መውጫና መውረጃው ሆኖ ያአገር መንገድ፤
ብዘራው አይበቅል፣ ቢበቅል አያፈራ
መጠላለፍ ብቻ ሆነ የ´ኛ ሥራ።

በተለይም በአሁኑ ሰዓት የአማራ ብልጽግና የሚባለው ቡድን ፡ የተላላኪነቱን ሥራ እንኳን መስራት ተስኖት፤  ህዝብን ከማስጨረስ አልፋ፣ አገርንም እያጠፋ ነውና “ ከነወንጀልህ ብዙ እድል አግኝተሃል፤ ከአሁን በኃላ ግን በቃህ።” መባል ስላለበት ነው። ህዝብም ለማይቀረው ትግል ራሱን ማዘጋጀት አለበት።

እናም የአማራ ብልጽግና ሆይ፤ ብዙ በልተህ ብዙ ለማበት፤ ብዙ ጠጥተህ ብዙ ለመሽናት ፣በአማራ ህዝብ ላይ ብሎም በኢትዮጵያ ላይ የሰራህው ግፍ አንደብት ሊገልጸው አይችልም፤ መጸሃፍ  ሊከተበው ቃላት አያግኝም።

ግን በገሃዱ ዓለም የሚታወቀውንና ኢትዮጵያን ለዚህ ያበቃችኋት ከወያኔም ሆነ ከአሁኖቹ ባለግዜዎችና ተረኞች በበለጠ  እናንተ ናችሁ። ምክንያቱም ሌሎቹ ሌላው ቢቀር ኢትዮጵያን የማፍረስና  ነፍጠኛን የማጥፋት ዓላማ አላቸው። እናንተ ግን ትላንትም ሆነ ዛሬ በሆዳችሁ እያሰባችሁ፣ ለሆዳችሁ የምትኖሩና ለሆዳችሁ የገዛ አገራችሁንና ወገናችሁን የሸጣችሁ በመሆናችሁ ነው።

እስቲ ይታያችሁ፤ ኦህዲድ  እንኳ´ ከተላላኪነት ወጥቶ ዛሬ ተረኛ በመሆን  እናንተን ተላላኪ አድርጎ፡ እንደ ወያኔ ሁሉ ኢትዮጵያን ያፈርሳል፡ አማራን ያርዳል።  እናንተ ግን መጸሃፍ እንደሚለው ” ህሊናችሁ በጋለ ብረት እንደ ተተኮሰ ሆኖ ደንዝዟልና–” ከሆዳችሁ ውጭ ሌላ ዓለም የላችሁም። ግን አሁንም ቅዱሱ መጸሃፍ ” እንጀራም የተሰራው ለሆድ ነው፤ ሆድም የተሰራው ለእንጀራ ነው፤ ሁሉንም ግን እግዚአቢሄር ያጠፋቸዋል።” ይላል።

የእማራ ብልጽግና ሆይ! እስከ አሁን በእናንተ ተላላኪነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት የፈሰሰው ደምና የጠፋው የሰው ህይወት ከአዕምሮ በላይ ነው። ከዚህ በኋላ የአማራም  ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ እናንተን የሚሸከምበት ጫንቃ የለውምና በስምምነና በሰላማዊ  መንገድ  የያዛችሁትን የተላላኪነት ኃላፊነት  አስረክቡ።

ያለያ  ግን የኢትዮጵያም ህዝብ ሆነ  በምስለኔነት  የምትገዙት በየቀኑ የሚታረደው ህዝብ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል። ለዚህ ጉዳይ ተፈጻሚነት ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብና ለሰው ልጅ መብት ቁመናል የምትሉ ሁሉ፤  የተደራጀ ትግል ማድረግና እንደ አስፈላጊነቱ ሰላማዊ ሰልፍ  ከማዘጋጀት ጀምሮ  ትግሉ ግቡን እስኪመታ  በአብሮነት መታገል የህልውና ጉዳይ  መሆኑ መዘንጋት የለበትም።

ምክንያቱም ከአሁን በኋላ ህዝብ የሚቀርበት ነገር ቢኖር እንደ በግ እየተጎተተና እንደ አውሬ እየታደነ መገደል ፤ ብሎም አገር አልባ መሆን ነው። እናንተን በማሰውገድ ግን ራስን ከመከላከል አልፎ፤ አገርን ለመታደግ የሚያስችል ኃይል መፍጠር  ይቻላል።

የእማራ ብልጽግናዎች ሆይ!  የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታን ጠይቃችሁ፤ የያዛችሁትን ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ ለማሰርከብ ተባበሩ።  ይህን ብታደርጉ  እናንተም ሆነ አገር ተጠቃሚ ይሆናል። ስለዚህም፤

1/ እናንተን የሚተካ በመላው የአገሪቱ ከምሁራን (አውነተኛ ምሁር)፣  ከተከበሩ የአገር  ሽማግሊዋችና ለስጋቸው ሳይሆን ለነፍሳቸው ካደሩ  የሃይማኖት አባቶች፤ እንድ  የባለአደራ አስተዳደር ጉባኤ (አስተዳደር)  ይቋቋም።

2/ የዚህ የባለአዳራ ጉባኤ እባላት ከማንኛውም የፓለቲካ ፓርቲና የጎሳ ቡድን የሌሉበት፤ እስከ አሁንም ያልተሳተፋ፣ ወደፊትም የማይሳተፋ መሆን አለባቸው።

3/ ይህ የባለአደራ ጉባኤ የአማራ ብልጽግና ተተኪዎችን በተዋረድ  ከህዝብ በሚያገኘው ድምጽና ጥቆማ በግልጽና በይፋ ይመርጣል። ተተኪ ተመራጮች ከዚህ በፊትም ሆነ ወደፊት በማንኛውም የፓለቲካም ሆነ የጎሳ ቡደን ያልተሰተፍና የማይሳተፋ መሆን አለባቸው።

4/ ለአማራ ብልጽግና ተተኪዎች ከተመረጡ በኋላ፤ ኃላፊነታቸ ከአማራ ብልጽጋና ይረከባሉ። ለአማራ ብልጽግናዎችም በግለሰብ ደረጃ እስከ አልሆነ ድረስ  በባለአደራው ጉባኤ ከህግ – ተጠያቂነት ነጻ መሆናቸን ማረጋገጫ ይሰጣቸዋል።

8/ የአማራን ብልጽግና የተኩት ኃላፊዎች ቀጥታ ተጠሪነታቸው ለባለአደራ ጉባኤ ሲሆን፣  እንደ ከፍተኛው የስልጣን  አስተዳደር ሆኖ ያገለግላል። የአማራን ብልጽግና የተኩና ከፍተኛ ኃላፊነት የተሰጣቸው በወደፊት ከሚደረግ ፓልቲካዊ ስልጣን የታገዱ ይሆናሉ።
7/  የባለአደራው  ጉባኤ  ዘመን በራሱ በአባላቱና ከዓላማው ግብ  ጋር በሚፈጽማቸው ተግባራት  የሚወሰን ሲሆን፤ ህዝብ በባለአዳራው  ጉባኤ አማካኝነት ተደራጅቶ አስተዳደሩን መጠበቅ፣ ህግና ሥረዓትን የማስከበር  ኃላፊነት እንዲወስድ  ያደርጋል።

7/ የባለአደራው ጉባኤ ከማዕከላዊ መንግስት ጋር በኢትዮጵያና በህዝቧ አንድናተ፤ እንዲሁም  የህዝብን መሰረታዊ መብት በማይነካ መንገድ ፤ ግልጽና ለህዝብ ይፋ የሆነ ውይይት በማካሄድ ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ህግ-መንግሥት  በህዝብ እንዲረቀቅና  እንዲጽደቅ ያስደርጋል።
8/  በመጨረሻም በአዲሱ በህዝብ በረቀቀውና በጸደቀው  ህገ መንግሥት አማካኝነት አገራዊ ምርጫ አካሄዶ፣ ለተመራጮች ወይም ለአሸናፊ ፓርቲዎች ኃላፊነቱን ያስረክባል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!

——–//—-ፊልጶስ

Email: [email protected]

 

60 ሚሊዮን ብር ተከፋፍለው የዘረፉ የብልፅግና ጋንግስተሮች ስም ዝርዝር፤ እና የዚህ ፓርቲ አባልና አሽቃባጭ የሆናቹህ ስመ አማራዎች ነፍሳቹህ ልትማር ነው፤

273953788 1589080531468329 3098789146286909793 n

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop