ብልፅግና ሆይ ራስህን ከሰቀልክበት ጉም በጊዜ አውርድ፣ ነገ ሌላ ቀን ነውና!! [መስፍን ማሞ ተሰማ] 

የብልፅግና መንግሥት ሆይ! ናዚስት ህወሃትን እንደ ድርጅትና እንደ ‘ክልላዊ’ መንግሥት ከኢትዮጵያ ካንሰርነት የማስወገድ ፍላጎትህም አላማህም ስላልሆነ ናዚስቱ በከፈተብን ጦርነት ላይ ያለማሰለስ በተደጋጋሚ እንደ መንግሥት የወሰድካቸው ናዚስት ህወሃትን ከሞት የማዳን/የመታደግ ተግባራት ሲያረጋግጡ የአማራና የአፋር ህዝብን በዋናነት የናዚስቶች የዘር ፍጅት መፈፀማያ የጦር አውድማ አድርገኻቸዋል።
የቀድሞው የወያኔ ፍጡር ኢህአዴግ ህወሃትን አውጥቶ ኢህአዴጋዊ መዋቅራዊ ግንባታውንና እሳቤውን – ዘር ተኮር መንግሥትነቱን – በአደረጃጀቱ ጠብቆ ብልፅግና ሆኖ ሲከሰት (ፀረ ወያኔ ኢህአዴግ ሀይላት የለውጥ ተስፋ ብንሰንቅምና ለብልፅግና ፓርቲ  አዎንታዊ ተግባራት ቀና ብንሆንምና ድጋፋችንን ብንሰጥም) በዚህ ደረጃና ጥልቀት ወያኔ ራሱ በከፈተብን ጦርነት በሰጠነው ሀገራዊ የህልውና ምላሽ ናዚስት ህወሃትን ከሞት አፋፍ በተደጋጋሚ የማዳን ስውርና ግልፅ ርብርብ መንግሥት ያደርጋል ብለን ባለመገመታችን ጦርነቱን በሙሉ ሀገራዊ ወኔና ስሜት ከውጪም ከውስጥም በምንችለው ሁሉ ስንደግፍና ስንሳተፍም (በተለይ ከውጪ ሀገር በኢኮኖሚም በመቴሪያልም)  ቆይተናል። የጦር ሀይሉ የበላይ ጠ/ሚር አብይ ወደ ግንባር ሲሄድ ከጎኑ ቆመናል። የአውሮፓውያንንና የአሜሪካን ዓለም ዐቀፍ ሽብር በውጪው ዓለም ሀገራት ከተሞችና አደባባዮች ያለማሰለስ ተሰልፈን ድምፃችንን ስለ ኢትዮጵያ አሰምተናል። NO MORE ብለን በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያ ወዳጆችን አሰልፈን ታግለናል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ወጣቱ የህይወት መሥዋዕትነትን ከፍሏል የአካል ገዳተኝነትንም ወርሷል። የዚህ ሁሉ ትግል ግብ የኢትዮጵያ ካንሰር የሆነውን ህወሃት እንደ ድርጅትና እንደ ጦር ሀይል እንደ ጀርመኑ ናዚ ፓርቲና እንደ ጣሊያኑ ፋሽስት ፓርቲ ከፖለቲካ፣ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ሀይልም  ማንኮታኮትና ወንጀለኛ መሪዎቹንም ለፍርድ ለማቅረብ ነበር። ይህ ግን በኢትዮጵያ ምድር በብልፅግና መንግሥት ህወሃት ላይ ከቶም ዕውን እንደማይሆን የተረዳነው ከዘገየ ነው። የብልፅግና መንግሥት ናዚስት ወያኔ በአማራውና በአፋሩ ህዝባችን ላይ የሚያካሂደውን የዘር ፍጅት፣ የማፈናቀል፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ ወይ ከዳር ቆሞ ይመለከታል፣ ወይ እንደ ገላጋይ መኻል ገብቶ “በየቦታችሁ” ቁሙ ይላል። ይህ አዙሪታዊ የብልፅግና ዥዋዥዌ ትላንት ነበር ነገም ተመልሶ ይከሰታል።
በግልፅና በተደጋጋሚ እንዳየነው ብልፅግና ናዚስት ህወሃትን (ወያኔን) እንደ ድርጅትና እንደ ፖለቲካዊ ተቋም ከነኢኮኖሚያዊ ጡንቻው (ለምሳሌ ኤፈርት) ጭምር ከኢትዮጵያ የፖለቲካና መንግሥታዊ ማዕቀፍ የማስወገድ ፍላጎት ከቶም የለውም። በተግባርም በመታየት ላይ ነው።
ከናዚስት ወያኔ ጋር እንደ ሀገር በተለይ ደግሞ በአማራና በአፋር ክልሎች የገባንበትን የህልውና ጦርነት ቢያንስ በአማራውና በአፋሩ ላይ እየደረሰ ያለውን ማባሪያ ያጣ የዘር ፍጅትና ምድራዊ ሠቆቃ የንብረት ውድመትና የአርሶ አደሩና የከተሜው መፈናቀል (በወለጋ ምድር በንፁሀን ኢትዮጵያውያን ላይ በማንነት በኦነግ የሚፈፀመውን ፋሽስታዊ ፍጅትንም ልብ ይሏል) ማቆም የምንችለው እንዴት ነው?!
የብልፅግና መንግሥት ሆይ፤ አንተ ብቻ ስለ ኢትዮጵያ ትንሳዔ የምታውቀው ወይም የተገለጠልህና ለእኛ ግን የተሰወረብን ምሥጢር ምንድን ነው?! ስለምን ስለ ሀገራችን ኢትዮጵያ የዛሬና የነገውን ህልውናዋን ሠላሟንና ዕድገቷን አስመልክቶ እንደ ዜጋ የያገባናል መብታችንን እና በጎ ተስፋችንን እንድናሟጥጥና በተስፋ መቁረጥ ፊታችንን እና የዜግነት ግዴታችንን ለአንተ ጥለን እንድንገለል ግልፅና ረቂቅ ደባ ታካሂዳለህ?! ብልፅግና ሆይ፤ ነገ ሌላ ቀን ነው። ህዝብን ስማ ህዝብ አንተን ብቻ እንዲሰማ ይቻለው ዘንድ እንደማይቻለው ራስህ የመጣህበት የሥልጣን መሰላል እንደምን ትምህርት ሊሆንህ አልቻለም?! ብልፅግና ሆይ ፀሀይና ንፋስ መኖራቸውን አትርሳና ራስህን ከሰቀልክበት ጉም በጊዜ አውርድ !!!! ነገ ሌላ ቀን ነውና . . . !!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !!!
ተጨማሪ ያንብቡ:  የሁለት ሀገር ስደተኛው - ጋዜጠኛ። (ሥርጉተ ሥላሴ)

3 Comments

  1. If A is B and B is C, then A is C. ይላል ሎጅኩ። እስከ መቼ እንሸፋፍናለን። አብይ ኦነግ እንደሆነ እራሱ ነግሮናል። ኦነግ ደሞ ሸኔ ነው። ስለዚህ አብይ ሸኔ ነው ማለት ነው። የአብይ መንግስት ሸኔ ነው። የሚመራው ሠራዊትም የሸኔ ነው። አለቀ።
    አማራ የሚፈለገው ስልጣን እስኪይዝ ነበረ። በአማራ እርዳታ ስልጣን ያዘ። ከስልጣን በሗላ ግን ኦነግ አብይ ስልጣኑን ይዞ እንደፈለገ እንዳያረግ አማራ ትልቁ መሠናክል ነው። አሁን ለአብይ ትልቁ ጠላት አማራ ነው ማለት ነው። ስለ አዲስ አበባ የማይስማማ አማራ ነው። የሚወዱትን ህገ መንግስት የሚጠላ አማራ ነው። ስለ ወለጋ የሚያለቅስ አማራ ነው። ኦርቶዶክስ ተገፋች ብሎ እሪ የሚል አማራ ነው። አብይ ሀገሪትን ሲያፈርስ ሊገዳደር የሚችል አማራ ነው ።ለዚህ ለኦነግ አብይ መሠናክል ለሆነ አማራን ደግሞ ለማዳከም አለምን ቢዞር እንደ ህወሀት ያለ ረዳት አያገኝም። ስለዚህ አሁን ባለው ሁኔታ ለአብይ አማራ ትልቁ ጠላት ነው። ህወሀት ደግሞ ትልቁ ወዳጅ ነው። ለአብይ የአፋሮች ሞት አያገባውም። ለአብይ የአማራ ሞት የሚፈልገው ነው። አማራ ግን አሁንም የአብይ ብልፅግና ያድነኛል ብሎ ያስባል። ትግሬወች አማራ አህያ ነው ይላሉ። እንደማየው እውነት ሳይሆን አይቀርም።

  2. አማራ አህያ ሆኖም አያውቅም እባቡ ትግሬ አንተ ነህ::ዐቢይ የኢትዮጵያ ህዝብ ለ5 አመታት መርጦታል እንደ እንቁራሪት አብጠህ ልትፈነዳ ትችላለህ:: ሸኔ ህውሀት ነው:: ይህን ለማስረዳት ጊዜዬን አላባክንም

  3. አዎን ናዚስቶቹ ህውሃት እደሚሉት እንደ ደመቀ እይነቱ እጋስስ እህያን እይትመለከቱ አማራ እህያ ነው ቢሉ እይደንቅም!ለምን ትልቅ የባረንት ሆዱን እየሞላ ያለ እንደ ደመቀ እንደ አገኘሁ ያሉ ብዝ እህዮች እሉና!እነርሱም የግዜ ጉዳይ እንጅ የሚበራዩበት መጥፎ ታሪክ ለልጅ ልጆቻቸው ለዘመው እዝማድ ለአማራም ማፈርያ ሆነው ይሚነሱበት ወቅት እየመጣ ነው!
    እንድያው ደመቀ መኮንን እፍረት የሚስማው ስው ነው?አጋስስ እንጅ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share