ከአንድ ክ/ዘመን በፊት የተተከለዉን ከፋፋይ የአገር ክህደት ሴራ ዛሬ አንደ አዲስ ደራሽ ዉኃ ማድረግ እና ሰሞነኛ አድርጎ ማጮህ ለዓመታት እንደሰደድ ዕሳት እየተስፋፋ ያለዉን ድህነት፣ ስደት(የአገር ዉስጥ መፈናቀል) ፣ ሞት እና ርዛት የሚያስታግስ ሳይሆን የሚያለባብስ ነዉ ፡፡
ከሰሞኑ የትግራይ አገረ ስብከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የመነጠል አዝማሚያ እንዳለ ማራገብ የአዋጁን በጆሮ ለሚሉ ጆሮ መስጠት ከመዘናጋት በላይ ሞት ነዉ ፡፡
ከላይ ለተባለዉ ምክነያት በጦርነት በትግራይ ለነበረዉ ጦርነት እና ላስከተለዉ ዉድመት ቤተ ክርስቲያን ድምፅ አላሰማች ማለት ምንድን ነዉ ፡፡
ለመሆኑ ህወኃት ኢህዴግ ከአስራ ዘተኝ መቶ ሰማንያ ሶስት ዓ.ም. ጀምሮ በዕምነት ተቋማት በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ ሳይቀር መፈንቅለ ፓትራያሪክ በማድረግ የራሱን ልማታዊ ሠዉ ሲያስቀምጥ ቤ/ ክ ድምጧን አሰምታለች የሚል ማን ነዉ ፡፡
ለመሆኑ አንድ የቤተክርስቲያን አባት በህይወት እያሉ ሌላ የሾመ(ያስቀመጠ) የህወኃት / ትግሬ ስርዓት አልነበረም ወይ፡፡
ከዚያ ጊዜ አስከዚህ ሰዓት ድረስ በመላ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊነት እና ማንነት ላይ በሆነ ጀምላ ማሳደድ ፣ ማፈናቀል ፣ መግደል ፤ማስገደል…..ድፍን ፴ ዓመታት ለሚከናወነዉ ቤ/ ክርስቲያን ምን የሚቆጠር አቋም ወሰደች ፡፡
በዕምነት ተቋማት ግቢ ሳይቀር ለተደረገ የጣልቃ ገብነት ወንጀል ቤ/ ክ ለአገር እና ህዝብ ከመወገን ይልቅ ለዓለማዊ አገዛዝ እንድትወግን ከላይ አስከ ታች በብቃት ሳይሆን በብሄር አምልኮት እና አገልጋይነት ተደራጂቶ እንደነበር እና ይህም እንደ ሌሎች ህዝባዊ እና መንግስታዊ መዋቅር በብሄር ስም የተጠላለፈ አሰራር ነበር ፤ ነዉ፡፡
አበዉ “ ዉኃን ምን ያጮኸዋል ሲሉ ድንጋይ ” እንዲሉ የኢትዮጵያ እና የህዝቧ የዘመናት ጥቃት ፣ ዉድመት እና ሞት ምንም ዓይነት ቁብ ያልሰጣቸዉ ዛሬ ከ1968 .ዓ.ም. ቀድሞ ለማጥፋት የጥላቻ መንደርደሪያዉ የዓማራ ህዝብ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ እና ኢትዮጵያዊነት ለማዋረድ እና ለማስወገድ ያልተፈነቀለ ድንጊያ እና ያልተቆረጠ ቅጠል አልነበረም ፡፡
ይህ ሲሆን አንድም ቀን የዓማራ ሞት እና ስደት ፣ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር መደፈር ፣ የኢትዮጵያ አንድነት አደጋ ላይ መዉደቅ ያላሳሰባቸዉ ዛሬ በኃይማኖት ተቋማት ያላቸዉን የብሄር (ቋንቋ) አደረጃጀት እንደ ት.ህ.ነ.ግ. አገር እና ህዘብ በማንነቱ ፤በርስቱ እንዲወረር ፤ እንዲመዘበር እና እንዲሸበር ቤተ ክርስቲያን በግላጭ ድጋፍ አላደረገችም የሚሉ ከሆነ በግልፅ ሊያወጡት ይገባል፡፡
ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ሠዉ ልጆች መጠጊያ እና መሸሸጊያ እናት ናት ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ዕጉም ስንል ገፍታናለች ፤ ድምፅ ነፍጋናለች፤ ሰንራብ አልደረሰችልንም ፤ ስንሞት እና ስንሳደድ ልጆቸን አትንኩ አላለችም ብሎ ቢወቅሱም የሚያምራባቸዉ ሌሎች ከትግሬ ዉጭ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ነበሩ ፡፡
ስለ ኢትዮጵያ ፣ ስለ ዕምነት ተቋማት ፣ ስለ ህዝብ እና ስለ ራሱ ክብር የሚያስብ ህዝብ ለደረሰበት መከራ እና ችግር ተጠያቂዉ መንግስት እና የዕምነት ተቋማት ሆነዉ እያለ የህይወት እና የምስቅልቅል ዋጋ የሚከፍለዉ ህዝብ በተለይም የቤተ ክርስቲያን ልጆች ናቸዉ ፡፡
እናም ይኸ ጩኸቴን ቀሙኝ መንጫጫት ቀርቶ የሚበጀዉ ለህይወት ወይም ሞት በፅኑ ዕምነት እና ዓላማ መዘጋጀት ያስፈልጋል፡፡
ሲጠቃለል አገር ለማፍረስ ከ1968 .ዓ.ም. ጀምሮ ኢትዮጵያን በማፍረስ ታላቋን ትግራዊ ለመቀለስ ያኔ የተተከለዉን ጋሬጣ ከ“መንቀል እና ማቃጠል ” ዉጭ ዛሬ ስለ ትናንቱ ማዉራት የሚተርፈዉ በስንፈት “ሞት እና ዉርደት ” ማስተናገድ ይሆናል ፡፡
ማላጂ
አንድነት ኃይል ነዉ