January 20, 2022
5 mins read

ትንሽም ብትሆን እውነትን ሳትቀላቅል ዋሽ ….. የሚያዉቁህ ባያምኑህም…… ነገር ግን ዋሽ ….

126144

ያንተ በስፋት የተሰራጨ ውሸት እነርሱ በጃቸው ከያዙት እውነት በላይ ተሰሚነት ያገኛል

(እውነቱ ቢሆን)

ወያኔወች፦ አምናም ውሸት፣ ትናንትም ውሸት ፣ዛሬም ውሸት፣ ዘለአለም ውሸት፣ ውሸት  ውሸት .. አሁንም ነገም ውሸት  ብቻ ናቸው፡፡ ይህንኑ ማንነታችውን  በትክክል ለመግለጽ ይረዳ  ዘንድ በመረጃ ፎረም ላይ ከአንድ ጸሀፊ ያገኘሁትን ወያኔ ማለት ሙሉውን ውሸት መሆኑን አሳምሮ የሚገልጽ አጭር ጽሁፍ ጽሁፉን እንደወረደ ከስር አቅርቤዋለሁ፡፡

የዲጅታል ወያኔ ማኒፈስቶ፦

ዋሽ፡፡ ነገር ግን በምትዋሽበት ጊዜ ትንሽም ብትሆን እውነትን አትቀላቅል፡፡ በቃ እስከመጨረሻው ድረስ ዋሽ!  የእውነታው ድራሹ እስከማይታወቅ ድረስ በውሸትህ ጽና፡፡ ሁሉም ራሱን መጠራጠር እስከሚጀምር ድረስ ውሸትን አቀናብራት፣ ሽፋን እንድታገኝ አድርጋት፣ ሀሰተኛ ዘገባ ዘግብ፡፡ ማንም ባያምንህም በውሸትህ ጽና፦ በሷ ላይ ተመስርተህ ቀጣይ እርምጃህን ፈጽም፡፤እራስህ የፈጠርከውን ሀሰት እራስህ አሰራጨው፡፤ ከዚያም ለእርሱ የሚመጥን እርምጃ ውሰድ፡፤ ያኔ ሁሉም ሰው በግራ መጋባት ውስጥ ሁኖ ጆሮ ይሰጥሀል፡፡በተቻለ መጠን የሀሰት ማስረጃወችን አሰራጭ፡፡ ያሰራጨሀውን ሀሰተኛ መረጃ  የሚያጠናክሩ የሀሰት ምስክሮችን ከየአቅጣጫው አዘጋጅተህ አቅርብ፡፡

የሚያዉቁህ በሙሉ አያምኑህም፡፡ አይሰሙህም፡፡ እነርሱን እርሳቸው፡፡ አይናቸው እያየ ጆሯቸው እየሰማ በአደባባይ ሀሰተኛ መረጃን ልቀቅ፡፡ እነርሱ እውነቱን ስለሚያውቁ እነርሱን ለማሳመን አትጃጃል፡፡ ይልቅ በተደራሽነትህ ተጠቅመህ ቅደማቸውና ያንተ ሀሰት የእነርሱን እውነታ እንድሸፍን አድርግ፡፡ያኔ በዙሪያህ ያለው ህዝብ እውነቱን ስለሚያውቅ አንተን እና የሀሰት ፕሮፓጋንዳህን አምርሮ ከመጥላት ውጭ ምንም አያመጣም፡፡ ነገር ግን ያንተ መረጃ በመላው አለም ተቀባይ ይሆናል፡፡ ተቃዋሚወችህ እውነቱን በጃቸው ይዘው ቁመው ይቀራሉ፡፤ የማያውቅህ የሩቅ ሰው ግን አማራጭ አጥቶ ከአንተ ጎን የመሆን እድል ይኖረዋል፡፡

ተቃዋሚወችህ አንተ ደረሰብኝ ያልከውን ሁሉ ባይፈጽሙትም አንተ ራስህ እነርሱን መስለህ ድርጊቱን ተውነው፡፡ ንጹሀን ተገደሉብኝ ካልክ በቃ ንጹሀን እንዲገደሉ አድርግ ወይም ማንነትህን ሰውረህ ንጹሀንን ግደል፡፡ ይህ የትግሉ መንገድ ነው፡፤ ድሉን ለማግኘት ማንኛውንም ነገር መፈጸም ግድ ይልሀል፡፤ ንጹሀን በግፍና በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉብኝ ብለህ ካሰራጨህ እና ተቃዋሚወችህ ያንን ካልፈጸሙት ይህ ነገር እንድፈጸም የራስህን ድርሻ ተወጣ፡፡ ንጹሀን በሚገኙበት ቦታ ዉጊያ ክፈት፡፡ ንጹሀን አልወጣ ካሉህ ዉጡና ተዋጉ በላቸው፡፡ እምቢ ካሉህ ማንነትህን ሰውረህ የጠላትን ገጽታ ተላብሰህ ጥቃት አድርስባቸው፡፡ ከዛ ሜድያ ላይ ውጣና ድርጊቱን በእጅጉ አውግዝ፡፡ ማውገዝ ብቻም ሳይሆን አጸፋ እወስዳለሁ ብለህ ተናገር፡፡ ዋሽ፡፡ እየዋሸህ ጽና፡፡ የዋሸሀውን ውሸት ሌላው ባያምነው አንተው እመነው እና በዛ ተመስርተህ አጸፋ መልስ ስጥ፡፡ ነገሩ ከቅም በላይ ሲሆንበት ሁሉም ይምታታበትና ያንተ ውሸት ከእነርሱ እውነት በላይ ተሰሚነት ያገኛል፡፡

ይህችን ከመረጃ ፎረም ላይ ያገነኋትን አጭር ነገር ግን የወያኔን ማንነት ቁልጭ አድርጋ የምትገልጽ አጭር ጽሁፍ ልኬያለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop