ወያኔ ዳግም እንዲወረንና እንዲገለን ቀርቶ እንዲኖርስ  እንፈቅድለታለን ????

የማንኛውም መንግሥት”ሀሁ’—– የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ነው። የዜጎቹን ደህንነት መጠበቅ ያልቻል አገዛዝ ስልጣኑ “የዛፍ ላይ እንቅልፍ ” ብቻ ሳይሆን፤ ለዘመናት በደምና በአጥንት የተገነባን የአገርና የህዝብን አንድንተን ያፈርሳል፤ ኑሮና ህይወትን ያመሰቃቅላል።

በአንጻሩ መሰረታዊ መብቱን ከአባራኩ የወጡ ገዥዎቹን ታግሎ ማስከበር የማይችል ዜጋ፤ ህልውናውም አደጋ ላይ መውደቁ የማይቀር ነው።
የአገር ልዋአላዊንትና የህዝብ ህልውና ፈተና ላይ ሲወድቅ፣ ዜጎች በየቀኑ እደከብት ሲታረዱና የመኖር ዋስትና ሲጠፋ፤ አስተዳድራለሁና እመራለሁ የሚለውን መንግስት ነኝ ባይ፤ እንዴትና ለምን? ብሎ የማይጠይቅና የማይሞግት፤ ብሎም ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ የማይረዳና ለራሱ ህልውና የማይታገልና የማይቆም ህዝብ መጨረሻው፤
ሌዎ ቶልስቶይ እንዳለው ”—ወላጆች ልጆቻቸውን ይቀብራሉ፤ ወላጆች ደግሞ ያለ ጧሪ ይቀራሉ፤ አገርም ባለቤት አልባ ትሆናለች።—”
በኢትዮጵያ ምድር እየሆነ ያለውም እውነታ ይኽው ነው። ታዲያ አሁን ያለው የህልውና ጥያቄ የመጣው በአንድ ጀምበር ሳይሆን፤ በሂደት መሆኑን ወደ ኋላ መለስ ብለን፤ ከትላንቱ የመማራ ክህሎት ብናገኝ እንደሚከተለው ለማስታወስ እንሞክ።

1/ ወያኔ ወደ መቀሌ ሲኮበልልና የጠ/ሚኒስተር አብይ አህመድ ስልጣኑን በያዙ ማግስት፤ የታለመው ሥር-ነቀል ለውጥና መሰረታዊ የሰውልጅ መብት ”በተረኝነት” ሲተካ፤ ህዝብ ተደራጅቶ መብቱን ማስከበር ባለመቻሉና የህዝብንም ጥያቄ ያነሱ ወደ እስር ቤት ሲወረውሩ ”እንዴትና ለምን?” በማለት ባለመጠየቃችንና ባለመታገላችን ፤ የኦነጋዊ ብልጽግና በማን አልብኝነት እንዲፈነጭ ተፈቀደለት።
ይህ ብቻ አይደልም ፤ የኦሮሚያ ብልጽግና ለኦነግ ”ኦነግ ሸኔ” የሚል የዳቦ ስም አው’ቶ፤ እስከ ዚች ሰዓት ድረስ ባንኮችን ሲያዘርፍ፣ ከተማን ሲያወድም፣ በመተከልና በወለጋ የሰው ልጅ በማንነቱ ሲያሳርድ፣ ልጅ አገርድ ተማሪዎች ታፍነው የደረሱበት ሳይታወቅ ሲቀር፣ ተጨባጭ የሆነ ትግል አላካሄድንም።
እነ አቶ ጃዋር ሙሃመድ የአሜሪካን ፓስፖርት ይዘው ” ሁለት መንግሥት አለ” እያሉ ህዝብን ሲያርዱና ሲያሳርዱ፤ ገዥው ኋይል በስልጣኑ እስኪመጡበት ድረስ አይነኬ መሆናቸው፤ በአጠቃላይ የሚፈጸመው ግፍ ”ጽዋው ሞልቶ ሲፈስ”፤ እንደ ህዝብ ገዥዎቻችንን ለማስቆምም ሆነ ተጠያቄዎቹን ለመጠየቅ ባለመቻላችን አሁን ላለንበት መከራ በቅተናል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የዶ/ር ዓቢይ አህመድ ተግዳሮቶችና የመፍትሔ እርምጃዎች | በገብረ ክርስቶስ ዓባይ

2/ በጠቅላይ ሚኒስተሩ አንደበት፤
– ”ዱቄት አድርግናቸዋል!”፤
– ድሞ ሌላ ግዜ “መለማመጃችን ናቸው!”፤
– ” በሳተላይት እየተከታተልናች ነው፤ ግን ልናጠፋቸው ያልፈለግነው ምርኮኞችንና ጻናትን ስለያዙ ነው።”—-የተባለው የሰባዊ- ፍጡር ሁሉ ጠላትና አጥፊ የሆነው ወያኔ፤ ”የፓለቲካ ውሳኔ” በሚል ሸምጋይ ቃል መከላከያ ከትግራይ የወጣው፤ ”የትግራይ ህዝብ እርሶ እንዲበላና የጥሞና ግዜ ለመስጠት ነው።” ተብሎ ሲነገራን፤
– ለምን? እንዴት ? ብለን እልጠየቅንም።
– መከላከያ ከኋላው የህዝብ ደጀን እለው፤ ታዲያ በትግራይ ድንበር መሽጎ እንዲት ሊከላከል አልቻለም? ብለን እልሞገትንም።
– መከላከያ ከትግራይ ነቅሎ ሲወጣ ለወያኔ ትልልቅ መሳሪያዎችን እና በክልሉ ውስጥ ለጦርነት ፍጆታ የሚውሉትን ሁሉ እንዱንም ሳይነካ፣ እንዴት ለጠላት ጥላችሁ ተወጣልችሁ? ብሎ መንግስት ነኝ የሚለውን አካል የጠየቀና እውነቱን ለማወቅ የሞከረ የለም።

ይልቁንም መንግስት ያድነናል! ይከላከልልናል! ዝም ጭጭ በሉ! እየተባለ፤ ወያኔ ከከተማ ከተማ እያከታተለ እየተቆጣጠና እየዘረፈ፤ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ተሰምቶ የማያውቀን ግፍና ሰቆቃ አየፈጸመ ሲቀጥል፤ ራስን አደራጅቶና በጎበዝ አለቃ እየተመሩ ፣ ጎን ለጎን የኦነጋዊ-ብልጽግና ካድሪዎችንና የጭቃ ሹሞችን እይስወገዱ፤ እንደመክላከል፤ ከተቻለም እንደማጥቃት፤ ገዥው ” ስትራተጅካዊ ማፈግፈግ ነው።” የሚለውን የምስለኔዋችን ቅስቀሳ እያመን፤ በተግባር እየሆነ ላለው”የዝሆን ጀሮ ይስጠን” ብለን፤ ንጹሁ እርሶ አደር ወገናችን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያለትሰማውንና ያልታየውን መከራ ተቀብሎ አስተናገደ፤ ሂሳብ ተወረረደብት።

3/ አሁንስ?????????
ጠ/ሚኒስተሩ ወያኔ የቤተ መንግሥታቸውን በር ማንኳኳት ሲጀምር ፤ ህዝባዊ ጥሪ አቅርበው ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ ለህልውናው እየተጋደለ ባለበት ወቅት፣ ስሜን ወሎ ራያና ሰሜን ጎንደር ያሉ የድንበር ወረዳዎችና ቀብሌዎች ገና እንደ ተወረሩ፤ ግራ የሚያጋባ ብቻ ስይሆኑ፤
”በ’ርግጥም መንግሥት ወያኔን ማጥፋት አይፈልግም! አሁንም በወሎ፣ በሰሜን ሸዋና በአፋር የደረሰው ጥፋት በቂ ስላልሆነ ፤ ወያኔ እንደግና ተጠናክሮ የቀረውን ሂሳብ ያወረርድ፣ የወልቃይትንም ”ኮሪደር” ያስከፍት።” የሚያስብሉ ፤ ርስ-በርሳቸው የሚጣረዙ መግለጫዎች የመንግሥት ባለስጣናት መሰጠት ጀመሩ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የቢሸፍቱው አልቂት፤ - ይገረም አለሙ

ለትዝብት ብሎም የምንሰማውን ሳይሆን የምናየውን እንድናምን እና ምን ዓይነት ገዥዎች እንዳሉን ከትላንቱ ብንማር እስቲ መግልጫዎቹን እንመልከት፤

unnamed 12ከዚህ ላይ የመከላከያ ጠቅላይ ጦር አዛዥ ብርሃኑ ጁላ በታህሳስ 12/2014 ባደርጉት የአንድ የመድረክ ንግግር ላይ፤ ” —-ብረት እንደጋለ ነው መደብደብ ያለበት፤ ወያኔንም እስከመጨረሻው እናሳድደዋለን ።—-” ነበር ያሉት፤ ነበር ባይሰበር።

ወያኔ ግዜ እንዲያገኝና ዳግም እንዲወር የሚያበረታታው ግን ከጦር ግንባር የተመለሱት የጠ/ ሚኒስተር የአብይ አህመድ መግለጫ ነው። መግለጫው፤ ጦርነቱ በድል መጠናቀቁን እና በወያኔ ተይዘው የነበሩ ሁሉ በመከላከያ ቁጥጥር ስር መሆናቸውን አብሰረው ፤ በትግሉ ለተሳተፋ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።

አሁን ያለው የጦርነቱ እውነታ፤

በመሃል አገር ከውጭ አገር በገቡ ተጋባዥ ኢትዮጵያዊን ጋር ”አስረሽ ምችው !” ቀጥሏል። አዲስ አበባ እስከ አልተነካችና በኦነጋዊ ብልጽግና ስር እስከሆነች ድረስ፤ የሰሜኑ ጦርነት የህዝብ ስቃይ ለፓለቲካ ፍጆታ የሚውል ሆኗል። ለትዝብት እንኳን በማሃል አገር በስብሰባና በየምክንያቱ ለድግስ የሚወጣው ወጭ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ተፈናቃዮች መዋል በተገባው ነበር።

ወያኔ ከመንግሥት በተሰጠው ፋታ ራሱን እንደገና እያደራጀና እያሰባሰብ ብቻ ሳይሆን፤ በተለይም በወልቃይት፣ በማይጠምሬ፣ በራያ- ሰቆጣና በተለያዮ ግንባሮች ጦርነት ከፍቷል። ዳግም ወረራ ለማካሄድ ብሎም ወልቃይትን ለመቆጣጠርና ከሱዳን ጋር ለመገኛኘት የሚያስችለውን ዝግጅት እያደረግ መሆኑን የሚነገሩን ራሳቸው የምንግስት ብዙሃን መገናኛዋች ናቸው። ታዲያ በዚች ወሳኝ ሰዓት ገዥዋቻችን ምን እያደረጋችሁ ነው? ብሎ መጠየቅ ያለበት ህዝብና በተለይም የወያኔ የሂሳብ ማወራረጃ የሚሆነው ወገን ነው።

ወያኔ ከአሁን በኃላ ድጋሜ ቢወር ምን ሊሰራ እንደሚችል ማሰብ ራሱ ይዘገንናል። ነገር ግን አሁንም የመንግሥትን አቋም ማስለውጥ ከተቻለ ግዜ አለ፤ ግዜው ግን ነገ ሳይሆን አሁን ነው። መንግሥት ሃስቡን ለወጠም እለወጠም ፤ ህዝብ ራሱን አደራጅቶና በጎበዝ አለቃ በመደርቃጀት መታገል የግድ ይለዋል። መንግሥትም እንደ ትላንቱ”ስልታዊ ማፈግፈግ” ቢል ፍጹም ተቀባይነት የሌለውና በኢትዮጵያ ህዝብ ደም እየተጫወት መሆኑ ተገንዝቦ፤ ከጎኑ ያለውን ህዝብ ይዞ፤ ወያኔን ብቻ ሳይሆን አመለካከቱንም እስከመጨረቻው ድረስ ማጥፋት፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ የመኖርና ያለምኖር ጥያቄ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦሮሙማ ማኔፌስቶ! አዲስ አበባ ኬኛ! የኢኮኖሚ ዘርፍ የመሬት ቅርምት!የዘገነም ያልዘገነም እኩል አዘነ! (ክፍል ሦስት) - ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም

”ስትሄድ የመታህ እንቅፋት ስትመለስ ከመታህ ችግሩ ከአንተ ነው።” እንደሚባለው፤ ህዝብም ያለፈውን ስህተት በፍጹም መድግም የለበትም። የደረሰው ጥፋትና እልቂት ከበቂና ከእዕምሮ በላይ ነውና ። ስለዚህ ሁላችንም መዳኛ የሆነችውን

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!

——-//——–ፊልጶስ

ታህሳስ/2014

E-mail: philiposmw@gmail.com

1 Comment

  1. ወሬና ለፓለቲካ ፍጆታ የሚነፋ ጡሩንባ ቃና የሌላቸው ምድር የማይረግጡ እይታዎች ናቸው። ወያኔን ማንም ማጥፋት አይችልም። ክፋታቸው እንዳለ ሆኖ ህብረታቸውና የክፋት ትስስራቸውን አለማድነቅ አይቻልም። ወያኔ ማለት የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ማለት ሳይሆን ሳጥናኤል ማለት ነው። ከዚያም የከፋ ደረጃ ካለ ስም ፈልጉላቸው። የሚገባቸው ያ ነው። የሚያታልሉት የትግራይን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለምን ጭምር ነው። ራሳቸው ገድለው ሞተብን፤ ራሳቸው አፍርሰው ፈረሰብን፤ ሌላውን እያስረቡ ተራብን የሚሉ ተኩላዎች ናቸው። እርግጥ ነው መብረቃዊ ጥቃት የተባለው እብደት በትግራይ መሬት ከተጫረ ወዲህ ግፍ በሁለቱም ጎራ አልተሰራም ብሎ ማመን ጅልነት ነው። እዚህም እንባ እዚያም ለቅሶ። ጉዳቱ የጋራ ነው። ግን ወያኔ በጎንደር፤ በአፋርና በወሎ እንዲሁም በሽዋ የፈጸመው ትውልድ ሊረሳው የማይችል ዘግናኝ ድርጊት ነው። ድሮስ ቢሆን ጫት እየቃመ፤ የዘረፈውን ቢራ እየተጋተ፤ ሃሺሽ እያጨሰ ወንድሙንና እህቱን ገድሎ አለቃ ነኝ ከሚል ድርብሹ እንዴት ስብዕና ይጠበቃል? የተጃጃለው የወሎ፤ የጎንደር፤ የሽዋና የአፋር ህዝብ ነው። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ወያኔ ሰራዊት ሲያሰለጥኑ፤ ከአማራ ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለን ሲሉ ሰው ፈዞና ደንግዞ ጠበቃቸው። የዛሬን አያርገውና ጀዋር እንዲህ ብሎ ነበር ” ታዲያ በትግራይ ያን ያህል ሰራዊት የሚያሰለጥነው ግብጽን ሊወጋበት ነው? ለወረራ እንደሚዘጋጅ ግልጽ ነው” ብሎን ነበር። ዛሬ እሱና መሰሎቹ ሌሎችም ጋዜጠኞች በአዲሱ መንግስት ዘብጥያ ከወረድ ቆዬ። የሃበሻው ፓለቲካ የመበላላት ፓለቲካ ነው የምንለው ለዚህ ነው። ትራፊውን የሌላ ትራፊ ሲበላው ይኽው ዘመን ቆጥረናል። በዚህ ላይ የአሜሪካ የአውሮፓና የአረቦችን እብደት ሲደመርበት ኢትዮጵያን እንደ ሶሪያ ለማድረግ ቆርጠው እንደተነሱ ልብ ያለው ሊገባው ይገባል። አሁን በቅርቡ አዲስ አበባ ላይ የተጎለተው የአሜሪካው ኤምባሲ ባወጣው መግለጫ ሰዎች ኢትዪጵያን ለቀው እንዲወጡ ብር እስከ ማበደር ድረስ ፈቃደኛ መሆኑን አንበናል። ይታያቹሁ በምን አይነት ሂሳብ ነው ለወረራ ራሳቸው ካልተዘጋጅ በስተቀር ሰው ኢትዮጵያን ለቆ እንዲወጣ አሁን ላይ ደግመው የሚያስፈራሩት? የሆነ የሴራ ሽርብ እንዳለ የፊልትማን የገና ጉዞ አስረግጦ ያሳያል።
    በዚህ ላይ የቻይናው የኤርትራ ጉብኝት፤ ወደ ኬኒያ የመጓዝ ብልሃትና አልፎ ተርፎም ለምስራቅ አፍሪቃ ቻይናዊ ባለስልጣን ለመመደብ መዘጋጀታቸው ልክ በቀደሙት ዘመናት በራሽያና በአሜሪካ እሳት አቀባይነት ስንገዳደል እንደኖርነው ሁሉ አሁንም የሚሆነው ይኸው ነው። ከ 30 ዓመት በላይ ብቅ ያላሉባትን ኤርትራ ቻይናዎች ለምን ዛሬ ፈለጓት? የጥቁር ህዝብ ገመና ከራሱና ከውጭ ሃይሎች በጥምረት የሚመነጭ ነው። እንደ ድር አራዊት በዘሩና በቋንቋው ወይም በሃይማኖቱ ተሰልፎ የራሱን ወገን ገድሎ የሚፎክረው ጅላጅል ጀግና የሚባልበት ምንም አይነት ሂሳብ የለም። ቻይናም ሆነ ነጩና የአረቡ መንጋ ሂሳባቸው አንድ ነው። የራስን ጥቅም ማስቀደም።
    በመሰረቱ የኢትዮጵያ ጦር ትግራይ አለመግባቱ አዋቂነት ይመስለኛል። ወያኔን ማውረድ የሚችለው የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው። ከውጭ የሚገባ ማንም አይነት ሃይል ነገሮችን ያባብሳል እንጂ መፍትሄ አያመጣም። አውቃለሁ እንዴ የትግራይ ህዝብ በወያኔ የታፈነ ነው እንዴት ይችላል ትሉ ይሆናል ከቆረጠ ይችላል። ግን የሚሆነ ነገር አይደለም። ለዚህ ነው ወያኔና የትግራይ ህዝብ አንድ ናቸው የምንለው። ያ ባይሆን 50 አመታት መከራ ባልዘነበበት ነበር። አሁን እንሆ ጠ/ሚሩ ለገና በለቀቁት ጽሁፍ ላይ ስለ ሰላም ያወራሉ። ስለ የትኛው ሰላም እንደሆነ ግን ግልጽ አይደለም። ከወያኔ ጋር እርቅ እንፈጥራለን ከሆነ የማይሆን ነገር ለሚስትህ አትንገር ነው። ወያኔ ሰላም አይፈልግም። ደ/ጽዪን የጋዜጠኛ ሙያዋ በወያኔ የተጠለፈባትና የጠለሸባት Nima Ebagir ጋር በ CNN ያደረገው ቃለ ምልልስና የጦር አዛዡ በትግራይ ቲቪ ቀርቦ የሰጠው ሃሳቦች ሰማይና ምድር ነው። ሲጀመር አፋርና አማራን ለቀን የወጣነው አሜሪካ ውጡ ብሎን ነው ሲሉ አለማፈራቸው። ስንት የትግራይ ልጆች ነው የረገፉት፤ በዚህስ የእብዶች ፍልሚያ ምን ያህል ንብረትና ሃብት ነው የወደመውና ወደ ትግራይ የተጫነው? ደግሞስ የሩቅ አዋጊው ወረደ በግድ ከበባውን እንሰብራለን ሲል በምን ሂሳብ ነው? ማን ነው የተከበበው? ለዚህ ነው የኢትዮጵያ ፓለቲከኞች ወላዋዪችና በሰው ደም ነጋጆች ናቸው የምንለው። አሁን ማን ይሙት ከዚህ ሁሉ እልቂት በህዋላ ሰው ሌላ ግጭት ይፈልጋል? ግን ያው ተላካኪዎቻቸው በሳተላይት ስልክ የሚነግሯቸው አለን በሉ ነው። ፊልትማን መቀሌ ሄደ አዲስ አበባ የሚያስበውና የሚተነፍሰው ለትግራይ ህዝብ ወይም ለኢትዮጵያ ሰላም አይደለም። አቤት ወዴት የሚለው ተላላኪ መንግስት መመስረትና መመዝበር እንጂ። 27 ዓመት ሙሉ ለትግራይ ህዝብ ስንቅ ሲያቀብሉ ቆም ብለው ለምንድነው ይህን ህዝብ ሁልጊዜ በእርዳታ እህል እንዲኖር የምናረገው? ከዚህ የሚወጣበትን መንገድ እንፈልግ አላሉንም? ሚስጢሩ ግልጽ ነው። የእርዳታ እህል አቅራቢው፤ የሚጭነው፤ የሚያከፋፍለው የሚያተርፍበት የሙሉ ጊዜ ሥራ ስለሆነ ነው። ለትግራይ ህዝብ ደረሰ የሚባለው ተላከ ከተባለው ኢምንቱ ነው። ገና አሜሪካና አውሮፓ ወደቦች ሳይለቅ ነው ስርቆቱ የሚጀምረው። ልክ እንደ ወያኔ የተራድኦ አቅራቢዎችም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በትግራይ ህዝብ ላይ ነጋጆች ናቸው። የትግራይ ህዝብ የፈጠራ ችሎታ ያለው፤ ታታሪና ሃገርና ወገኑን የሚወድ ህዝብ ነው። ወያኔ በዘር ፓለቲካ ከለከፈው ወዲህ ግን ብዙ ነገሮች ተዘባርቆበታል። ደግሞስ ጠበንጃ ተደግኖብህ እንዴት የጠራ እይታ ይኖርሃል? ለትግራይ ህዝብ ነጻነት የወያኔ ከስልጣን መውረድ ወሳኝ ነው። አይ ወያኔም እንዳለ ይሁን ሰላም እንፍጠር ከተባለ የሚጎዳው የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የቀረው የኢትዮጵያ ህዝብም ጭምር ነው። ለምን ቢባል ወያኔ ደም ካልፈሰሰ እንቅልፍ አይወስደም። ጭራቆች ናቸው። ሁሌም እሳት እየጫሩና እያስጫሩ ሃገርን ማመሳቸው አይቀሬ ነው። በቃኝ!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.